>

በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ተከልክሎ የነበረው የአቶ ስንታየሁ ቸኮል ህክምና በፍርድ ቤት ተፈቀደ  (ባልደራስ)

በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ተከልክሎ የነበረው የአቶ ስንታየሁ ቸኮል ህክምና በፍርድ ቤት ተፈቀደ 
ባልደራስ

በወህኒ ቤቱ ሓላፊ ኮማንደር ጫላ ፀጋ ተከልክሎ የነበረው የኅሊና እስረኛው የአቶ ስንታየሁ ቸኮል የግል ህክምና ዛሬ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ውድቅ ተደርጓል።
አቶ ስንታየሁ  ሲጠይቁ የነበረው የህክምና ጥያቄ ከወራት እንግልት በኋላ ነው የተፈቀደው። ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንፃር የሰዎችን ሰብዓዊ መብት የመጠበቅ ግዴታ መርሆዎችን በመጥቀስ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በግላቸው ህክምና የማግኘት እና  ሙሉ ጤንነታቸውን የመከታተል መብት ሊጠበቅላቸው እንደሚገባ አብራርቶ ፍርድ ቤቱ  ህክምናውን በመረጡት ተቋም እንዲያገኙ አዝዟል።
በመሆኑም በቅርቡ በፖሊስ ታጅበው እንደሚታከሙ ይጠበቃል።
Filed in: Amharic