>
5:13 pm - Thursday April 19, 6514

በኦሮምያ የተጀመረው ኦርቶዶክስን የመከፋፈል ሴራ በትግራይ ፍሬ አፍርቷል...!!! (ጎዳና ያእቆብ)

በኦሮምያ የተጀመረው ኦርቶዶክስን የመከፋፈል ሴራ በትግራይ ፍሬ አፍርቷል…!!!

ጎዳና ያእቆብ

*…. አንድ ድል ለብልፅግና! የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን ለመፍጠር በዲፒሎማት ቪዛ ፈይሳ አዱኛን ወደ ሀገር አሜሪካ ማስገባት እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል ተሞክሮ ቢከሽፍም እነሆ ጥረቱ በትግራይ እየሰመረ የመጣ ይመስላል::  ደብረ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከፍቷ።

*… 
ለመሆኑ ግን ፈይሳ አዱኛ በትግርኛ ምን ይሆን???
በጥላቻ እና በፍረሀት ተጠምደህ ከእሳትና ከውድመት የተረፈችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስትፈራርስ ንቁ ተሳታፊ እየሆንክ ያለህ ኦርቶዶክሳዊ ሁላ አንተም የአፍራሽ እጅ ሆነህ እናት ቤተ ክርስቲያንህን እያፈረስክ ነውና እንኳን ደስ አለህ!!
ህዋሃት ለ40 አመታት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አከርካሪን ለመስበር ሞክሮ ያቃተውን በንቁ ተሳትፎህ ስላሳካህለት በስራህ ውጤት ደስ ይበልህ:: ሀሴትም አድርግ:: ዋናው በጉያህ የታቀፍከውንና እያወደመህ ያለውን ናፓሊዮን ሳይሆን ሚስተር ጆንስን በመፍራት ይመጣ ይሆን እያልክ የውድመቱ አካል ሁን::
ስብሀት ነጋ የተመኘውን የኦርቶዶስክን አከርካሪ መስበር የመንፈስ ልጁ የሆነው አብይ አህመድ እያሳካው ለመሆኑ ቆም ብሎ ማሰብን ይጠይቃል:: እንደማየው ከሆነ ማሰብ ደግሞ ጎጂ ባህል ሆኖብናል:: የወለደ አይሞትምና ህዋሃት በልጁ በአብይ አህመድ እና በብልፅግና አካሉን ባይሆን በሀሳቡና ሀሳቡ በወለደው ህገ መንግስትና የጎሳ ፌደራሊዝም ህያው ሆኖ ይኖራል::  ለዚህም ነው አብይ አህመድ በግብ አንድ ሆነን በአካሄድ እንለያይ ይሆናል ሲል ኮንቪንስም  ኮንፊውዝድም ሊያደርገን እንደሚሞክረው ሳይሆን በግብ ደረጃ እሱ የሚላትን አዲሲቷ ኢትዮጵያን ሳይሆን እድሜና ታሪክ ጠገብ ኢትዮጵያን ስለምንሻ በግብ እንለያያለን::
በአካሄድም ቢሆን የብልፅግና ፓርቲም እንደሚለው ለእከሌ ብሔር ይህን ያህል ለእከሌ ደግሞ ይህን ያህል የሚል ሳይሆን እንደአንድ ሕዝብ ሁላችንም በእኩልነት የምንታይበት ማንም ተረኛና ባለጊዜ የማይሆንበት ለራሱ ብሔር ተወላጅ ሞት ሀገር ምድሩን የሚሰይሰይምበትና ለቁጥር የሚታክት ሀውልት የሚያቆምበትና ለሌላው ብሔር ደግሞ ለጅምላ ቀብር እካቫተር የሚላክበት ኢትዮጵያ የህዋሃት መራሹ ኢህአዴግ  አዲሲቷ ኢትዮጵያ አካሄድ ስለሆነ በአካሄድም አንድ አይደለንም:: ፈይሳ አዱኛን አንድ አይደልንም አብይ አህመድ!  ለመሆኑ ግን ፈይሳ አዱኛ በትግርኛ ምን ይሆን?
Filed in: Amharic