>
5:26 pm - Thursday September 15, 6467

የኦህዴዳዉያን መፈክር:- "አህያ በናዝሬት አይበሳቆል/አይታረድ፤ አማራ ግን በወለጋ ይታረድ! ዝም በሉ....!!! (ሸንቁጥ አየለ)

የኦህዴዳዉያን መፈክር:-
“አህያ በናዝሬት አይበሳቆል/አይታረድ፤ አማራ ግን በወለጋ ይታረድ! ዝም በሉ….!!!
ሸንቁጥ አየለ

*….. ስለሚጨፈጨፈዉ አማራ ከተናገራችሁ ኦነግ/ሸኔን ታስከፉብናላችሁ”
የኦህዴዳዉያን ካድሬዎች እና እግር አጣቢዎች ለእንሰሳት በተለይም ለአህያ መበሳቆል/መታረድ ሰሞኑን ጠበቃና ተቆርቋሪ ሆነዉ ብዙ ይለፈልፋሉ::
ብዙ ይጮሃሉ::በወለጋ ስለሚያልቀዉ አማራ ግን አንድም ኦህዴድ/ካድሬዎቻቸዉ እና የኦህዴድ ምሁራን ትንፍሽ ብሎ አያዉቅም::እረ ኦህዴዱ ቀርቶ የኦህዴድ ደጋፊዎች ትንፍሽ አይሉም::
——-
ሆሆይ…ለካ የኦህዴድ እግር አጣቢዉ ብአዴን እና ብአዴን የቀፈቀፋቸዉ በአማራ ብሄረተኝነት ካባ የተጠቀለሉትም “ዝም በሉ ዝም” እንበል ተባብለዋል::ኦህዴዳቸዉ እንዳይቀዬም መሆኑ ነዉ::
 ——-
የኦህዴዳዉያን መፈክር ጠቅለል ብሎ ሲቀርብ እንዲህ ይላል “አህያ በናዝሬት አይታረድ::አማራ ግን በወለጋ ይታረድ::ዝም በሉ::ስለሚጨፈጨፈዉ አማራ ከተናገራችሁ ኦነግ/ሸኔን ታስከፉብናላችሁ” የሚል ነዉ::
ደግሞ እኮ ኦህዴዳዉያን ሁሉ እንደ ሳሙና እቃ አንድ መሆናቸዉ ነዉ የሚገርመዉ:: እንዴት ከመሃላቸዉ አንድ ሰዉ ይጠፋል?
አንድ ሰዉ? አንድ ?
——-
ኦህዴዳዉያን በእነሱ ቤት የክፍለ ዘመኑ የብጥ ስትራቴጂ ብለዉት “አማራን ከኦሮሚያ ማጽዳት::ህዉሃትን ለማጥፋት ከሆዳሙ ብአዴን ጋር ተባብሮ እንዲሁም ብሄረተኛ ነኝ ባዩን አማራ አደናግሮ መያዝ” የሚል ብሂል ይዘዋል:: ለጊዜዉ ሰርቶላቸዋል::
—–
የኦህዴድ መከላከያ የአማራ አርሶ አደር በራሱ እንዲዋጋ አምስት ዞኖችን ለህዉሃት አስረክበዉ ኦህዴዳዊ መከላከያቸዉን ይዘዉ ወጥተዋል::
የመከላከያ አዛዦቹ እና ናዛዦቹ ኦህዴዳዉያን ናቸዉ::
ሌላዉ ቀርቶ በራሱ ለሚዋጋዉ የአማራ አርሶ አደር መሳሪያ እንኳን እንዳይቀርብለት ከልክለዋል::
—————–
የቀን ጉዳይ ሆኖ ነዉ እንጂ ቀኑ ሲደርስ የብድሩን ዋጋ ታዩታላቹ::የሰፈራችሁት ስፍር ይመለስላችኋል::
“የቀን እንጂ የሰዉ ጀግና የለዉም እንዲል” የአማሮች ብሂል::
Filed in: Amharic