>

ኦነግ ለህዉሃት ያለዉ ናፍቆት ፤  ህዉሃት ስለ ኦሮሞ ህዝብ ያለዉ የተዛባ አመለካከት...?!? ( ሸንቁጥ አየለ)

ኦነግ ለህዉሃት ያለዉ ናፍቆት ፤  ህዉሃት ስለ ኦሮሞ ህዝብ ያለዉ የተዛባ አመለካከት…?!?
————
ሸንቁጥ አየለ

*…. ኦነጋዉያን  በምን ስሌት አስልተዉት ይሆን ወያኔ ከአቢይ አህመድ ይልቅ ለኦሮሞ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ የሚመስላቸዉ?
 
ለጊዜዉ ኦነግ ለህዉሃት ያለዉ ናፍቆት እንዲሁም ህዉሃት ስለ ኦሮሞ ህዝብ ያለዉ የተዛባ የፖለቲካ ትንታኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ የማይገቡን እና ግራ የሚያጋቡን እንቆቅልሽ ናቸዉ::
1ኛ.የኦሮሞን ህዝብ እጅና እግር ይዘዉ እንደገና ለወያኔ ባርነት ለማስረከብ የሚተጉት የኦነጋዉያን አክራሪ ሀይሎች የፖለቲካ ቀመር ጉዳይ ሁሌም  እንቆቅልሽ ነዉ::ኦነጋዉያን  በምን ስሌት አስልተዉት ይሆን ወያኔ ከአቢይ አህመድ ይልቅ ለኦሮሞ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ የሚመስላቸዉ?
አቢይ አህመድ እንደሚታወቀዉ በጣም ዘረኛ ከመሆኑ የተነሳ “ኦሮሞን ኦሮሞ ከሚገለዉ ብለን ኦነግ ወንጀል ሲሰራ ዝም አልነዉ” የሚል አጠቃላይ አክራሪ የኦነግ/ሸኔን ሀይል ያቀበጠ:ፍርድ እና ፍትህ የማያዉቅ:ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን በነገዳቸዉ/በሀይማኖታቸዉ ሲጨፈጨፉ ከኦሮሞ ዉጭ ያሉ ብሄረሰቦች እስከሆኑ ድረስ ግድም የማይሰጠዉ ገና ለአቅመ መሪነት ቀርቶ ለአቅመ ተላላኪነት ያልደርሰ ሰዉ ነዉ::ይሄ ሰዉ ግን አንድ የማይታማበት በኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን ፍልስፍና እየተመራ ከኮንዶሚኒዬም ቤቶች ጀምሮ እስከ ሰፈራ ጣቢያዎች ከስልጣን እስከ ቢዝነስ ጉዳዮች ሁሉ አይኑን ጨፍኖ ለራሱ ነገድ ቅድሚያ የሚሰጥ ሰዉ መሆኑ ነዉ::ሌላዉ ቀርቶ በኦነጋዉያን/ሸኔዎች ላይ ጠንከር ያለ መግለጫ ለማዉጣት ልቡ የሚንሰፈሰፍ ፍትህ ምን እንደሆነ:ስልጣን ምን እንደሆነ ገና ያልተረዳ ሰዉ ነዉ::ሀገር እንዴት ይመራል? ብዙሃን ኢትዮጵያዉያን ሁሉ እንዴት እኩል ፍትህ ሊያገኙ ይገባል የሚለዉን ጥያቄ ለአንድም ቀን በቃላት እንጂ በልቡ አንሰላስሎ የማያዉቅ ሰዉ ነዉ::
እናም ኦነጋዉያን አቢይ በአንቀልባ አዝሎ እሽሩሩ ከሚላቸዉ ይልቅ ወያኔ በጥይት ግንባር ግንባራቸዉን እያለች የምትገዛቸዉ የባርነት ስርዓት እንዴት ሊናፍቃቸዉ ቻለ? አቢይ እንዲህ የዘር ማጥፋት እያከናወኑ እያቀማጠላቸዉ ሳለ እንዴት ወያኔ ሰልፍ አደረጋችሁ ብላ በጥይት የምትደበድባቸዉ ስርዓት ሊናፍቃቸዉ ቻለ:?ፈጽሞ እንቆቅልሽ ነዉ::
2ኛዉ እንቆቅልሽ ደግሞ ወያኔዎች ስለ ኦሮሞ ህዝብ ያላቸዉ የንቀት እና የእብሪት ስሌት ነዉ::ወያኔዎች በመጀመሪያዉ ማኒፌስቷቸዉ አማራን ማጥፋት አለብን ብለዉ በ1967 ሲወያዩ ስለ ኦሮሞ ህዝብ የሚከተለዉን ትንታኔ አስቀምጠዉ ነበር::”ነፍጠኛዉን ከሰበርነዉ ኦሮሞዉን እንዳሰኘን እናደርገዋለን::በምንፈልገዉ መልክ እንሰራዋለን” ሲሉ ሰፊ የንቀት ትንታኔዎች ብሎም እኔ እዚህ ለመጻፍ የሚቀፉኝ ብዙ መጽሃፎችን አዘጋጅተዉ እና ፕሮፖጋንዳዎችን  አከናዉነዋል::
