>

የእነ እስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ  !! (ዘመድኩን በቀለ )

 ሰበር ወሬ… ሰበር ዜና  !!

የእነ እስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ  !!

… ችሎቱ በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ መሰረት የእነ እስክንድር ነጋን የፍርድ ሂደት ለማቀላጠፍ የተሰየመው ችሎት ዛሬ በጠዋት ነው የተሰየመው። ዳኞች ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል። ተከሳሾችም፣ ዐቃቤ ሕግም በችሎቱ ተገኝተዋል። ጋዜጠኞችም ታዛቢና የእስረኞቹ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመዶችና አድናቂዎቻቸውም ጠበቆችም በችሎቱ ታድመዋል። ዕለቱ ደግሞ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የሚሰሙበት ዕለት ነው የተባለው። ከዓመት በላይ የታሸው ችሎት ጀመረ።

… ከሳሽ ዐቃቤ ሕግም መናገር ጀመረ…

“… ክቡር ፍርድ ቤት… እርግጥ ነው እነ እስክንድር ነጋ ላይ ይመሰክሩልኛል ብዬ ያዘጋጀኋቸው 21 ምስክሮች ነበሩ። ከ21 ምስክሮቼ ውስጥ 12 በዚህ ጉዳይ ላይ አንመሰክርም ብለውኛል። አሁን ለጊዜው እየተደራደርኩ ያለሁት ከ9ኙ ጋር ብቻ ነው። እናም ክቡር ፍርድ ቤት ሆይ የቀሩትን ዘጠኙን ምስክሮቼን ለማግባባት እንዲመሰክሩልኝ ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል። እኒህ ዘጠኙንም እያግባባኋቸው ያሉትንም ምስክሮቼንም ቢሆን ስማችን በማኅበራዊ የትስስር አውታሮች እና በሚዲያዎች የሚወጣ ከሆነ ለመመስከር አንፈልግም እያሉኝም ነው። ስለዚህ የምስክሮቼ ስማቸው በሚዲያ መውጣት የለበትም። ፍርድቤቱ ይህን ትእዛዝ ይስጥልኝ። ስማቸው እና ማንነታቸው የሚገለጥ ከሆነ ግን ምስክር ማሰማቱን እንተወዋለን።”

“…ፍርድ ቤቱም መልሰ… እንዲህም አለ። “በዚህ እና በሌሎቹ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት 8:30 እንገናኝ ብሎ ችሎቱን ለምሳ እረፍት ሰጥቶ ተነሣ።

… ከሰዓት በኋላ።

… ችሎቱን ለመታደም ጋዜጠኞች… የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ቡድኖች… የባልደራስ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ወደ ፍትሕ አዳራሽ አመሩ። ችሎቱ ተቀይሮ ጠበቃቸው። እናም ጠባብ በሆነው ችሎት ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ወኪሎች፣ ከህዝብም ዕድሜያቸው ጠና ያሉቱ ተመርጠው እንዲገቡ ተደረገ። ሌላው ህዝብ በውጭ ቀረ።

… ሙግቱ የግራ ቀኝ ክርክሩ ደራ። የእነ እስክንድር ጠበቆች የወመሕግ…124 እና 136 ጠቅሰው ዐቃቤ ሕግ ምስክር አሰማለሁ ካለ በኋላ በሕጉ መሠረት ምስክሮቹን አቅርቦ ቃለ መሃላ ፈጽመው እንዲመሰክሩ ማድረግ ነው እንጂ የምን መሽኮርመም ነው ብለው ሞገቱ። ዐቃቤ ሕግም እምቢዮ አለ።

…ፍርድ ቤቱም ውሰነ። የምስክሮቹም ስም ዝርዝራቸው ይሰጥ። ተባለ ተሰጠ። በዚሁ መሠረት የመስካሪዎቹም ስም ዝርዝርም ታወቀ። እናም ነገ ጠዋት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ በችሎት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመው ምስክርነታቸውን እንዲሰጡም ወሰነ። በዚሁ መሠረት ሁለቱ እስክንድርን እስርቤት አብረውት ታስረው የነበሩ እንደሆነነ ከመነገሩ በቀር ማንነታቸው ያልታወቁ በስም የተገለጡት መስካሪዎች በነገው ዕለት ቀርበው እነ እስክንድር ከጃዋር ጋር ተመሳጥረው በኦሮሚያ ከቄሮ ጋር ዐመፅ ማስነሳታቸውን መጽሐፍ ቅዱስ መትተው በመማል ሊመሰክሩ መዘጋጀታቸው ነው የተነገረው።

1… ፈንታሁን አሰፋ

2… መንበረ በቀለ

3… ወርቁ ታደሰ

4…  ፍፁም ተሰማ

5… ደረጀ ግዛው

6… ቴዎድሮስ ለማ

7… ያየህ ብርሃኑ

8… ጌትነት ተስፋየ

9 …ትንሣኤ ማሞ~ የነገ ጠዋት መስካሪዎች ናቸው ተብሏል። ተቺዎች በሙሉ ቄሮዎች አይደሉ እንዴ? በማለት ከወዲሁ ፉተታ ጀምረዋል።

… የፍርድ ቤት ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ መጨረሻውን እንይ እና እነዚህ ስሞች የእውነት ስም ስለመሆናቸው… መታወቂያም ተሠርቶላቸው የተዘጋጁ ይሁኑ አይሁኑ… ሃይማኖታቸውንም ከቀረቡ በኋላ ይፋ የሚሆንበትን መንገድ እናሳውቃለን ብለዋል ተብሏል።

… በከሰዓቱ የችሎት አዳራሽ መቀየር የመሃል ዳኛው የእኔ ስህተት ነው በመላት ከነገ ጀምሮ ግን ችሎቱ በቀደመው የፍትህ አዳራሽ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። እስክንድር ኦርቶዶክስ ነው። የተዋሕዶም አማኝ ነው። በችሎቱ ላይ የነበሩ የሃይማኖት አባት ካህን መስቀል ያሳልሙት ዘንድ ቢጠይቅም ተከልክሏል። የሆነው ሆኖ አዲስ አበቤ ዛሬ ግልብጥ ብሎ ነው ችሎቱን ለመከታተል በስፍራው የተገኘው። ነገም ጠዋት እንዲሁ እንደ ዛሬ ለመገኘት ቀጠሮ ይዞው አዲስ አበቤዎች ተለያይተዋል።

… የነገ ሰው ይበለን። ምስክሮቹ ቀርበው ምለው የሚመሰክሩትን የምስክርነት ቃላቸውንና ሌሎቹንም የፍርድ ቤት ውሎዎች አደርሳችኋለሁ።

• ሰለም አምሹ፣ እደሩ፣ ዋሉ

Filed in: Amharic