>

ዐቃቤ ህግ ዛሬም ምስክሮቹን  በችሎት ፊት ማቅረብ አልቻለም!  (ባልደራስ)

ዐቃቤ ህግ ዛሬም ምስክሮቹን  በችሎት ፊት ማቅረብ አልቻለም! 

ባልደራስ 

   ከዛሬ ጀምሮ ዐቃቤ ህግ  ምስክሮቹን ማሰማት እንዲጀምር የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን ማቅረብ አልቻለም ። ምስክሮቻችንን በ15 እና 16 እናሰማለን እስከዚያ ድረስም ለምስክሮች ጥበቃ የሚያስፈልጉ ተግባራትን አከናውናለው በማለት ዐቃቤ ምስክሮቹን አለማቅረቡን ለፍ/ቤት ተናግሯል ።
ይሁን እንጂ የግፍ እስረኞች ጠበቆች ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ምክንያት ውድቅ በማድረግ ። ምስክር አሰማሙ በአምስት ቀናት የተከፋፈለው ምስክሮች ብዙ ስለሆኑ እና በሁለትና በሶስት ቀናት ስለማያልቅ ነው ። ሆኖም ምስክር በሚያቀርብበት ቀን ለምስክሮች የማደርገውን ጥበቃ አልጨረስኩም ማለት  የፍ/ቤት ትዕዛዝ አለማክበር ነው።  ዐቃቤ ህግ ምስክር ማሰማት ፍላጎት እንደሌለው ጭምር ከሁኔታው መረዳት ይቻላል ። የዐቃቤ ህግ ቀጠሮ አለማክበር እና የፍ/ቤት ትዕዛዝ አለመጠበቅ የተከሳሾች መሠረታዊ መብት የሚጥስ በመሆኑ  ዐቃቤ ህግ ምስክር ማሰማት በፈለገ ጊዜ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብቱ ተጠብቆ ክሱ ተቋርጦ ደንበኞቻችን ከእስር ይፈቱ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን እሱ በፈለገው ጊዜ ሳይሆን፤  ከዚህ ቀደም በተሰጠው ጊዜ መሰረት ከሐምሌ 14 እስከ 16 ባሉት ሶስት ቀናት ምስክሮቹን አቅርቦ እንዲያሰማ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
Filed in: Amharic