>

የአማራ ህልውና ዘመች በቀንደኛ ጠላቱ ብአዴን ብልጽግና ላይ ይቀጣጠል!!!! (ወንድወሰን ተክሉ)

የአማራ ህልውና ዘመች በቀንደኛ ጠላቱ ብአዴን ብልጽግና ላይ ይቀጣጠል!!!!
NOMORE_ብአዴን
 ወንድወሰን ተክሉ

፠ አማራ ሕልውናውን ለማስቀጠል….
የአማራ ሕዝብ እንደ ህዝብ የመኖርና ያለመኖር ግልጽና ግጥጥ ፍጥጥ ብሎ የመጣ አደጋ ተደቅኖበታል። የአደጋው ምንጭና ህልውናውን የሚፈታተነው ጠላት ብዙዎች እንደሚያስቡት ወራሪው ወያኔ ይመስላቸው ይሆናል። ግን እውነታው የአማራ የህልውናው ትልቁ ጠላት ብአዴን/ብልጽግና ነው።
አማራውም ህልውናውን ለማስጠበቅ የቅድሚያ ቅድሚያ ዘመቻውን ከፍቶ ማጧጧፍ ያለበት በብአዴን/ብልጽግና ላይ ነው። ለምን?? ለሚለው በአጭሩ ለማስቀመጥ አማራው ከትህነግና ኦነግ አቅጣጫ የተሰነዘረበትን የህልውና ጥቃትን ለመመከት መጀመሪያ ከቁጥር 2 ወያኔና ኦነግ በመሆን የለየለት የአማራ ጠላት በሆነው ብአዴን/ብልጽግና ላይ ዘምቶ ነጻነቱን መጎናጸፍ ግዴታ አለበት።
፨ ለማሸነፍ – በጠላት እጅ አለመመራት
፨ ለማሸነፍ – ከውጣዊ ጠላት እጀ ነጻ መውጣት
፨ ለማሸነፍ – እራሱን በራሱ የሚመራ መሆን ይጠበቅበታል።
                    ፨፨፨፨      ፨፨፨፨
፠ የአማራ ምርጫ የህልውናው ምርጫ ነው!
፨ አማራ እንደ ሕዝብ ህልውናዬን አስቀጥላለሁ ብሎ ካመነ የህልውና ጦርነቱን የቅድሚያ ቅድሚያ እንደካንሰር በተጣበቀበት ብአዴን ብልጽግና ላይ በማድረግ ከስርመሰረቱ ነቃቅሎ ካልጣለና እራሱን በራሱ የሚመራበትን አማራዊ አስተዳደር በአፋጣኝ ካልመሰረተ – ህልውናው ተሸጦና ተበትኖ በባርነት ለመኖር የተስማማ መሆኑን ማወቅ አለበት!!!!
፨ አማራው በብአዴን/ብልጽግና ስር እየተገዛና እየተመራ አይደለም ወያኔን የመሰለ ወራሪ ተዋጊ የደረጀ የታጠቀና መንግስታዊ ቁመና ያለውን አደገኛ የአማራን ጠላት ተከላክሎ ማሸነፍ ይቅርና በአደረጃጀቱ በትጥቅና በሰው ኋይል እዚህ ግባ በማይባለው የጉምዝና የኦነግ ታጣቂዎች ጥቃት እንኴን መከላከል የማይችል ተሸናፊ ባሪይ ሕዝብ ይሆናል።
ከአጣዬ፣መተከልና መሰል እልቂቶች ያልተማርን ከሆነ በእነዚህ ሁለት ግዛቶች የተፈጸሙብን ጭፍጨፋ በሁሉም መመዘኛ እጅግ አናሳ በሆኑ ኋይሎች ሆኖ ሳለ እራሳችንን ማዳንና መከላከል ያልቻልንበት ምክንያት እየገዛን ባለው ብአዴን ብልጽግና አመራር ምክንያት ነው።
፨ አማራው በብአዴን/ብልጽግና ስር እየተገዛ አይደለም ከተደራጀቺዋ ትህነግ ወረራና ጥቃት እራሱን ሊከላከል ይቅርና እጅግ አናሳና ኋላቀር በሆነው የጉምዝ ታጣቂዎች ወረራና ጥቃት እንኴን እራሱን መከላከል አይችልም
ኢትዮጱያን ለሺህ ዘመናት እየገነባና ብሎም ደሙን አፍሥሶ አጥንቱን ከስክሶና ምትክ የለሽ ብርቅና ውድ ህይወቱን ሰውቶ ሀገር ጠብቄያለሁ የሚለው አማራ በዚህ ትውልድ ነው እጅግ በሚያሰቅቅ በሚያሳፍርና በሚደንቅ ውርደት በሁሉም መመዘኛ ከእሱ  ባነሱ የጉምዝ፣የኦነግ/ኦህዴድና የትህነግ ታጣቂ ኋይሎች እየተፈራረቁበት መጫወቻና መሳለቂያ የሆነው በዚህ በብአዴን/ብልጽግና ስር እየተገዛና እየተመራ ስለሆነ ነው።
፠ እናም – እማራው እንደ ሕዝብ ህልውናውን አስጠብቆ ማስቀጠል ከፈለገ፦
1ኛ – NO MORE ADP
2ኛ- NO MORE ODP
3ኛ- NO MORE PP
4ኛ- NO MORE TPLF
በማለት  ሁለንተናዊ የትግል ኋይሉን በአንደኛ ተራ ቁጥር ላይ ባለው ብአዴን ላይ በማዋል ከስርመሰረቱ ለአንዴና ለመጭረሻ ጊዜ ነቃቅሎ በመጣል የራሱን ነጻ አማራዊ አስተዳደር ማቌቌም ይገባዋል።
፨ የድንጋይ ወፍጮ አንገቱ ላይ የታሰረ ሰው ባህር ውስጥ ቢጣል የታሰረበትን የድንጋይ ገመድ ሳጽበጥስ ዋኝቶ ነፍሱን ማዳን ይቻለዋልን?
Filed in: Amharic