>

ይድረስ ለናፍቆት እስክንድር ነጋ ...!!!  ( የእስክንድር ነጋ ልጅ ) ሰለሞን አላምኔ

ይድረስ ለናፍቆት እስክንድር ነጋ …!!!

 ( የእስክንድር ነጋ ልጅ )
ሰለሞን አላምኔ

 አባትህ እስክንድር ነጋ ሀሙስ እለት በነበርው ችሎት ምን አዳለ ታውቃለህ ፦ ” የተከበረው ፍርድ ቤት እኛ ነፃ ሰዎች ነን ። እኔ በወያኔ ዘመን በነበረው ስርዓት በውሸት ክስ ፤ በውሸት ፍርድ ቤት ፤ በውሸት ምስክር ለ 10 አመታት ታስሪያለኩ ! ዛሬም ይሄው 11 ኛ አመቴን በእስር አስቆጥሪያለሁ ያለምንም ጥፋት ! የተከበርው ፍርድ ቤት እኔ ልጄ ሲወለድ ከእናቱ ጎን መቆም አልቻልኩም ፤ ማሳደግም አልቻልኩም ምክንያቱን በውሸት ተከስሼ እስር ቤት ነበረኩ ! ከእስር ቤት ወጥቼ ግን ልጄን ሳገኘው ልጄ ይሄን ጥያቄ ነበር የጠየቀኝ ?! ” አንተ ማን ነክ ” አባቱ መሆኔን እንኳን አያውቅም ነበር !  ብሎ ሲጨርስ እንባዎቹ በአይኑ ላይ ይታዩ ነበር የሚናገራቸው ቃሎቹም እየሰለሉ ይሰሙ ነበር ።
     አባትህ  ይሄን ቃል ሲናገር ችሎቱ ውስጥ ያለን ሰዎች እንባችንን መቆጣጠር አልቻልንም ነበር ! ወንዱም ሴቱ ያለቅስ ነበር ! ማልቀስ ያልቻለው የችሎቱ ታዳሚ ደግሞ አንገቱን ወደ መሬት አቅርቅሮ ያዝን ነበር ! ዳኞቹም ይሄን ቃል አባትህ እስክንድር ነጋ ሲናገር አይኑን ማየት እንኳን አልቻሉም ነበር ! እኔም በህይወት ዘመኔ በፍርድ ቤት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ማልቀሴ ነበር ! ማልቀሴን ያወኩት እንባወቼ እጆቼ ላይ ሲንጠባጠቡ ነበር !
     ናፍቆት እስክንድር ነጋ አባትህ ይሄን የተናገርው አዝኖ ወይም ተስፋ ቆርጦ እንዳይመስልክ ! አባትህ ያ የማይበገረው ፣ ያ የማይሰበረው የማይሸበረው ፣ ያ ሰውነት ልክ ፣ ያ ሀቅ የእውነት ተምሳሌት ፣ የዲሞክሲ የፍትሕ የእኩልነት ታጋይ ፣ የከተማው መናኝ ፣ ያ የድሎት ባይተዋር የድሆች አባት ፣ ያ ከልጁ ከናፍቆት በላይ ኢትዮጲያን የሚወድ ፣ ያ ከትዳሩ ይልቅ የአባቶቹን ሀገር ያስቀደመ ፣ ያ ከቤተሰቡ ናፍቆት ይልቅ የሀገሩ ናፍቆት የሚያንገበግበው ፣ ያ አባትህ እስክንድር ስልጣን ቤት እና ድልቅቅ ያለ መኪና ቀርቦለት ይሄ የሰው ሀቅ ነው….. ቢጫዋ ኩርቱ የድሆች ፌስታል ይሻለኛል ያለው ያ እምነተኛው አባትህ ……….. በፍፁም ትህትና ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ዳኞች ወደ ህሊናቸው ይመለሱ ዘንድ እንጅ እሱማ መቼ መንፈሱ በእንደዚህ ያለ ተልካሻ ክስ የሚሰብር ነው ።
      ታናሽ ወንድሜ ናፍቆት አባትህ የአንተ ብቻ አባት አለመሆኑን ተረዳ ! አባት የሚሊዬን ህፃናት አባት ነው ! አባት ያላቸውም ሁሉ አባት ! የሀገር አባት ! ለወጣቶችም ለጎልማሶችም ለእናቶችም አባት ነው ! ሲታሰሩ የሚያስፈታ አባት ! ችግር ሲገጣማቸው ቀድሞ የሚናገር የሚደርስ አባት ! ለእነሱ ሲል እራሱን ከውድ ልጁ እና ባለቤቱ አስበልጦ የሚሰዋ አባት ነው ያንተ አባት እስክንድር ነጋ !
    እናም አባትህ ያ የሀገር አባት እስክንድር ነጋ ነገም አሸንፎ ወጦ አንተንእንደሚኖር ነው አይደል ናፍቆት የምታስበው ?! አይመስለኝም መቸ እሱ እንደማነኛውም አባት ነው ¿ እሱ ሀገር ሰላም ሳይሆን የእሱ ሰላም ይፈልጋል እና ።
ጠዋት አባትህ በችሎት ያሰለቀሰኝ ሳይበቃኝ ከመገናኛ ወደ ሰሚት በሚወስደው መንገድ ላንተ ይሄን መልዕክት ስልክ ስንት ግዜ እንባየንን ከእይኖቼ እንዳበስኩ ያሳደገችን #የአጉንታዋ_ማርያም የክርስቶስ አናት ትመስክር !
Filed in: Amharic