>
5:13 pm - Wednesday April 20, 3059

የአራት ኪሎ ችግኝ ተካዮች -  ህወሓት  ራያ ኦፍላን እና ራያ አላማጣን ይዛ ግራካሱ ተራራ ላይ ተቀምጣለች፤ አልሰማችሁ ይሆን...??? (ሀብታሙ አያሌው)

የአራት ኪሎ ችግኝ ተካዮች –  ህወሓት  ራያ ኦፍላን እና ራያ አላማጣን ይዛ ግራካሱ ተራራ ላይ ተቀምጣለች፤ አልሰማችሁ ይሆን…???
ሀብታሙ አያሌው

ጌታቸው ረዳ ዛሬም በአደባባይ ከጦርነት እና ከኃይል እርምጃ ውጪ አማራጭ የለም ሲል የህወሓትን አቋም አሳውቋል።  የሰላም ጥሪን ተፀይፈው ጦርነት ወይም ሞት ብለዋል።  ምርጫው የነሱ ሆኗል።
የአራት ኪሎ ችግኝ ተካዮችም ህወሓት  ራያ ኦፍላን እና ራያ አላማጣን ይዛ ግራካሱ ተራራ ላይ ተቀምጣ  በድርድሩ እከክልኝ ልከክልህ ትጫወታለች በለው ሲጠብቁ… ህወሓት ወደ አፋር ሾልካ ወደ ሐራ ገበያ በማቅናት የጅውቲን መስመር ዘግታ የፌደራል መንግስቱ ጉሮሮ ላይ ልትቆም አቅዳ መንቀሳቀሷ የተገለጠላቸው ዘግይቶ ነው።
አሁንም ጥብቅ እርምጃ ወስዶ ህወሓትን በልኩ ካልከረከማት በአፋር ሐራ ገበያ አድርጋ የጅውቲን መስመር መዝጋት ፣ የአፋርን አማፅያን አስተባብራ ከኦነግ ጋር በባቲ መስመር ተጨባብጣ ፣ የኢሳ አማፅያንን እሳት አስለኩሳ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ከኦነግ እና ከቤንሻንጉል አማፅያን ጋር ቀጠሮ ይዛ  አራትኪሎን ለመሳለም እንደምታስብ አትጠራጠር።
እናማ ከጀርባ መቆመሩን ትተህ በፓርላማ አሸባሪ ብለህ የፈረጅከውን የህወሓት ቡድን በመንግስታዊ ኃላፊነትህ ከፊት ቀድመህ ታገለው።  የአማራ ህዝብ በክተት ለህልውናው የሚያደርገው ትግል  ይደግፍሃል እንጂ አንተን ተክቶ ጦርነቱን የሁለት ክልል እያደረገ አይደለም።
የጋመ ጦርነት ህዝብ እየቀጠፈ ሰራዊቱ አዲስ አበባ ላይ ችግኝ ተከለ የሚል አስነዋሪ ዜና በመድገም በህዝብ ቁስል እንዳትቀልድ አደራህን።
የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ ፍርደ ገምድል አቋም ከልኩ አልፏል።  እነ ጌታቸው ረዳ ጦርነት ወይም ሞት ሲሉ ዝም ብለው አጠቃን እያሉ ሲሸልሉ አልሰማንም ብለው ህዝብን ከጥቃታቸው ለመከላከል የሚወሰድ ርምጃን እናወግዛለን ካሉ – የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ቆሞ አንሰማችሁም የሚል ምላሽ ጀባ ይላቸዋል !!
Filed in: Amharic