>

ጅብ ሊበላህ ሲመጣ ብላውና ተቀደስ ....!!! (መስቀሉ አየለ)

ጅብ ሊበላህ ሲመጣ ብላውና ተቀደስ ….!!!
(መስቀሉ አየለ)

*.... እዝራ ስቱኤል እንደጻፈው፤ ባንድ ወቅት  እስራኤላውያንም በአሕዛቦች እጅ በምርኮ ሳሉ የሆኑትን ሲገልጽ “ግናይቱ እንደጠፋ፣ ዘመራ ዘውዳችን እንደተወሰደ፣ ካህናቶቻችን እንደተጎተቱ፣ ሚስቶቻችን እንደተደፈሩ፣ ከምንም በላይ የህግ ማደሪያ ታቦታችን ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች አይቀርም” እያለ ቁጭቱን ወረቀት ላይ ሲያሰፍር ስለዛሬይቱ ኢትዮጵያ የሚናገር ይመስል ነበር።
የእነ ራስ ስሁለ ሚካኤል የልጅ ልጆጆጆች አያያያያቶቻቸው በሄዱበት መንገድ መንጎዱን ቀጥለውበታል። የእናት ኢትዮጵያን ጡት የመንከስ  የታሪክ ውርስ በተመለከተ የጆሮውን በአዋጅ አድርገውታል። በእዚህ በኩል እናት፣ አባት፣ ልጅ አዋቂ፣ ገበሬ፣ መነኩሴ፣ ቃልቻ፣ አናጢ፣ ቁራሌው፣ ልዋጭ ልዋጭ፤ ብሎ ልዩነት የለም። “እንደ ህዝብ እንወጋለን፣ እንዋጋለን ” ብለው መንገድ ገብተዋል። የትናት ኢትዮጵያ ዛሬ የለችምና መንገድ መንግባታቸው መሃል ሸዋ ላይ ለመንገስ እንዳልሆነ ያውቁታል። ተከዜን ሲሻገሩ እነርሱ እንደተናገሩት “ከአማራ ጋር ሂሳብ ሊያወራርዱ”፣ መሃል ሸዋን ቢደርሱ ደግሞ ያቆሰሏትን “ኢትዮጵያ ገድለውና ገንዘው በመቅበር” ተነቅሰውት የኖሩትን የደደቢት ማኔፌስቶ ዳር ሊያደርሱ መሆኑን በሚገባን ቋንቋ ነግረውናል።
በሃሰት ተደማሪዎችና በጦሩ ውስጥ በመሸጉ አምስተኛ  እረድፈኞች ጥምር ሴራ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ወሰንና ህዝብ  በእነዚህ የሰይጣን ጭፍሮች እጅ ከገባ ወራቶች የተቆጠሩ ሲሆን እንደ ህዝብ እንደ እነዚህ ባሉ የጨለማው አለም አበጋዞች እጅ  መውደቅ ማለት መልኩ ምን ..እንደሚመስል በውስጡ ያለፉት ወገኖቻችን አንድ ሁለት ብለው በመዘርዘር ሰሞኑን እንዳጋሩን፣
” ፩ ፎቶግራፍ ተነስተው ፖስት ካደረጉ በኋላ የቴሌ ታወሮችን በመመምታት ኔትወርክ ያጠፋሉ። 
፪ ሰውን ሁሉ ወደቤት እንዲገባ ትዕዛዝ ይሰጣሉ።
፫ ሞባይል ይቀማሉ፤ ይወስዳሉ፤ ምንም ሳያስቀሩ። 
፬ የተዘጋ ማንኛውንም መኖሪያ ቤት፣ሱቅ፣ መሥሪያ ቤት ይዘርፋሉ፤
፭ ሰው የሚኖርባቸው ቤቶችን ተራ በተራ፣ይዘርፋሉ፤
፮ የፍርድ ቤት፣ የመዘጋጃ ቤት፣ የትምህርት ቤት፣የጤና ሰነዶችን ሙሉ በሙሉ ያወድማሉ። [በእነዚህ ሰነዶች መውደም ምክንያት የሚመጣውን ቀውስ አስቡት።
፯ ከተማ ውስጥ ምሽግ ይሠራሉ። የመዋጊያ ቦታቸውን ከተማ መሃል ያደርጋሉ።
፰ የዘረፉትን ንብረት በሙሉ ወደትግራይ ይጭናሉ፤ ይልካሉ።t
፱ በየቤቱ ገብተው ከበሉ በኋላ በበሉበት ይጸዳዳሉ።
፲ የሞተባቸው፣የተገደለባቸው ሰው ካለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይቀብራሉ።
፩፩፤ በየቤቱ እየዞሩ ከሕጻናት እስከ አሮጊት ይደፍራሉ፤ ” እያሉ ዘርዝረውታል። ይህ ማለት እንግዲህ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ የተዘመተብንን ወረራ ከመካከልቻን ነጥረው በሚወጡ የጎበዝ አለቆቻችን እየተመራን እንደ ህዝብ መመከት ሲገባን እጅ እግሩን በሴራ የተተበተበን መንግስት ተስፋ ስናደርግ ወርቃማ ግዜያችንን እያባከንን እና ነጥብ እየጣልን በመሆኑ ከላይ የተዘረዘረውንና ሰው ቀርቶt የጭነት አህያ የማይችለውን ግፍ በጣም ከሚጠሉን እርጉማኖች እጅ ለመቀበል በፈቃዳችን የወሰንን መሆንችንን የተረዳነውtt አይመስልም። እዝራ ስቱኤል እንደጻፈው፤ ባንድ ወቅት  እስራኤላውያንም በአሕዛቦች እጅ በምርኮ ሳሉ የሆኑትን ሲገልጽ “ግናይቱ እንደጠፋ፣ ዘመራ ዘውዳችን እንደተወሰደ፣ ካህናቶቻችን እንደተጎተቱ፣ ሚስቶቻችን እንደተደፈሩ፣ ከምንም በላይ የህግ ማደሪያ ታቦታችን ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች አይቀርም” እያለ ቁጭቱን ወረቀት ላይ ሲያሰፍር ስለዛሬይቱ ኢትዮጵያ የሚናገር ይመስል ነበር።
Filed in: Amharic