ወያኔዎች አሁኑ በቅርቡ እንኳን የኦሮሞ ህዝብ ያሳዬዉን የጀግንነት ተጋድሎ እና ከአማራ ጋር ተባብሮ ከስልጣን እንዳባረራቸዉ እያወቁም አሁንም የንቀት ትንታኔአቸዉን ቀጥለዋል::”ኦሮሞው አያስቸግረንም::የአማራ ክልልን ካለፍን ቤተመንግስቱን በአንድ ቀን እንቆጣጠረዋለን” እያሉ እየጻፉ ነዉ::
ሆኖም የኦሮሞ ህዝብ እጅግ ብዙ እና ትልቅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በዉስጡም እጅግ የመጠቁ ምሁራንን :በርካታ ለኢትዮጵያዊነት የታመኑ ጀግኖችን የያዘ ህዝብ መሆኑን ወያኔዎች ለቅጽበት አያስተዉሉም::ምናልባት ይሄ የተዛባ የንቀት ግንዛቤአቸዉ ከኦነጋዉያን ጋር በሚሰሩበት ወቅት ኦነጎቹ የሚያሳዩዋቸዉ ልክስክስ ስነ ልቦና ሊሆን ይችላል የሀገሪቱን ሰፊ ብሄር እንዲህ ለመናቅ ያስደፈራቸዉ::ወያኔ ታላቅ ፈተና ወደፊት የሚገጥማት ከሰፊዉ የኦሮሞ ህዝብ ጭምር ነዉ:: ወያኔዎች እንደሚሉት የኦሮሞን ህዝብ እንዳሰኛቸዉ ማድረግ ከቶም አይችሉም::
ለማንኛዉም ወያኔም ስለ ኦሮሞ ህዝብ ባለዉ የተዛባ ግንዛቤ ድጋሚ የጁን ያገኛል::ኦነጋዉያንም ስለ ወያኔ ባላቸዉ ፍቅር የተነሳ የናፈቁትን የባርነት ናፍቆት ከወያኔ መንደር በሆነ መልክ ይደርሳቸዉ ይሆናል::
ለዚህ ማሳያዉ ሴት እና ህጻናት በማረድ የሚታወቀዉን የኦነግ ሰራዊት የወያኔ ሀይል በግዳጅ ከፊት አሰልፎ ከጀርባዉ ሞርታር ደግኖበት ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር እንዲሁም ከኦህዴድ ልዩ ሀይል ጋር በግዳጅ እንዲዋጋ ያደርገዋል::ኦነግ እንግዲህ ቢያንስ የፈለገዉን የባርነት ናፍቆት ከወንድሞቹ ጋር በወያኔ አስገዳጅነት በመዋጋት ያገኛል::ኦነግ በተለይም ከኦህዴድ ልዩ ሀይል ጋር በሚዋጋበት ጊዜ የበርካታ ወንድሞቹን ደም ለህዉሃት ሲል ያፈሳል ማለት ነዉ::ህዉሃትም አንዴ ኦነግ ቀንበሯ ዉስጥ ከገባላት ብኋላ አስገድዳ የኦህደድን ልዩ ሀይል ማለትም የራሱን ኦሮሞ ወንድሞች እንዲጨፈጭፍ ታደርገዋለች::
ለማንኛዉም ኦነግ ከጥቂት ጊዜ ብኋላ በመላዉ የኦሮሞ ህዝብ አክ እንትፍ ተብሎ የሚተፋ ሀይል ነዉ::የኦሮሞን ህዝብ መልሶ እጅና እግሩን ይዞ ለባርነት በህዉሃት እንዲመራ እየሰራ ያለ የባርነት ስነልቦና ተሸካሚ መሆኑን ህዝቡ በደንብ እያስተዋለዉ::ትልቁን የኦሮሞ ህዝብ እወክላለሁ ብሎ የተነሳዉ ኦነግ ለኢትዮጵያዉያን ወንድማማችነት:አንድነት:እኩልነት እና ፍትህ ከመስራት ይልቅ እየተከተለዉ ያለዉ የሌሎች ነገዶችን ዘር የማጥፋት የሰይጣን መንገድ እራሱን አንቆ ይበላዋል::
በአጠቃላይ ኦነግም ህዉሃትም ከምድሪቱ ጠፊ ናቸዉ::ኢትዮጵያ ታብባለች::የኦሮሞ ህዝብ:የትግሬ ህዝብ: የአማራ ህዝብ የሚለዉ የዘረኝነት በሽታም ከምድሪቱ ይነቀላል::የጎሳ ፖለቲካ በአዋጅ ይሻራል::ይሄ የማይቀር ሀቅ ነዉ::ኢትዮጵያዉያንንም ኢትዮጵያ የተባለች ሀገራቸዉን እንደገና በፍቅር በጋራ የሚኖሩባት ይሆናል::
ለጊዜዉ ግን ኦነግ ለህዉሃት ያለዉ ናፍቆት እንዲሁም ህዉሃት ስለ ኦሮሞ ህዝብ ያለዉ የተዛባ የፖለቲካ ትንታኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ የማይገቡን እና ግራ የሚያጋቡን እንቆቅልሽ ሆነው አሉ::
Filed in: Amharic