>

የወገን ሰቆቃ በሳውዲ ወህኒ ‼  * - የአስሮ የማስራብ ግፍ ... ‼ (ነቢዩ ሲራክ)

የወገን ሰቆቃ በሳውዲ ወህኒ ‼ 

ነቢዩ ሲራክ

* – የአስሮ የማስራብ ግፍ … ‼
☞ ከአይን እማኝ ወዳጀ 
 
በጅዳ ሰማይ ስር …
   በጅዳ ሰማይ ሀበሻ ስር ከወትሮው የተለየ ነገር ይስተዋላል። የሳውዲ የጸጥታ ክፍል ሰራተኞች በከተማው ከሞሉት ከ20 በላይ የውጭ ዜጎች ሀበሻ በሚል የሚታዎቀውን ኢትዮጵያዊ የእኛ ዜጋ ይፈለጋል፣ ይሳደዳል ፣ ቤት ይሰበራል ይያዝና ወደ አስከፊው ወህኒ  ይወረወለራል። ተፈላጊው  ወህኒ መግባቱን ተከታትለው የሚረዱት በአረብኛ “ሸባብ”  ተብለው የሚታዎቁት ዘራፊ የአረብ ወጣቶች የተገፊውን ዜጋ ሀብት ንብረት ይዘርፉታል … 🙁
    የሀበሻ ዘር በአውራ ጎዳና ቀርቶ በሰፈር መንደሩ አይታይም።…የበረሃውን የወደብ ከተማውን  የበጋ ሙቀት ደግሞ እንደ እሳት ይለበልባል። ሀሩሩን ሙቀት እየተጋፉ ወደ እስረኛ ማቆያ ማዕከሉ ከደረሱት በጅዳ ቆንስል ስር ህዝባዊ ድጋፍ ለማድግ የተመረጡት ወገኖች በወህኒው የሰሙ ሳይሆን ያዩትን ሰከናገሩት ልብ ይሰብራል።  በተመለከቱት ስቃይና መከራ ልባቸው የተሰበረ ወገኖች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ተከታትለው በሰፊው ማስታዎሻ ይዘውታል
 …
   ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪ ወገኖቸ ከያዙኩት ማስታዎሻ ” ወዳጀ የምትላቸውን ወገን ሲሰቃይ ምላስ የሚመጥጡትን ካነቃ ፣ ካስተማራቸው መረጃውን እንድታጋራቸው እፈቅድልሃለሁ ” ያለኝ የአይን እማኝ ወዳጀ ነው። እኔም በወህኒው ከነበሩት የደረሰኝን የአይን እማኝ መረጃዎች እንዳይሰለቹ ” የወገን ሰቆቃ በሳውዲ ወህኒ ‼ ” የሚል ሰም ሰጥቸዋለሁ። ታሪኮቹን ትረዷቸው ዘንድም በእያንዳንዱ ክፍል ከጉዳዩ ጋር የሚገናኝ ስም ሰጥቸ ሰቆቃ በደሉን አቀርችሁ ዘንድ ፈቅጃለሁ ። እነሆ ክፍል አንድ … አስሮ ማስራብ  🙁
አስሮ ማስራብ ...
  የእስረኛ ማቆያ በረት መሰሉ የታሳሪዎች አዳራሽ እጅግ በጣም ግዙፍ ነው። የሰፊው አዳራሽ መስኮትና በሮቹ በፍርግርግ ብረት ተዘግተዋል። ነፍርግርግ የወህኒው ብረቶች  መካከል የሚሾልኩ የሀበሻ እጆች በዝተው ይታያሉ። በየቀዳዳው በየክፍተቱ የተዘረጉ እጆች … የሚናገሩ ያህል የሚሰማ ፣ ስቃይ እና መከራ በዝቶባቸው በፍጹም ተማጽኖ የሚርገፈገፉ ፣ ድረሱልን የሚሉ የሚመስሉ ተማለዱን ብለው የሚለምኑ እጆች… ግፍ ሲፈጸምባቸው ድረሱልን ብለው ለምነውን መልስ የማንሰጣቸው አቅም የሌለን ደካማ አቅመ ቢሶቹ  ታመናል … እኔና የቀረነው መዝጋቢዎች መልስ ላጣንለት ጉዳይ አቅም አላቸው ለሚባሉትን የሀገር የወገን ተወካይ  ዲፕሎማቶችና ልዑክ ተብየዎች የተገፊ ዜጎችን ተማጽኖ አቅርበን አጥጋቢ ምላሽ አጥተናልና ለእኒያ እጆች ተማጽኖ መፍትሔ የለንም  🙁
