>
5:21 pm - Sunday July 20, 9681

"ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር በአካል ተገናኝተን ግምባር ፈጥረናል...!!!" ሕወሓት) ቃል አቃባይ (ጌታቸው ረዳ ) D.W

“ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር በአካል ተገናኝተን ግምባር ፈጥረናል…!!!”
ሕወሓት) ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ 
D.W

የትግራይ ኃይሎች መንግሥት ኦነገ ሸኔ ከሚለው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር በአካል መገናኘታቸውን የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። ሁለቱ ኃይሎች በቅንጅት ወደ መዲናይቱ የሚያደርጉትን ጉዞ እንደሚገፉበትም ዐስታውቀዋል።
ጌታቸው ረዳ አያይዘው «ከኦነግ/የኦሮሞ ነጻነት ጦር [OLF/OLA] ጋር ግንባር ፈጥረናል። ትግራይ ውስጥ ያሉንን ዓላማዎች ለማሳካት አዲስ አበባ መሄድ የሚጠይቅ ከሆነ፤ ወደ አዲስ አበባ እንሄዳለን። ነገር ግን አሁን ወደ አዲስ አበባ እያመራን ነው ማለታችን አይደለም» ብለዋል። የሁለቱ ኃይሎች ጥምረትን በተመለከተ ከሕወሓት ኃይሎች የተሰጠውን አስተያየት ውግያ እየተካሄደ ባለባቸው አካባቢዎች የስልክ እና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች በመቋረጣቸው ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጫ ማግኘት አለመቻሉን የዜና ምንጩ ገልጧል። የኢትዮጵያ መንግስት የኮሙኒኬሽን አገልግሎትም ሆነ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን በጉዳዩ ላይ ወዲያው የሰጡት አስተያየት አለመኖሩንም የዜና ምንጩ አክሎ ጠቅሷል። በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጦር መሣርያ ያለው የከተማዋ ነዋሪ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ አቅርቧል። መግለጫውን ተከትሎ ጥፋት ለመፈጸም የሚፈልግ ሰው ካለ በቁጥጥር ስር እንደሚውል የከተማው አስተዳደር ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። በጉዳዩ ላይ በዝርዝር የተባለነገር ግን የለም። የከተማ አስተዳደሩ ስላቀረበው ጥሪ ከወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ምን ትላላችሁ? አስተያየታችሁን አጋሩን።
Filed in: Amharic