ግርማካሳ
*…. መንግስት ሕዝብን ዜጎችን የመጠበቅ ስራዉን ቢሰራ ኖሮ፣ ፋኖ ሚሊሺያ ወዘተ ባላስፈለገ ነበር.. !
የሕወሃት ጦር በሁሉም መስፈርት የወታደራዊ አቅም የበላይነት አለው፡፡ ከ350 ሺህ በላይ ለሶስት አመት የሰለጠነ ስራዊት አለው፡፡ ከአስር ሺህ በላይ ሜካናዝድ ስልጠና የወስዱ ከባባድ መሳሪያዎች የሚተኩሱ አሉት፡፡ የመሳሪያ፣ የትጥቅ። የጥይት ችግር የለበትም፡፡ አጭር ጊዜ ስልጠና የሰጣቸው፣ ለዘረፋ የሚያሰማራቸው ደግሞ ሌሎች በመቶ ሺሆች አዘጋጅቷል፡፡
አሁን አለ የሚባለው፣ እነ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የሚመሩት፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶር አብይ አህመድ የሚይዙት የፌዴራል መንግስት የመከላከያ ጦር፣ ይሄ የወያኔን ጦር መቋቋም አይችልም ነበር፡፡ ወያኔዎች አራት ኪሎ በቀላሉ ይገቡ ነበር፡፡ እንደሚዝቱትም እነ ዶር አብይ አህመድ ይዘው ለፍርድ ያቀርቡ ነበር፡፡ ወያኔዎች ይሄንን ስለሚያውቁም ነው ፣ “ብዙ ጊዜ አይወስድብንም” ብለው ጦርነት የከፈቱት፡፡
ወያኔዎች አንድ የሰሩት እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት አለ፡፡ ትልቅ miscalculation !!!!!! እርሱም ሕዝቡን መናቃቸውና መርሳታቸው ነው፡፡ የጎንደር፣ የአፋር፣ የወሎ ሕዝብ በሚሊሺያ፣ በፋኖ ተደራጅቶ የራስ ምታት ነው የሆነባቸው፡፡ በራሱ ወያኔን መቋቋም የማይችለው የመከላከያ ሰራዊትም በሕዝባዊ ሰራዊትና ሚሊሺያ ሲደገፍ አቅም እንዲያገኝ ነው ያደረጉት፡፡
አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ፡፡ወያኔ በምእራብ ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር ድንባር ላይ፣ ከጨጨሆ መድሃኔዓለም የምትገኘዋን እጅግ በጣም አደገኛና ስትራቲጂክ የሆነችውዋን ደብረ ዘቢጥ አላነቃንቅ ብሎ ነበር፡፡ መጀመሪያ አየር ኃይል ድብደባ አደረገ፡፡ አካባቢው ለአየር ድብደባ ብዙ ስለማይመች፣ ወያኔዎቹ ፍንክች ሊሉ አልቻሉም፡፡ በኋላ የወገን ጦር በሶስት አቅጣጫ ወደ ደብረ ዘቢጥ አመራ፡፡ በስተቀኝ ፋኖ ስምሪት ወሰደ፡፡ በስተ ግራ የአማራ ልዩ ኃይል፤ በመሃል ደግሞ የመከላእክያ ሰራዊት፡፡ በሶስት አቅጣጫ ሲመጣባት ወያኔ አልቻለችም፡፡
ወያኔ ደባርቅና ዳባት ልትይዝ ነበር፡፡ ወያኔ ደብረ ታቦር ጫፍ ደርሳ ነበር፡፡ ደባቅር፣ ዳባት፣ ደብረ ታቦር ቢያዙ ኖሮ ጎንደርንና ባህር ዳርን በቀላሉ ገቢ ታደርግ ነበር፡፡ ወያኔን ደባቅርቅ፣ ዳባት፣ ደብረ ታቦር እንዳትገባ ማን ነው ያስቆማት ? አሁንም ወያኔ ያለ የሌለ ኃይሏን አሰማርታ ወደ ደሴና ኮምቦልቻ እየገስገሰች ነው፡፡ ብዙ ሞከረች፡፡ እስካሁን አልቻለም፡፡ ለምን ? ማን ነው ያስቆማት ????
በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው አራት ኪሎ ያሉ፣ እነርሱ በወያኔ እንዳይያዙ፣ ወያኔንን መክቶ ለያዘላቸው ኃይል ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኛ አለመሆናቸው ነው፡፡ ፋኖ የአማራ ሚሊሺያዎች ከወያኔ ጋር በሚያደርጉት ትንቅንቅ አራት ኪሎ አስፈላጊውን ትጥቅ እንዲያገኙ አላደረገም፡፡
አቶ ብናልፍ አንዱ አለም በገጹ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ የሆነ ታጣቂ አንቀበልም እያሉን ነው፡፡ የመንግስትን ሚና ለመተካት የሚደረግ ሙከራ ነው በሚል፡፡ ይሄን ሲሉ እኮ መንግስት ስራው እየሰራ ያለ ይመስል ነው !!!!
መንግስት ሕዝብን ዜጎችን የመጠበቅ ስራዉን ቢሰራ ኖሮ፣ ፋኖ ሚሊሺያ ወዘተ ባላስፈለገ ነበር፡፡
አንደኛ ደረጃ መንግስት ሚናዉን ስራዉን በብዙ ቦታ ስላልተወጣ መሰለኝ ዜጎች በራሳቸው አነሳሽነት ተደራጅታቸው ራሳቸውን ለመከላከል እየተንቀሳቀሱ ያሉት፡፡ እነ አቶ ብናልፍ ራሱን ለመከላከል እየተደራጀ ያለው ወገን ላይ “ጀግና ለመሆን” ከሚሞክሩ፣ ወያኔና ኦነጎች ላይ ጀግና ለመሆን ቢሞክሩ፣ እንደ መንግስት ስራቸውን ቢሰሩ የተሻለ ነበር የሚሆነው፡፡
በቆቦ፣ በራያ፣ በወልዲያ በላሊበላ፣ በዋገመራ ህዝቡ በራሱ ተደራጅቶ የሽምቅ ውጊያ እያደረገ ነው፡፡ መንግስት በነዚህ ቦታዎች የለም፡፡ ታዲያ እንዴት ነው በመንግስት ቁጥጥር ስር ሊሆኑ የሚችሉት ?????
መንግስት ሕዝብን ዜጎችን የመጠበቅ ስራዉን ቢሰራ ኖሮ፣ ፋኖ ሚሊሺያ ወዘተ ባላስፈለገ ነበር፡፡
አንዳንዴ የሕዝቡን ትልቅ መነሳሳት አይቼ ልቢኡእ በተስፋ ሲሞላ፣ እንደ አቶ ብናልፍ ያሉትን ያኔ የሕወሃት አሁን የኦህዴድ ተላላኪ የሆኑትን አይና ደግሞ ተስፋዬ ወደ ታች ይወርዳል፡፡