>

" የምርጫ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም፤  ድምፅ ተዘርፏል...!!!" (ባልደራስ)

  1. ” የምርጫ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም፤  ድምፅ ተዘርፏል…!!!”
ባልደራስ

 *…. በፍርድ ቤት ክስ መስርቻለሁ!
 
*…. ከዚህ በኋላ የመንግስትን ስርአት አልበኝነት የምንሸከምበት ትከሻ የለንም
 
የስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተለይ የአዲስ አባባ የቅድመ ምርጫ ሂደት እና የድህረ ምርጫ  የነጻ፣ የፍትሃዊነት እና የዴሞክራሲያዊ መመዘኛዎችን የማያሟላ  መሆኑን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታውቋል።
“ገዥው ፓርቲ በዋና ፈፃሚነት፤ ምርጫ ቦርድ በተባባሪነት ዘርፈውታል። ይህም በመሆኑ በፍርድ ቤት ክስ መስርቻለው” ብሏል ፓርቲው ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የምርመራ ውጤት።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው የመጨረሻው የመራጮች ምዝገባ አሀዝ መሰረት በአዲስ አበባ 1.4 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል። ይኸው ቦርድ አጠቃላይ የምርጫ ውጤቱን ይፋ ባደረገበት ዕለት እንዳስታወቀው ደግሞ በከተማዋ 1.8 ሚሊዮን ዜጎች ድምፅ ሰጥተዋል። ይህም አራት መቶ ሺህ ዜጎች በምርጫ ቦርድ ሳይመዘገቡ መምረጣቸውን ያረጋግጣል። በመሆኑም ዝርፊያውን የራሱ የምርጫ ቦርድ ሪፖርት የሚያረጋግጥ መሆኑን ባልደራስ ጠቁሟል።
  በአዲስ አበባ የቅድመ ምርጫ ሂደትን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ሰኔ 1ቀን 2013 ዓ.ም.  በ25 ገጾች በተዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት የእጩዎች፣ መራጮች እና የፓርቲ አባላት የደህንነት ሁኔታ፤ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የታዩ
መሰናክሎችን እና  በምርጫ ቦርድ በኩል የታዩ ችግሮች፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ፣ የመራጮች መዝገብባ እና የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀምን አስመልክቶ  ከፍተኛ ችግር የነበረበት እና የምርጫ መመዘኛ ትንሹን መስፈርት ያላሟላ እንደነበር ገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የአዲስ አበባ ምርጫ እና ድህረ ምርጫ ሂደትን በተመለከተ ባልደራስ ያካሄደውን የጥናት ውጤት በዋናው ቢሮ በዛሬው ዕለት በተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል ። የጥናት ውጤቱ በ30 ገጾች እና በ8 ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው። የሚከተሉትን አንኳር ጉዳዮችም ዳሷል፦
~ የድምፅ አሰጣጡን ስነ-ስርዓት እና የቆጠራ ሂደቱን
~ በድምፅ አሰጣጥ ሂደት በድምፅ መስጫ ወረቀቶች  ላይ የታዩ ክፍተቶችን
~ የቅሬታ አፈታት
~ የፓርቲ ወኪሎች ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች
~የምርጫ አስፈፃሚዎች ማንነት እና ያሳዩዋቸው ተግባራት
~ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የነበራቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ
~ በመራጮች ላይ የተፈጠሩ ጫናዎች
~ የምርጫ ጣቢያዎችን እና የምርጫ አዋጁን መቃኘት
በአጠቃላይ በድምፅ መስጫው ቀን እና በድህረ ምርጫው ቀናት የታዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ዳሷል።  መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን ሳይናሳዊ እና አስረጂ በሆኑ የአጠናን ስልቶች አቅርቧል።
የምርጫውን  ውጤት አልቀበለውም ‼
ባልደራስ የምርጫውን ውጤት አልቀበ ለውምአለ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፤ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን ገምግሞ ውጤቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
ግምገማው የአዲስ አበባ ምርጫ እና ድህረ ምርጫ ሂደትን የተመለከተ ነው፡፡
በውጤቱም ባልደራስ ፤ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ስለዘረፉት የዚህን ምርጫ ውጤት በፍፁም አልቀበልም ብሏል፡፡
ገዥው ፓርቲ በዋና ፈፃሚነት፤ ምርጫ ቦርድ በተባባሪነት ምርጫውን ስለዘረፉት  በፍርድ ቤት ከስሻለሁ ሲል የግምገማ ውጤቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫ አሳውቋል፡፡
ይህ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በምርጫ ቀን እና በድህረ ምርጫ ባሉት ቀናት የታዩ ተግዳሮቶችን የሚዳስስ ነው፡፡
እንደ ቅድመ ምርጫ ሂደቱ ጥናት ሪፖርት ውጤት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በዕጩዎች፣ በፓርቲው በአባላትና በመራጮች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች (ስድብ፣ ዛቻ እና እስር) እንደተከናወኑበት ከጥናቱ መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡
በአንድ የምርጫ ጣቢያ ክልል ከአንድ በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው እንደነበር የጥናት ቡድኑ በምርመራ ግኝቱ አመልክቷል፡፡ ይህ ደግሞ ምርጫ ቦርድ ካወጣው ህግ ጋር የሚፃረር ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ከነዋሪው ህዝብ ብዛት ጋር የማይመጣጠኑ እና ቁጥራቸው አነስተኛ እንደነበር ጥናቱ አስገንዝቧል፡፡
የጥናቱ ግኝት እንደሚያሳየው ብዙዎቹ የምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንደማያውቁ በጥናቱ አማካኝነት ለመረዳት ተችሏል፡፡
የምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ጠንቅቀው ላለማወቃቸው ዋናው ምክንያት የምርጫ ቦርድ የምርጫ አስፈፃሚዎች አመላመል ብቃትን ሳይሆን ማንነት መሰረት ባደረገ መልኩ ስለሆነ እንደሆነ የጥናቱ ግኝት ያሳያል፡፡
ስለሆነም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፤ምርጫው ስለተዘረፈ ፤ የምርጫውን ውጤት በፍፁም አልቀበለውም ብሏል፡፡
ከዚህ በኋላ የመንግስትን ስርአት አልበኝነት የምንሸከምበት ትከሻ የለንም
Filed in: Amharic