“አንድ Dollar ብቻ…!!!’
ተመስገን ደሳለኝ
ፍትሕ መጽሔት የአየር መንገዱን ጉድ ሰፋ ባለ የምርመራ ሪፖርት ይዛ መጥታለች!
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማሪያም ኢትዮጵያን እንዴት እያደማት እንዳለ ፍትሕ መጽሔት በምርመራ ሪፖርቷ በሰፊው ታስቃኛችኋለች።
‘አንድ Dollar ብቻ’ ለምን ይመስልሃል?
ለአውሮፕላን ኪራይ ነዋ! ያውም በወር!!
ኢትዮጵያን እየወጉ ያሉ ትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዛሬም የወር ደመወዝተኞች ናቸው። ከነ ሙሉ ጥቅማጥቅማቸው ደመወዛቸው በሂሳብ ቁጥራቸው በየወሩ ይገባላቸዋል። በዓለም ታሪክ የገዛ ሀገራቸውን እየወጉ፣ ከሚወጉት ሀገር መልሰው ጠቀም ያለ ደመወዝ በየወሩ የወሰዱ ስለመኖራቸው ከኢትዮጵያ በስተቀር ርግጠኛ አይደለሁም።
የገዛ ሀገሩን በሳይበር ጥቃት ውድ መረጃዎችን ኦና የሚያስደርግ ባንዳ የት እንዳለ ማወቅ ከፈለክ የምርመራ ሪፖርቱን አንብብ!
ከጥቅምት 24/2013 የሰሜን ዕዝ ከጀርባ መወጋት በኋላ በርካታ ተፈላጊ ወንጀለኞች በአየር መንገዱ በኩል ከኢትዮጵያ ሲወጡ ጠያቂ አልነበራቸውም።
ገራሚው እውነታ በአየር መንገዱ ታሪክ ግዘፍ የሚነሳ ወንጀል የፈፀመው ሰው ከኢትዮጵያ በጥቂት ማይልሶች ርቀት የሚኖር መሆኑ ነው። ለነገሩ ቀጣሪና ተልዕኮ አመቻማቹስ በሥልጣን ላይ አይደል እንዴ!
የሆነው ሁኖ ኢትዮጵያ በዓላማ እና በዕቅድ ነው እየደማች ያለችው። ደሟን የመጠጡ የትግሬ ወንጀለኞች መቅኔዋን አፍስሰው አጥንቷን ለመስበር በመታተር ላይ ናቸው።
አልገባህ ያለኝ የዐቢይ አህመድ ፍላጎት ነው። ከዚህ ሁሉ ጉድ በኋላም የሀገር ከዳተኛ ወንጀለኞች በኃላፊነት እንዲቀጥሉ መፍቀድ ምን የሚሉት አመራር ነው?
ተወልደ ገብረማርያም የሚባል የእናት ጡት ነካሽ በስራ አስፈጻሚነት እስከቀጠለ ድረስ በመጭው ጊዜ ኢትዮጵያን አብዝቶ የሚያዋርድ ጉድ ከዚህ አየር መንገድ ጠብቁ!! ያው ‘ወያኔ ያልመራት ኢትዮጵያ ውልቅልቋ ይውጣ’ ነው ዓላማው!
በአደባባይ መሰቀል ያለባቸው ወንጀለኞች ዱባይ ላይ ተቀምጠው ለዳግም ጥፋት ኢትዮጵያ ላይ ሴራ ሲያኝኩ ይውላሉ! ይርጋ ገብረመድኀን አንዱ ማሳያ ነው!!
በአንድ ጎን በአየር መንገዱ በጀት የኢትዮጵያን ጦር ሲወጉ ይውላሉ፤ ውጭ ያሉት ደግሞ ለሌላ ዙር ከባድ ወንጀል እየተዘጋጁ ነው። ለሁሉም አመቻማቹ ወገናቸው ደግሞ በኃላፊነቱ እንደተሰየመ ነው! አጃዒብ ነው!!
ለሁሉም ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ መስከረም 15/2014 ለንባብ የምትውለውን ፍትሕ መጽሔት ያንብቡ፤ ኢትዮጵያ እንዴት በከፋ ሁኔታ እየደማች እንዳለ በዚህ ምርመራ ላይ ይመለከታሉ።