የህወሀት ግስጋሴ የመከላከያው ማፈግፈግ ሸዋሮቢትን እስከማስረከብ ደርሷል…!!!”
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በየኛ ቲቪ ያስተላለፈው መልዕክት ባጭሩ:–
~ ሸዋሮቢት በህወሃት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ገብታለች::
~ ከተማዋን ሲጠብቅ የነበረውን ህዝባዊ ሃይል አስወጥተው እኛ አለን እንከላከላለን ሲል የነበረው መከላከያ አፈግፍጓል::
~ ህዝብ በራሱ ተደራጅቶ እራሱን መከላከል ባለበት መንገድ መስራት ይጠበቅበታል እንጅ በመንግስት ላይ ያለን እምነት እና መተማመን መቀጠል የለበትም::
~ መከላከያ እየተከተለው ያለው ማፈግፈግ የሚለው አካሄድ ፍጹም ስህተት ነው:: መሳሪያ እና ልብሱን እየጣለ፡ ህዝቡን እና ህዝባዊ ሰራዊቱን ለጠላት አጋልጦ የሚሸሸው ልክ አይደለም::
~ ሸዋሮቢት እና ደብረሲና ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ወደ ደብረብርሃን እየሸሹ ነው::
~ የህወሃት ታጣቂዎች ሸዋሮቢትን ተቆጣጥረው ወደ ደብረሲና እየቀረቡ ነው::
~ መንግስት በሁመራ እና በሚሌ በኩል ሃይሉን እና ጉልበቱን ማሳየት ሲችል በወሎ እና በሸዋ ግንባር ግን ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ አልፈለገም:: ይህ ለምን እንደሆነ አይታወቅም::
~ መንግስት ከ110 ሚሊየን ህዝብ በላይ ደጋፊ ከጎኑ ይዞ የሃይል እጥረት የሚል ሰበብ ማቅረብ አይችልም::
~ እኛ እየተናገርን ያለነው ዛሬ ላይ እንዳንናገር እየተደረግን ቢሆንም ነገ እውነቱ ታውቆ ታሪክ ሊጽፈው ይችላል::