>
5:01 pm - Sunday December 2, 1190

በአማራውላይ የተከፈተው ሁለተኛው የወረራ ግንባር..!!! (ወንድወሰን ተክሉ)

በአማራውላይ የተከፈተው ሁለተኛው የወረራ ግንባር..!!!
ወንድወሰን ተክሉ
የሰንዳፋው ሸኔ ድርጊት ሳይስፋፋ፦

ከደሴ-ኮምቦልቻ ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙ ወገኖቻችን የሰንዳፋ እና አከባቢው ፀጥታ ሃይሎች የሚያደርሱት በደል ከሚታሰበው በላይ መልከ ብዙ ነው፥
1) አንዳንዶቹ በደፈናው አትገቡም ተመለሱ ብለው ተጓዥ መንገዶኞችን መልሰው ያባርራሉ
2) ሌሎቹ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡትን መኪኖች እና ተሳፋሪዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ለሰዓታት ያንገላታሉ፣ እስር ቤት ያሳድራሉ
3) አንዳንዶቹ ደግሞ “አማ” የሚል ታርጋ ያላቸው መኪኖች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ አንፈልግም የሚሉም ናቸው።
በኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለፉት ሶስት አመታት ወሎየው  የተበደለውን ያክል የትም በማንም አልበደለም። ጁንታው ከራያ-ደቡብ ወሎ መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣቸው እናቶች እና ህፃናት ሀገር አለኝ ብለው ወደ አዲስ አበባ ርቀው ቢሄዱ የትህነጉ ሌላው ክንፍ የሆነው  በብልፅግና ስም የሚንቀሳቀሰው ገዳይ ሃዩ የኦነግ ሼኔ ቡድን አይኑ ደም በመልበሱ ወገኖቻችን ላይ የጭካኔ ዱላውን እያሳረፈ ይገኛል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
የአማራ እና ኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ባለስልጣናት ለአይኑ የጠላችሁን ህዝብ ድጋሚ ለጆሮውም እንድትቀፉት የሚያደርግ በደል ሲፈፀምበት ቆማችሁ አትዩት!!
የወሎ ድምፅ  Voice Of Wollo
Filed in: Amharic