>
5:14 pm - Thursday April 20, 8141

የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመቀሌ የመስፍን ኢንጂነሪንግ ላይ ከፍተኛ የአየር ድብደባ ፉጸመ...!!! (ሰለሞን ዳኛቸው)

የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመቀሌ የመስፍን ኢንጂነሪንግ ላይ ከፍተኛ የአየር ድብደባ ፉጸመ…!!!
ሰለሞን ዳኛቸው


     የኢትዮጵያ አየር ሃይል ጀቶች ዛሬ ረፋዱ አራት  ሰዓት ላይ መቀሌ በሚገኙት የህውሃት የጦር ሰፈሮችና በተለይም መስፍን ኢንጂነሪንግ በሚሰኘው የተሽከርካሪዎችና የጦር ምህንድስና ማምረቻ ተቋም ላይ የቦምብ ጣቃት  ማድረሳቸዉ  ዘገባዎች አመለከቱ።
  የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዲፕሎማቶችንና በመቀሌ ከተማ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው የኢትዮጵያ አየር ሃይል ጀቶች በዛሬው ጥቃታቸው በተለይም መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ  ተቋም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቀዋል።
    የአይን እማኞቹ ጨምረው እንደጠቀሱት የጦር ጀቶቹ ዘቅ ብለው ጥቃቱን ሲያደርሱ ማየታቸውንና በድብደባውም ተቋሙ በቃጠሎ መጋየቱን ጠቁመው፤ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፣ ወደ አመድነትም ተቀይሯል ማለታቸውን ኤፍፒ ጨምሮ ገልፆል።
“መከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎችን በተመለከተ  የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣  በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው። የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች  ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ  የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው።”
 በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በደረሰው በዚሁ የአየር ድብደባ በሰዎች ላይ ጉዳት ስለደረሰው ጉዳት  በዘገባው አልሰፈረም።
በመቐለ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የመሳሪያ ማከማቻ፣ መስሪያ እና መጠገኛ ሆኗል።
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በመቐለ ከተማ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የጦር መሳሪያ ማከማቻ፣ መስሪያ እና የከባድ መሳሪያዎች መጠገኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ታማኝ ምንጮች ነግረውናል። እንደምንጮቻችን ገለጻ አሸባሪው ቡድን በመቐለ ከተማ የሚገኘውን የመስፍን ኢንዱስትሪያልን ሙሉ በሙሉ የመሳሪያ ማከማቻ እና ማምረቻ እንዲሁም የከባድ መሳሪያዎች የጥገና ማዕከል አድርጎ እየተጠቀመበት ነው።
የኢፌዲሪ አየር ኃይል በመቐለ ከተማ የሚገኙና አሸባሪ ቡድኑ ለሽብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን ስፍራዎች፣ እና መሳሪያዎች ላይ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። መከላከያ ሰራዊቱ በአየር ኃይሉ አማካኝነት በመቐለ ከተማ የሚገኙ የግንኙነት መሳሪያዎችን እና ታወሮችን የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምባቸው መቆየቱን በማረጋገጥ እርምጃ የወሰደ ሲሆን ዛሬም የአስቸኳይ ጊዜ ማጣሪያ ባወጣው መረጃ የሽብር ቡድኑ ለመሳሪያ ማከማቻነት እና ለጥፋት ስራው የሚጠቀምባቸው አካባቢዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አረጋግጧል።
Filed in: Amharic