>

ህወሓት ጦርነቱን ገፍቶበታል - ነዋሪዎች በፍርሃት ከቀያቸዉ እየተሰደድ ነዉ...!!! (ጀርመን ሬድዮ)

ህወሓት ጦርነቱን ገፍቶበታል – ነዋሪዎች በፍርሃት ከቀያቸዉ እየተሰደድ ነዉ…!!!

ጀርመን ሬድዮ

*… የራያ ዋጃ፣ የራያ አላማጣ እና ኮረም አካባቢዎች በህወሃት ኃይሎች መያሳዛቸውን ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች ስፍራውን ለቅቀው ለስደት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። መንግሥት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም አውጆ መከላከያ ሠራዊቱን ከመቀሌና ከተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ካስወጣ ወዲህ ህወሀት በአማራ ክልል የተያዙ ላለፉት 30 ዓመታት በትግራይ ክልል ስር የቆዩ ግዛቶችን ለማስመለስ ውጊያውን እንደሚቀጥል በይፋ ገልጿል።   
የህልውና አደጋ አጋጥሞናል ሲል መግለጫ ያወጣው የአማራ ክልላዊ መንግሥት «የህልውና አደጋውን አንድነታችንን ጠብቀን በትግላችን እንቀለብሳለን» በማለት «በየትኛውም ዘመን ሰልጥናችሁ፣ የአገርና የህዝብ ሉአላዊነት ለማስከበር በማንኛውም የመንግሥት ጸጥታ መዋቅር ውስጥ ተሰልፋችሁ ስታገለግሉ የቆያችሁና በታሪክ አጋጣሚ የሙያ ዘርፍ የቀየራችሁ የክልላችን ነዋሪዎች ለህልውናችን የምናደርገውን የትግል ጥሪ ተቀብላችሁ በክልሉ ጸጥታ መዋቅር ውስጥ እንድትቀላቀሉ» ሲል ጥሪ አቅርቧል። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች ይበርዳል ተብሎ የተገመተው ግጭት ጦርነት መልኩን ቀይሮ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች እንዳይስፋፋ ስጋታቸውን መግለጽ ጀምረዋል። ጦርነት አውዳሚ እንደመሆኑ በሺህዎች እና ሚሊየኖች የሚገመቱ ወገኖች ሕይወት ለከፋ አደጋ መዳርጉ አይቀርም። ምን መደረግ አለበት ትላላችሁ? ከፌደራል መንግሥትስ ምን ይጠበቃል?
Filed in: Amharic