>

እርጉም መቃብር! (ዘምሳሌ)

እርጉም መቃብር!

ዘምሳሌ


አኖሌም ይፍረስ
የመለስ  ክፉ ስራ እና መቃብርም  ይደምደስ

እርጉም መቃብር

የኢትዮጵያውያን ቅርቃር
የሰብአዊነትም  ፀር  የዘር ፍጅት አድባር
የሀበሾች  ምራዥ ዘር

የሳጥናኤል አካል  የክፋት ዛፍ ቅጠል
የእናት ሀገር ደባል  ጡት ነካሽ ራስ ጠል

በጠላሀት ሀገር በገፉኸው እምነት በር
በረገጥከው ምድር  ባቆሙልህ ቀብር
ሄደህ ስትደመር  ሲውጥህ ያ አፈር

የምላስህ ምራዥ  ሆኖ አዛዥ ናዛዥ
የንፁሐን ገናዥ  የተገፉት በዝባዥ
የሀገር ቁስል ዕዥ  የምናብ ጦር አዛዥ

ባካልህ ብስባሽ  ምድሪቱንም አርካሽ
ሀገር መሬት አፍራሽ  የንፁሐን ደም ላሽ
የነበርክ ተከሳሽ
መርዝህን በትነህ  አኖሌን ገትረህ
ሀገርን አባልተህ
በቁም ክህደት ኖረህ ከመቃብር ወርደህ
መንፈስህን ልከኽ  ኢትዮጵያን ጎድተህ
በምስጥም ተበልተህ

በስምህ ሕግ  ታሞ  መሪም ያን ተሳልሞ
በአንተው እግር ቆሞ  የለውጥ ፅዋ ስሞ
በምክር ቤት ልሞ  ለኪዳንህ ቆሞ

የተንኮልህ ፍሬ  አርጎ ብሔር አውሬ
በጎጥ ልጅ መንደሬ  ሲታመስ በወሬ
ሳይለወጥ ዛሬ

የኢትዮጵያን ተስፋ  በመርዝህ ሲገፋ
ደጎቿን ሲያስጠፋ  ባንተው ሀይል ሲደፋ
ባመጣኸው ዳፋ  ወገንም  ሲጠፋ

እድሉን አግኝተኽ  በክብር ተቀብረኽ
ከመሬቷ ጠልቀኽ  በመንፈስህ ቆመኽ
ሕዝብን እያባላኽ  ከሙታንም  ገነህ

እስካለህ ጠበቃ  ባንተው የሚመካ
በኢትዮጵያችን ጫንቃ  ሳትጠልቅ ጨረቃ
ህዝቧን እያስጠቃ ለመምራት ሳይበቃ

አንተ ጉድጓድ  ኖረኽ   በአድናቂህ ታጅበኽ
በፈጠርከው ሕግህ ሀገር ትመራለኽ
ከገባኸው መሬት  አውጥተው እስኪጥሉኽ

መለስ ብለው ነቅተው  ከእንቅልፍም ድነው
ከጥፋት ታቅበው  ጉርጓድኽን ምሰው
ሕግና አካልኽን  ቅሬት በድንህን
ሀውልቱን ፈንቅለው  ጠያፍ ገፅታህን
እርኩስ ተፈጥሮህን

ከሀገር አጥፍተው  ስሬትክን አቃጥለው
ባሕር ችላ ባልከው  አመድክን በትነው
ምግባርህን ሽረው  ኢትዮጵያን ገንብተው
በነፃነት ፅንተው  ህግህንም ሽረው
ለህዝብ ለሀገር ሚጠቅም ህገደምብ አፅድቀው

ያንተንም መቃብር  ካረፈባት አፈር
ከጠላኸው ምድር ገፁን በመሰወር
ሕዝቡን ከሚያሳርር
ከዚያ ይነቀላል  ሕግ ለኢትዮጵያ ሲኖር
ያ እርጉም  መቃብር  መለስ ሚሉት ቀብር
የኢትዮጵያዊነት ፀር!

Filed in: Amharic