>

ጊዜው አሁን ነው! (ዘመነ ካሴ)

ጊዜው አሁን ነው!

ዘመነ ካሴ

በትክክል ማን እንደ ሆንን ለወዳጅም ለጠላትም የምናሳይበት ጊዜው አሁን ነው።ባንድ አይን የምናይበት፣ ባንድ ሳንባ የምንተነፍስበት፣ ባንድ ልብ መክረን ባንድ አፍ የምንናገርበት ትክክለኛ ጊዜው አሁን ነው።ደረታችን ነፍተን ፣ ቀጥ ብለን መቆም አለብን።መንበርከክ ባርነትን እንጅ ነፃነትን አስገኝቶ አያውቅም።እልቂታችን የመሽቆጥቆጣችን ውጤት እንጅ እምቢ ባይነታችን የወለደው አይደለም።ዛሬ ላይ ቆመን ” የፈራ ይመለስ”  አይደለም ማለት ያለብን።”የፈራ ከፊታችን ዘወር ይበል!” እንጅ።
 ከስብእና ካርታ ላይ ሊሰርዝህ /ሊያጠፋህ ተማምሎ  የወሰነን ጠላት ስለ ሰው ልጅ ክቡርነት እና ስለ አብሮ መኖር አስፈላጊነት፣ ስለታሪክና ሰብአዊነት፣ ስለ መከባበርና መቻቻል አስፈላጊነት በመስበክ፣ በመለማመን፣ በመለማመጥ ልቡን አትለውጠውም።ሰይጣናዊ አላማውን አታስተወውም።በጉንጩ ይዞ እየዞረ ላያችን ላይ  ‘ ቡፍፍፍ’ የሚለውን መርዝ የምታስተፋው ማጅራቱን መተህ በመጣል ነው።
ተኝተህ ማደር የምትችለው ዳግም ተነስቶ እንዳይራመድ አድርገህ ቅልጥሙን ሰብረህ በግንባሩ ስትደፋው ነው።
~~ የጎመን በጤና ዘመን አልፏል።እጅና እግርን አጣጥፎ ቁጭ ብሎ ” ወንድሜ ጎመን በጤና ” እያልን የምንሽሎከሎክበት ዘመን አብቅቷል።ጠላትህን አፍንጫውን ይዘህ ካላንበረከክኸው ጎመኑም ጤናውም አይገኙም።የሉም።
ስለዚህ፥
√ አማራው ከቤተሰብ ጀምሮ በጎጥ፣ በቀበሌ፣ በወረዳ እያለ ዛሬውኑ መደራጀት አለበት።…. በክልሉ ውስጥ አራት ሽህ ቀበሌዎች ቢኖሩ አራት ሽህ የቀበሌ ህዝባዊ አደረጃጀቶች ይኖሩናል ማለት ነው።
√ ከ 18  እስከ 45 አመት ያለ አማራ በሙሉ ፥ እደግመዋለሁ ‘በሙሉ’ መሰረታዊ ወታደራዊ ስልጠና መውሰድ አለበት። ይህን ለማድረግ ትምህርትቤቶች ዝግ የሚሆኑበት የክረምቱ ወራት ምቹ ነው።በእያንዳንዷ የአማራ ጎጆ ውስጥ ቢያንስ አንድ ” ተዋጊ’ ሊኖረን ይገባል።ስለዚህ መሰልጠን ማሰልጠኑን ዛሬውኑ እንጀምረው።በፍጥነት የወልቃይት እና የራያ “ጣጣችን” ጨርሰን  ሙሉ ትኩረታችን ወደ መተከል እና ሸዋ ማድረግ አለብን።እዛም አካባቢ ከባድ የቤት ስራ  አፍጥጦ እየጠበቀን ነውና።
