>
5:21 pm - Sunday July 21, 0639

የቡሽንና የባራክን የአዞ እንባና ስላቅ ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ላይ አይደግመውም!  [መስፍን ማሞ ተሰማ]

የቡሽንና የባራክን የአዞ እንባና ስላቅ ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ላይ አይደግመውም!

መስፍን ማሞ ተሰማ


የአምባ ገነኗና ጣልቃ ገቧ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ጁነየር ጥንተ ጥንታዊት የኤፍራጥስና ጢግሮስ የሜሶፖታሚያ ሥልጣኔ ምንጭ ኢራቅን ከአባሪዎቹ የምዕራብ ግብዛን ሀገሮች ጋር ተባብሮ  ሉዓላዊነቷን የግዛት አንድነቷንና የሕዝቧን በሠላም መኖር ከደረመሱና ከበታተኗት በሗላ ሥልጣኑን ሲለቅ  “ኢራቅን መበተን በሥልጣን ዘመኔ የሰራሁት ስህተት ነው” ሲል ዘግናኝ ስላቅ ተሳልቋል።
“ምላሱ ጤፍ ይቆላል” የሚባለው ሌላው ግፈኛ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ደግሞ በነፃነት ተምሳሌነት የምትታወቀውን ሊቢያ እንዳልነበረች አድርጎ ካፈራረሳትና ሕዝቦቿን ስደተኛና ሀገር አልባ ካደረገ በሗላ ከሥልጣኑ ሲለቅ “ሊቢያን ማፍረስ አልነበረብኝም” ሲል ሌላ ዘግናኝ ስላቅ ተሳልቋል።
እነሆ በግፍና ማስረጃ አልባ ውንጀላዎቸ ኢራቅ ፈርሳለች፣ ሊቢያም ፈርሳለች፣ የሌሎቹን ባናነሳ እንኳን። ማን አለብኝ ባይና በዓለም ፖሊስነት በተለይም በአዳጊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ራሷን አድራጊ ፈጣሪ አድርጋ የሾመችው አሜሪካ ጭፍሮቿን ሆ! እያስባለች ኢራቅና ሊቢያን በጣልቃ ገብነት በወታደራዊ ዘመቻ ከማፈራረሷ በፊት ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ፋብሪኬትድ ክስና ውንጀላ እንደምታቀርበውና አጋሮቿም  እንደሚያስተጋቡት ያኔም በቅጥፈት የተሞላ ድራማ (Weapons of Mass Destruction – WMD) በሚል ካባ በሉዓላዊ ሀገራትና ሕዝቦች ላይ ወንጀል ፈፅመዋል።
በጆ በይደን ዘመን ደግሞ የእኒህ ወራሪና ግፈኞች ጭዳ ኢትዮጵያ ትሆን ዘንድ ተመርጣለች። ለአስራ አንደኛ ጊዜ በራሳችሁ ጥሪ በራሳችሁ ሸንጎ ኢትዮጵያን ከሳችሗል። ለአስራ አንደኛ ጊዜ ለወራሪዎችና ለመርዝ ጋዝ መሣሪያዎቻቸው ያልተንበረከክነው የአባትና የአያቶቻችን ልጆች የሆንነው የዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ዘብ ኩሩና ጀግኖች ተወካያችን ታዬ አፅቀ ሥላሴ በርጋታ፣ በግርማ ሞገሥናነ በልዕለ መተማመን (Ultimate Confidence) ኢትዮጰያ የተተበተበባትን የመሰሪዎች፣ ግፈኞችና ጣልቃ ገቦች ድር በጣጥሳ በድል አድራጊነት እንደምትወጣ በጥንተ ጥንታዊት ሀገር የምንኖረውን አንድ መቶ ሚሊዮን ሕዝብና እናታችንን ኢትዮጵያ ወክሎ በአዳራሻችሁ ውስጥ ሲያውጅ የተሰማንን ተፈጥሯዊ ኩራትና ሀገር ፍቅር ኢትዮጵያዊ ስላልሆናችሁ አታውቁትምና አንገልፅላችሁም። ነገር ግን ያለ ሚሊ ሰከንድ ጥርጣሪ የምናስተጋባው ሀቅ ኢትዮጵያን አንድ ኢትዮጵያዊ በህይወት እስካለ/እስካለች ድረስ ማፍረስ መቼም ከቶም እንደማትችሉ ነው!!!
ጆ ባይደን ሆይ!! ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እንደ ጣልቃ ገብ ዕብሪተኛ ጓደኞችህ ቡሽና ኦባማ ትሳለቅባትም ሆነ  የአዞ እንባ ታነባ ዘንድ እድሉን ከቶም የማታገኝ መሆኑን ታውቀው ዘንድ በአስተርጓሚም ቢሆን መስማት ከቻልክ ስማ!!! አልሰማም ከልክም ፈራጁ ታሪክና ፈጣሪ  ናቸውና ከታሪክ ተምረህ ከፈጣሪህም ታርቀህ በእኩይ ዓላማ ለእኩያን ኢሰብዓዊ ወንጀለኞች ፈረስ ከመሆን ትታቀብ ዘንድ ምክራችን ይድረስህ!!! ኢትዮጵያ ያንተ ኢራቅ ወይ ሊቢያ መቼም ቢሆን አትሆንም!!!
ድል ለኢትዮጵያ!!!
ክብርና ሞገስ ለአምባሳደራችን ታዬ አፅቀሥላሴ!!!
ዘለዓለማዊ ሞት ለትህነግና ለባንዳ!!!
Filed in: Amharic