>
5:13 pm - Saturday April 18, 1959

አቶ አገኘሁን 'ሽጉጥህን ጠጣው' ሲሉ ለነበሩ ተሸናፊዎች.. !!!  (አሳዬ ደርቤ)

አቶ አገኘሁን ‘ሽጉጥህን ጠጣው’ ሲሉ ለነበሩ ተሸናፊዎች.. !!!
 (አሳዬ ደርቤ)

*… ‹‹የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ እሳትና ጭድ ናቸው›› በሚል ንግግሩ ህውሓትን ከፌደራል ያስባረረው አቶ ጌታቸው ረዳ ግን አላማጣ ላይ ሆኖም በብስጭት እየተንተከተከ ‹‹ኢትዮጵያን ለማንም እንዳትበጅ አድርገን እናፈራርሳታለን›› የሚል መረጃ ለኒዮርክ ታይምስ በመስጠት የኦሮሚያ ፣ የደቡብ ልዩ ሃይል ከአማራና ከአፋር ልዩ ሃይል ጋር ተሰልፎ አገሩን ይታደግ ዘንድ ጥሪ አስተላለፈ፡፡  
ስለሆነም አላማጣ ገብቶ እናቱን ከጠየቀ በኋላ በሠዓት 120 ኪሎሜትር በመሮጥ ላይ የሚገኘው አቶ ጌታቸው ረዳ ‹‹እቸኩላለሁ›› የማይል ከሆነ በመኪና ልንሸኘው እንጂ ልንዘልፈው አይገባም እላለሁ፡፡ 
 
ትሕነጎች ውጊያ ባይችሉም በውሸት ወሬ ግን ነፋስ በጎራዴ የሚከታትፉ ናቸው፡፡ በጥይት ተመትተው ሲያጣጥሩ ብታገኟቸው እንኳን ‹‹እየገደልን ነው›› እንጂ ‹‹ተመትተን ነው›› አይሏችሁም፡፡
ሰሜን እዝን ጨፍጭፈው ጦርነቱን በለኮሱ ማግሥት ሲነዙት የነበረውን ውሸት መለስ ብላችሁ አስታውሱት እስቲ…
ጄት እንጥላለን፣ ነፍጠኛውን እንቀብራለን… እያሉ ነበር ከፕላኔት ሆቴል ቆላ ተምቤን ዋሻ ውስጥ የገቡት!
ያም ሁኖ ግን የክልሉ ኤሊትና አክቲቪስት ተነጥሎ በማሰብ መርሕ ሃቁን ተጋፍጠው ክልላቸውን ከመታደግ ይልቅ ‹‹ጥይትን በውሸት ማሸነፍ ይቻላል›› የሚለውን የትሕነግን መርሕ ባንድ ልብ ተቀብለው መንኮታኮት የሚመርጡ በመሆናቸው ‹‹በባዶ ትምክሕት በጀመራችሁት ጦርነት ለውድመትና ውርደት ዳረጋችሁን›› ብለው ሊወቅሷቸው አይሞክሩም፡፡
ይሄን ሁሉ ማለት ያስፈለገኝ እንደነሱ በውሸት ፕሮፖጋንዳ እራሳችንን እንደልል ወይም ደግሞ የክልሉ መንግሥት የሚሠራውንና የሚናገረውን ሳንመረምር ባንድ ልብ እየተቀበልን ለውድቀት እንዳረግ ለማለት አይደለም፡፡
ይልቅስ ‹‹የክልሉን መሪዎች ያላግባብ ሥማቸውን አናጥፋ›› ለማለት ፈልጌ ነው፡፡ ለምሣሌ ያህል አቶ አገኘሁ ተሻገር ‹‹ወልቃይትና ራያን ያስወሰድኩ ቀን ሽጉጤን እጠጣለሁ›› በማለቱ  በርካታ የአማራ አክቲቪስቶች መሳለቂያ አድርገውት ነበር፡፡
በበኩሌ ግን በጦርነት ላይ ጠላትን ለመደምሰስ ወደ ፊት መገስገስ ብቻ ሳይሆን ወደ ኋላ መመለስም ግድ የሚል መሆኑን መገንዘብ ቢሳነን እንኳን ‹‹ፈጠን ብለህ ራያን አስመልስ›› ማለት ሲቻል በቅጽበት ውስጥ እራስን ተሸናፊ አድርጎ ‹‹ሽጉጥህን ጉረስ›› እያሉ አቶ አገኘሁን መዝለፍ ልክ አይደለም እላለሁ፡፡
ሰሜን እዝ ላይ ትንኮሳ በፈጸመች ማግሥት ተደምስሳ ብሎም ወልቃይትን ራያን ለባለቤቱ መልሳ የሸሸችውን ህውሓትን ከአሸናፊ ተርታ መድቦ አቶ አገኘሁን ተሸናፊ ማድረግ ስህተት ነው›› እላለሁ፡፡ አንዳንድ የጦር መሪዎችን መዝለፍ ከዲጂታል ወያኔዎች እንጂ ከአማራ አክቲቪስቶች የሚጠበቅ አይደለም፡፡
ሌላው ቀርቶ አቶ ጌታቸው ረዳንም ስንተች ክብሩን በሚጠብቅ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ጌቾ በቀልማዳ ምላሱ በሚነዛው ፕሮፖጋንዳ እስካሁን ድረስ ህውሓትን እንጂ እኛን ጎድቶን አያውቅም፡፡ ለምሳሌ ያህል እሱ ‹‹የአማራ ኤሊት ላይ የምናወራርደው ሒሳብ አለን›› የሚል መረጃ ባይሰጠን ኖሮ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ‹‹ሆ›› ብለን ባልተነሳን ነበረ፡፡
ሲቀጥል ደግሞ ከበላይ አካል በመጣ ትዕዛዝ ጦሩ ከኮረምና አላማጣ ከመውጣቱ ጋር ተያይዞ የጁንታው ልጆች እራሳቸው በለጠፉት ፖስት የሱዳንን ሕዝብ ከጎናቸው አሰልፈው ሲደሰቱ ነበር፡፡
‹‹የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ እሳትና ጭድ ናቸው›› በሚል ንግግሩ ህውሓትን ከፌደራል ያስባረረው አቶ ጌታቸው ረዳ ግን አላማጣ ላይ ሆኖም በብስጭት እየተንተከተከ ‹‹ኢትዮጵያን ለማንም እንዳትበጅ አድርገን እናፈራርሳታለን›› የሚል መረጃ ለኒዮርክ ታይምስ በመስጠት የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ከአማራና ከአፋር ልዩ ሃይል ጋር ተሰልፎ አገሩን ይታደግ ዘንድ ጥሪ አስተላለፈ፡፡
ስለሆነም አላማጣ ገብቶ እናቱን ከጠየቀ በኋላ በሠዓት 120 ኪሎሜትር በመሮጥ ላይ የሚገኘው አቶ ጌታቸው ረዳ ‹‹እቸኩላለሁ›› የማይል ከሆነ በመኪና ልንሸኘው እንጂ ልንዘልፈው አይገባም እላለሁ፡፡
Filed in: Amharic