√ ስልጠና የወሰደውን ሃይል በሰሜን አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ከስር ከስር በሁሉም ስጋቱ ያለባቸው አካባቢዎች ላይ በማስፈር አማራው ራሱን በንቃት መጠበቅ አለበት።
√ በውጭ ሃገራት የሚኖሩ አቅሙና ፍላጎቱ ያላቸው አማራዎች እና ቀና ኢትዮጲያውያን እህትና ወንድሞች ስለት የሆነ የዲፕሎማሲ፣አድቮኬሲ እና ሎቢ ቡድን ፈጥሮ መነጋገርና ስራ መስራት  የሚገባበት እጅግ ወሳኝ ወቅት ላይ እንዳለን መገንዘብ ያለብን ይመስለኛል።
√ ፕሮፓጋንዳ ሳይንስ ነው።አርትም ነው።ዝምብሎ ሚዲያው ስለተገኜ ብቻ እየወጣህ ” አቅጣጫ የተቀመጠበት ሁኔታ ነው ያለው” እያልህ ምታላጋጥበት የአላዋቂ ስራ አይደለም።ጦርነቱ ሙያው እና ልምዱ ባላቸው መኮንኖች ይመራ እያልን እንዳለነው ሁሉ ፕሮፓጋንዳውም ተሰጦው፣ ሙያውና ልምዱ ባላቸው ሰዎች በጥንቃቄ መመራት ይኖርበታል።ልክ እንደ መሳሪያው ጦርነት የስነልቦና ጦርነቱም ወረቀትና አእምሮ ላይ የሰፈረ ግልፅ ስትራቴጅ ይፈልጋል።እና ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የምትፅፉ ወንድምና እህቶች፣ ዩቲዩበሮች፣ ሜንስትሪም ሚዲያው ላይ የምትሳተፉ በሙሉ ይህን ጉዳይ አጥብቃችሁ ብታስቡበት መልካም ነው።መናበብ ያስፈልጋል።
√ ተቀራርበን እንመካከር።ቡድን ወለድ ፍላጎቶች ደንበር ሆነው ሳያቆሙን ተራራ ሆነው ሳያግዱን ተቀራርበን እንመካከር።ግዴላችሁም እንመካከር።ራያና ወልቃይት ጫፍ ላይ የምትተኮስን አንዲት ጥይት ሸዋና ጎጃም ጫፍ ያሉ ጆሮዎች ጥይቷ ገና ከአፈሙዙ ሳትርቅ  እኩል መስማት የሚችሉበትን ‘አየር’ መፍጠር አለብን።ማእበሉ ግለሰብም፣ ቡድንም አካባቢም አይለይም። አይመርጥም።እኩል ነው የሚጠርገን። የጥፋት ማእበል ነፍስም አእምሮም የለውምና።ገና ከመነሻው አንድ ሆነን ካዩን እኛን ስለማጥቃት ዘራችን ስለማጥፋት የሚያስብ ጠላት በሙሉ ሴራ ከሚጎነጉንበት ወንበሩ አይነሳም።ይፈራል።እዚያው የክፋት አመዱ ላይ ሲንደባለል ይውላል።አመድ እንደቃመ ይሞታል።……
====በተረፈ የጎንደርን ተጋፋጭነትና እጅ አልሰጥም ባይነት፣ የጎጃምን አስተዋይነትና አትንኩኝ ባይነት፣ የሸዋን ተፈጥሯዊ የፖለቲካና የመንግስት አስተዳደር ጠቢብነት፣ የወሎን ፍፁም ስልጡንነትና ግፍን ተፀያፊነት እንደ ድርና ማግ ባንድ ላይ ሸምነን ተላብሰን፥እየሮጥን የማንወጣው ተራራ፣ ዋኝተን የማናቋርጠው ውቅያኖስ አይኖርም።ማንስ ደፍሮ ከፊታችን ይቆማል?