    ከእኒያ ጨንቋቸው እጆቻቸውን በብረቱ አሳልፈው እያፍተለተሉ ጠይቀው ካጡት ታሳሪዎች ጀርባ ደግሞ ከሩቅ የሚያስተጋቡ ድምጾች ይሰማሉ።  “ለኔ ለኔ ለኔ… እባክህን ለኔ” የሚሉ የሀበሻ የተማጽኖ ድምጾች … በጩኸቱ መካከል የሚሰማው የግፊያው ፣ መጨናነቁ ሀየከት ሌላ ጭንቀት ፣ ሌላ መከራና ሌላ ሰቆቃን ይፈጥራል … “ለኔኔኔ … አረ ለኔ አልደረሰም ለኔ” ይሉሃል  ከፍ ባለ የተማጽኖ እና የምላጃ የወገን ድምጽ … ታዲያ ይሄ ሁሉ ለምን ይመስለሃል ? ? ? የመሳፈሪያ ቅጻቸውን ሞልተው ወደ ሀገር ለመሸኘት ጓጉተው እንዳይመስልህ ። እሱ አይደለም ። ለፖስፖርታቸው ወይም የመጓጓዣ ሰነድ ሊሲፖሴ ተሰርቶ ለመቀበል አይደለም። ይሄ ሁሉ ጩኸት ፣ ትርምስ እና ግጭት ለአንዲት የሻይ ብስኩት ነው ‼ ሁለትና ሶስት ቀን ምግብ የሚባል ያልቀመሱ ወገኖችን ከማየት በላይ ምን የሚያም ነገር አለ ? 🙁   ‼ የአስሮ ማስራብ ግፍ  ‼
   ይሄ በፊልም ሳይሆን በሳውዲው ወህኒ በጅዳው ማቆያ ሳላ የሚሆነው፣ የሚያስነባ  በአካል ያታየ የወገን መከራና ስቃይ አንዱ ገጽታ ነው። አንበር ወደሚሉት በመደበኛው የወህኒ ክፍሎች ያለው ስቃይና መከራ ደግሞ  ያለው ይብሳል ተብያሁ ።
ከአይን እማኙ ወዳጀ ማስታዎሻ 
  * አሁንም የፈቀዳችሁ ብቻ Like እና  Share በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት  መልዕክቱን ታደርሱ ዘንድ በተገፊዎች ስም የጠበቀ አደራየን አቀርባለሁ ፣ በአክብሮት  እማጸናችኋለሁም  ‼
የ6 ወር ልጅን ከእናት አባቱ መለያየት  ‼
 ከእማኙ ምስክርነት ለቅምሻ እነሆ  …
  … በወህኒው አዳራሽ እየተንቀጠቀጠ የሚያነባ ፣ ብርክ የያዘውን ጎልማሳ ወጣት አባት ስቃይ እየተመለከትኩ ብዙ አሰብኩ
… እናቱም አባቱም ጥለውት ወህኒ የወረዱ የ6 ወር ህፃን ምን እየበላ ፣ ምን እየጠጣ ፣ ምን እየሆነ ከቶ ከማንስ ጋር ይሆን  ? ከቶ የብላቴናው እጣ ፈንታ ምን ይሆን  ? ብየ ራሴን ጠየቅኩና ታመምኩም … ያውም ልጅ ባዶ ቤት የአብረክ ክፋይን ጥሎ ወህኒ የመውረድ የህይዎት ዘመን ጸጸት…
   …የወላጅን ህመም ያልረዱት አሳሪዎች በጥቂት ወንጀለኞች ምክንያት በሳውዲ መንግስት ያልተፈለገ የተጠላ ሀበሻ ነውና ህመሙ ጠልቆ አልተሰማቸውምና አላመማቸውም ። የወላጅ ጭንቀት ለቅሶ ምንማቸው አልሆነም … 🙁
  በሳውዲ ሽሜሲ የአይን እማኙ ወዳጀ ምስክርነት  …  ኦ ስደት  …  ‼
ሙሉ ታሪኩ ይቀጥላል …
Filed in: Amharic