መንግስታዊ ጭፍጨፋ በወለጋ
ይድረስ ለመላው አማራው ሕዝብ – ኦህዴድ መራሹ ብልጽግና ከ60ሺህ በላይ በሆኑ አማራዊያን ላይ ግልጽ የጭፍጨፋ ዘመቻ አዘዘ -!!
ወንድወሰን ተክሉ
የኦሮሚያ ክልል ኬሚኒኬሽን ቢሮ ኋላፊ በወለጋ ኪረሙ ወረዳ ከጨፍጫፊው ቡድን ጭፍጨፋ ህይወታቸውን ለማትረፍ አምልጠው በየጫካው የተሸሽጉትን አማራዊያንን « በመንግስት ላይ የሸፈቱ ሽፍቶች ናቸው። እኛም አድነን ያሉበት ገብተን እንጨርሳቸዋለን» በማለት በአማራ ተወላጆች ላይ የተከፈተው የኦነግ ሸኔ ጭፍጨፋ የተባለው ሙሉ በሙሉ ተቀይሮ ወደ መንግስታዊ ጭፍጨፋነት መለወጡን ባለስልጣኑ በይፋ አውጇል።
ሕዝባችን በግፍ እየተጨፈጨፈ ያለው ሽፍታ በሚሉትና በዳቦ ስሙ ኦነግ ሸኔ በሚባል ኋይል ሳይሆን በሽመልስ አብዲሳ በሚመራው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኋይል ወይም እራሱን ብልጽግና ብሎ በሚጠራው መንግስት መሆኑን ከዚህ የበለጠ ይፋዊ ማስረጃና ማረጋገጫ አያስፈልግም።
የባለስልጣኑ አገላለጽ ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካ የሸሹትን የአማራ ተወላጆችን ለምን ቁጭ ብለው ተቀምጠው ተጨፍጭፈው ማለቅ ሲገባቸው ወደ ጫካ በመሸሽ ህይወታቸውን ሊያተርፉ ቻሉ በሚል ንዴት በመንግስት ላይ የሸፈቱ ሽፍቶች ስለሆኑ ያሉበት ቦታ አድነን በመያዝ እንጨርሳቸዋለን በማለት የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኋይል መታዘዙን ነው የገለጸው።
ይህ ማለት ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ጭፍጨፋ እለት አቢይ አህመድ አሊ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ነኝ የሚለውን ዶ/ር ይልቃል የሚባለውን ሰውዬ በሚያስጎበኘው የስንዴ እርሻ ምርት ውስጥ ሆኖ አንገቱን በማቀፍ « መደራጀት ለእርሻ እንጂ ክላሽ ታጥቆ ለጦርነት መሆን አይገባም። ገበሬ ትራክተርና ኮምባይነር ለመግዛት መደራጀት ይገባዋል እንጂ እያንዳንዱ ገበሬ ክላሽ እየገዛ ለጦርነት መደራጀት አይገባውም….» እያለ ሲናገር የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ነኝ ባዩ ዶ/ር ይልቃል ተብዬው አንገቱን እያወዛወዘ በእውነት ተናግረሃል ስምምነቱን የገለጸበትን ሁኔታ በወለጋ ያሉት አማራዊያን ነፍሳቸውን ለማዳን ብለው ያነገቡትን የግል መሳሪያን እንደ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ የታጠቁ አድርጎ ማሳያውና ብሎም ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ጫካ የሸሹበትን ምክንያት ደግሞ ህይወታቸውን ለማዳን ብለው ያደረጉት ሽሽት ሳይሆን በመንግስት ላይ የፈጸሙት የሽፍትነት ተግባር አድርጎ በመግለጽ አመጸኛ ሽፍቶችን ደመሰስን ለማለት የሽፍታ ስም እንደሰጧቸው መረዳት ይቻላል።
ገዳይ አስገዳይ ጨፍጫፊና አስጨፍጫፊ ሰለባዎቻቸውን በትክክለኛ ስምና ማንነት እየጠሩ የሚገድላቸውም ሆነ የሚጨፈጭፏቸው ሳይሆን ሽፍታ መጤ ሰፋሪ ወዘተ ስያሜን እየሰጡ የሚጨፈጭፉ መሆናቸው ይታወቃል።
ይህ የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ኋላፊ በአማራ ላይ የተከፈተውን ማንነት ተኮር ጭፍጨፋን መንግስታዊ ዘመቻ መሆኑን ከቃላት በላይ በግልጽ ይፋ የሚያሳውቅ በመሆኑ መላው የአማራ ህዝብ የብልጽግና መራሹ አስኴል በሆነው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኦህዴድና ባህርዳር ላይ በተቀመጠው ባልደረባው የአማራ ክልላዊ መንግስት ተብዬ ብአዴን ጋር በመተባበር በወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በሙሉ ጨፍጭፎ ለመጨረስና ለማጽዳት ግልጽ መንግስታዊ ዘመቻ መታወጁን መላው አማራ በያለበት ሆኖ በማወቅ ማድረግ ያለበትን እንዲያደርግ በጥብቅ እናስገነዝባለን።
ከመስከረም 30ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያለማቌረጥ እየተካሄደ ባለው ጭፍጨፋ በመቶ የሚቆጠሩ አማራዊያን በግፍ የተገደሉ ሲሆን ወደ 60ሺህ የሚጠጋውን እና ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ በየጫካው ተሸሽጎ ያለውን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ በመንህስት ላይ የሸፈተ ሽፍታ የሚል ታፔላ ለጥፈውበት መንግስታዊ ሰራዊት ያዘመቱበት መሆኑ ታውቆ በአካል የምትችል ፈጥነህ ወዱስፍራው በቡሬ በኩል እንድትገሰግስ በተለያየ መንግስታዊ ተቌም ውስጥ ያለህ የአማራ ተወላጅ በሙሉ ባለህ ኋላፊነት እና አቅምና ሙያ ተጠቅመህ የወገኖችህን ህይወት እንድትታደግ መረባረብ ግዴታችሁ እንደሆነ ተገንዝባችሁ ፈጣን እርምጃ በመወሰድ ለወገኔቻችን እንድትደርሱ በጥብቅ እናሳስባለን።,