>

ይድረሰ ለኢትዮጵያውያን - እስከመቼ  ?! ( ዘምሳሌ)

ይድረሰ ለኢትዮጵያውያን

እስከመቼ  ?!

 

 ዘምሳሌ


ተግባር የለሽ  ዲስኩር  ፖርላማ ሲለፈፍ
ለዛፉ ሲጨነቁ ህዝብአዳም   ሲረግፍ
ወለጋና ሰሜን የዘር ተኮሩ  ግፍ
በየቀን ሚወድቁት የኢትዮጵያ አዕላፍ

በደኖ አርባጉጉ ገለምሶና ወተር
የጋራሙለታው የአሰቦትም መንደር
በሸቤ አጋሮ ኪረሙ  ጭናም ስር
ቤኔሻንጉል ጉምዝ የአምሀራ ልጅ መኸር

በሰው ነፍስ ነቀላ ዛፍ መትከል ተይዞ
በደመራው መድረክ በህልምእዣቱ ጉዞ
በገጀራ ድምቀት አንገት ተጠምዝዞ
ብልፅግና ፈረስ መደመር ታግዞ

በፌዘኛ መንግሥት   ስትመራ ሀገር
ልማት ተረኝነት  በኦሆዲዶች ሰፈር
በከተማ ዳቦ አዲስ ምርት ሲቆጠር
ወለጋ አፋር   ወሎ  ሬሳ  ሲደረደር

ተቃዋሚ  አሳፍሮ  ሽቅብ ተመንጥቆ
ለአኩራፊ  ጠበኛ  ጥቂት ስልጣን ለቆ
የሀገሪቷ  ክብር አሽቆልቁሎ ውድቆ
የሁለት ዘረኞች   ፀብ  እውነትን  ጨፍልቆ

መፍትሔ  ያጣ እልቂት ሰቆቃ እያበዛ
ትውልደ አምሀራውን  ሲፈጁት  እንደዛ
እይተው   እንዳላየ  ሆነው  እንደዋዛ
ጭፍኑ አስተዳደር  ደደቦች  ሲያበዛ

እርጉሙ ነቀርሳ  ሀገርን አራቁቶ
ሕዝቡ ባገሩ ላይ  በአገዛዝ ተከድቶ
ለመብቱ ማይቆመው ሁሉ  በአንድ ወጥቶ
እስከመቼ ይሆን ሚቆየው ተዘግቶ
ኢትዮጵያን ዘንግቶ
እስከመቼ …

Filed in: Amharic