ኢትዪጲያውያን ወንድምና እህቶቻችን እንተጋገዝ።ነጩ በሬ እንደሞተ ማወቅ የሚገባው ቀዩ ወይም ጥቁሩ የመንጋ ጓደኛው ተነጥሎ በጅብ ሲበላ ቆሞ ያየለት መሆኑን መረዳት አለበት።ነገርይዮው ከጀርባው ከባድ የጅኦ ፖለቲካ ትንቅንቅም ተሽሸክሟልና እንተባበር! ። ለአማራ ያልሆነ እኩይ ሃይል ለማንም አይሆንም።ሰይጣን አንዱን ወገን ከሌላው ነጥሎ የሚወድበት ልብ የለውም።ሰይጣን ያው ሰይጣን ነውና።መርከቧ ከሰመጠች በሙሉ እንጅ ተርፎ የሚንሳፈፍ አካል አይኖራትም።…….።
አማራ ያሸንፋል!! አማራ ሲያሸንፍ ኢትዮጲያ ታሸንፋለች!
// ባለፈው ጊዜ “የመንግስት” የተናጠል የተኩስ አቁምና ሙሉ ትግራይን ለቆ መውጣት በግሌ ፍፁም ብስጭት ውስጥ ስለከተተኝ ከሁለት አመት ካንድ ወር ገደማ በኋላ ወደ ማህበራዊ ሚዲያው ስመለስ ማለት የነበረብኝን አንድ ነገር ሳልል ቀረሁ።ተንበርክኬ መግለፅ የነበረብኝ ነገር “ምስጋና” ነው። ሁኔታዎች አላመች ብለውኝ ብዘገይም፥
– የድንግል ማሪያም ልጅ ዘላለማዊ ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን።ባለፉት ዘጠኝ የውጣ ውረድ አመታት ሽህ ጊዜ ከሞት መንጋጋ ሳይሆን ከሞት ሆድ ውስጥ አውጥተኸኛል።የነ አብርሃም አምላክ ክብር ተመስገን።
-ቤተሰቦቼ በኔ ምክንያት  ያለፉት ዘጠኝ አመታት ሊገለፅ የማይችል የስነልቦና ሰቀቀን ውስጥ ወድቃችኋል።አንዳንዴ መሳሪያ አንስቶ መንግስትን የማስወገድ ሃሳብን በግሌና ከቅርቦቼ ጋር አንስቼ የወሰንሁበት 2003 አም ሳስብ ያን ውሳኔ ባልወስን የቤተሰቡን ሰቀቀን የኔንም መከራ ማስቀረት እችል ነበርን? ብዬ አስባለሁ።የሆነው ሁሉ እንዲሆን ተፅፏል።የተፃፈው ደግሞ ይፈፀም ዘንድ ግድ ይላል።ለሁሉም አመሰግናለሁ።እግዚአብሄር ዋጋችሁን ይክፈለው።
– ጓደኞቼ ቃል የለኝም።በተለይ ያለፉት ሁለት አመታት ከኔ ይልቅ እናንተ አይሆኑ ሁናችኋል።የእናንተ መሆኔ የምድራችን እድለኛው ሰው ያደርገኛል።ቃሉ ስሜቴን መግለፅ የሚችል ከሆነ አመሰግናለሁ።
– በሃገር ውስጥና ውጭ የምትኖሩ አማራዎች እና ሌሎች ኢትዮጲያውያን እህት እና ወንድሞቼ ለጭንቀታችሁ፣ ለፀሎታችሁ፣ እና ለልዩ ልዩ ድጋፋችሁ አምላክ ውለታችሁን ይክፈለው።
– በመንግስት እና ፖለቲካ መዋቅሩ ውስጥ ያላችሁ እህትና ወንድሞቼ እሳት የወለደችውን ላም እንደሆንሁባችሁ በደንብ እረዳለሁ።ላም እሳት ወለደች፣ እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወው ልጅ ሆነባት።አምሰግናለሁ።
ባጠቃላይ የህዝብ ድምፅ የእግዚአብሄር ድምፅ ነውና፣ ሰው ካዬ እግዚአብሄር አዬ ነውና ድምፃችሁ የአምላክ ድምፅ ሆኖ በህይወት ኖሬ ይኸው ምስጋናዬን ለመግለፅ በቃሁ።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ !
                   አመሰግናለሁ።//
Filed in: Amharic