>

 "ደሴ ወጥመድ ነበረች....!!!"   *(ፕሬዚዳንት  ኢሳያስ አፈወርቂ)

 “ደሴ ወጥመድ ነበረች….!!!”

 ፕሬዚዳንት  ኢሳያስ አፈወርቂ
ገዛህኝ ጸጋው

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሕወሓትን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ወያኔ ጣእረሞት ላይ ሆኖ እየተወራጨ ነው የመሞቻው ጊዜም በጣም እየቀረበ ነው ይላል። እየቀረበ ነው ስንል በጣም ከበዛ ሳምንታት ለማለት ነው። 
የኢትዮጵያ ጦር ከትግራይ መውጣቱ ና ከዛም ቀጥሎ በነበሩት ጊዜያት ወደ አማራ ና አፋር አንዳንድ ቦታዎች ገብቶ መቆጣጠሩን ያዩ ሰዎች የኢትዮጵያ ጦር በጣም እንደተዳከመ አድርገው ሲያወሩና ሲያስወሩ ነበር። ያ ግን ሆን ተብሎ የተሠራ ታክቲክ ነበር በዚህም ሰፊ ወታደራዊ  ፖለቲካዊ ና ዲፕሎማሲያዊ ትርፍ ተገኝቶበታል ይላል። ከግጭቱ ቀደም ብሎ ሕወሓት አስቦና አቅዶ ተራራማና ሸለቋማ በሆኑ ቦታዎች መሣርያ በስፋት አካማችቶ ነበር። በከፍተኛ ቁጥር የሰለጠኑ ወታደሮች ነበሩት ድንገት በከፈተውም ጥቃት በርካታ መሣርያ መያዝ ችሎ ነበር የኢትዮጵያ መከላከያንም ማዳከም ችሎ ነበር ይላል።
 ያ ሲቀለበስ ወደ ሌላ አዲስ ጨዋታ ገባ ይኸውም መሣሪያዎችን ገጠራማ ቦታዎች በመቅበር እና የሠው ሀይሉን በየቦታው በመበተን በአጭር ኪሳራ የኢትዮጵያን ሀይል እንደ ጨው በሟሟት አአ ን ድጋሚ መቆጣጠር ነበር። ስትራቴጂውን ሲያረቅ የክረምት ወራት ውስጥ ያሉ እንደ ጭቃ ጉም ዝናብ ከትግራይ ገደላማና ተራራማ ገጠሮች ጋር በሚፈጥሩት ህብር የምድር ጦር ከባባድ ተሽከርካሪዎችና የአየር ሀይል ክፍሎች ለሚያደርጉት ፀረ ሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ እንቅፋት መሆን፤ የደጀኑ ወቅታዊ የሞቀ ድጋፍ ከአሜሪካ አውሮፓ ከባድ ጫና ጋር በማቀናጀት ነበር ብሎዋል።
ሆኖም የኢትዮጵያ መሪዎች ሁኔታውን አንብበው ጦራቸውን አራቁ በዚህ ከዲፕሎማሲያዊ ና ፖለቲካዊ ትርፍ ውጭ ጦራቸው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ ቀነሱ። ጊዜ አግኝተው  የወደፊት አላማዎችን ጭምር ታሳቢ ያደረገ ከባድ ጦር እየገነቡ ነው። በተጨማሪም የሕወሓትን ሀይል እስከ ደሴ የተዘረጋ ወጥመድ ሰርተው ሰፊ ቀጠና ውስጥ በመለጠጥ የሰለጠነ ሠው ሀይሉ ላይ ሊገመት የማይችልና ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊ ኪሳራ እያደረሱበት ነው አለኝ የሚለውን ከባድ መሣርያውንም በሙሉ እያስተፉት ነው ብሎዋል።
ተከቦና ታጥሮ ያለው ሕወሓት ከአጭር ጊዜ የውጊያ ጫና ውጪ የሠው ሀይሉን እያሰለጠነ መተካት ቢችል እንኳ ለረጅም ጊዜ ጦርነት ወሳኝ የሚባሉ እንደ ነዳጅ የመሣርያ መለዋወጫዎች ና ተተኳሽ ነገሮችን ለመተካት የሚችልበት አማራጭ የለውም። ያ ማለት በሜካናይዝድ ና በብርጌድ Conventional ውጊያ መዋጋት የሚችሉባቸው ጊዜያት እየተሟጠጡ ነው ስለሆነም የኢትዮጵያ ጦር በሳምንታት ውስጥ አካሄዶችን ቀልብሶ መቀሌ ይገባል ያልኩት በርካታ ነገሮች ታሳቢ በማድረግ ነው ብሎዋል።
የኢትዮጵያ ጦር ቀጣይ መቀሌ ሲገባ እንደበፊቱ በየተራራውና ገደላገደሉ በከፍተኛ ደረጃ መሣርያ ያከማቸ ብዛት ያለው የሠለጠነ ሀይል በየቦታው የበተነ ከባድ ሀይል እንደማይገጥመው ከዛ ይልቅ ብዙም ልምድና ስልጠና የሌለው ሞራሉ የደቀቀ ከከባባድ መሣርያ ይልቅ የነፍስ ወከፍ አነስተኛ መሣርያ የያዘ ተስፋ ያጣ ሀይል ነው ሚጠብቀው ያንን ደግሞ በቀላሉ ማበጠር የሚቻል ነገር ነው
ብሎዋል።
 ሕወሓት የመቀጠል ተስፋ አለው ወይ ተብሎ ለተጠየቀው ሲመልስ ያንን በ 3 ከፍለን ማየት እንችላለን ይላል። 1. ሕወሓት በውጊያ አሸንፎ አአ ይጠጋል ብንል እንኳ የኤርትራ ሰራዊት እንደለመደው በቀናት ውስጥ መቀሌ ይገባና ያ ሁሉ ልፋቱ ይቀለበሳል ያንን እነሱም ያውቁታል። 2. ጦርነቱ ባልተፈለገ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ ይቀጥልና ህዝቡ ተሰላችቶ ኢትዮጵያ ሳትፈልግ ሕወሓት ጋር የሠላም ውል ትፈራረማለች። 3.ሕወሓት ሁኔታዎች እንሚያመለክቱት በአጭር ጊዜ ተሸንፎ ይጠፋል ነው። በሁሉም መስፈርት ስትገመግም የሚሆነው 3ኛው አማራጭ ብቻ ነው ብዬ በእርግጠኝነት ልነግርህ እችላለሁ በማለት የሕወሓት ጉዳይ ከንግዲህ የአጭር ጊዜ ጉዳይ መሆኑን አብራርቶዋል
ምንጭ Eastafro.com
Filed in: Amharic