>
5:26 pm - Friday September 15, 1989

•…ኢትዮጵያን የነካ…  (ዘመድኩን በቀለ)

•…ኢትዮጵያን የነካ… 

ዘመድኩን በቀለ

“…ጣልያን ሮማ ገና ልዕለ ኃይል ከሚባሉት የዓለም ኃያላን መንግሥታት መካከል አንዷ ነበረች። የካቶሊክ ሃይማኖት መንበረ ጵጵስና መቀመጫ፣ በሥነ ሥዕል፣ በሥነ ህንጻ፣ በሙዚቃው የተራቀቁ ጠቢባን መናሃሪያ ማዕከልም ነበረች። ሮማ በቅኝ ግዛት ያልገዛችው ሃገር በጣም ጥቂት እንደነበር፣ እነ ጀርመን ሁሉ በሮማውያኑ ሥር እንደነበሩ ይነገራል። እስራኤል ኢየሩሳሌምም በእነሱ ቁጥጥር ስር ነበር። ክርስቶስ ኢየሱስም ለሞት የበቃው በሮማውያኑ የፍርድ ሸንጎ ነበር። ገናናዋ ሮማ ከዘመን ብዛት እየወደቀች ብትመጣም እንኩትኩቷ ወጥቶ የአውሮጳ ደሃ ሃገር እንድትሆን ያደረጋት ግን የማይነካውን በመንካቷ ” የእግዚአብሔር መቅደሱ ኢትዮጵያን” በመዳፈሯ ነው። ውቃቢ የራቃት፣ መቅኖዋ የፈሰሰው፣ ቆሌዋም የተገፈፈው ኢትዮጵያ ላይ ከተነሣሣች በኋላ ነበር። ሃቅ…
…አሁን ደግሞ ከጣሊያን ትምህርት ያልወሰደች ከተፈጠረች 400 ዓመት እንኳ በቅጡ ያልሞላት፣ በአይሪሽ ስደተኞች የተፈጠረች፣ የዘመኑ ልዕለ ኃያል ሃገር ነኝ ባይ ትእቢተኛዋ አማሪካ የሌለ አቅበጥብጧታል። 24/7 ኢትዮጵያን ለመናድ እንቅልፍ አጥታ የምታድረዋ አማሪካ መውደቂያዋ ብቻ ሰይሆን ለመታሰቢያ የሚተርፍ ነገር በዚህ ምድር ሊያሳጣት ነው መሰል የሌለ ተቅበዥብዣ ሆኗ ከማይገባው ቀይ መስመር አልፋ ዘው ብላ ገብታለች። ሃሺሽ ለምዶ እንደቀረበት የሃሺሽ ሱሰኛ ነው እያክለፈለፋት የሚገኘው። ታደርግ ትሠራውንም አሳጥቷል።
…ኢትዮጵያን ሲያዩዋት ከሩቅም ከቅርብም በሥጋ ዓይን ለሚመለከቷት ጭርንቁስ፣ ደሀ፣ ምስኪን፣ የእኔ ቢጤ፣ አቀመ ቢስ እንኳን ገፍተዋት እፍ ቢሏት ተከስክሳ በአፍጢሟ ተደፍታ ብትንትኗ የሚወጣም ነው የምትመስላቸው። ብዙዎች ኢትዮጵያን የሚያዩት በዓለም መነፅር ነው። እሱ መነፅር ደግሞ የኢትዮጵያን ቁልጭ ያለ ማንነት ለማሳየት አይመችም። ያቀዣብራቸዋል። እናም ይሸወዳሉ። ከዚያም ይገዳደሯታል።ሊገፏት፣ ሊጨብጧትም ይሞክራሉ። ሆኖም ግን አይሳካላቸውም። ባልተሳካላቸው ቁጥር ደግሞ የበለጠ ንዴት ቁጣ፣ እልሃቸውም ይጨምራል። ከዚያ በኋላ የመውጊያውን ብረት ይቃወማሉ። ይገፋሉ። ራሳቸው ተወግተው ይወድቃሉ።
…ወያኔ የዓለም መንግሥታት ሁሉ የርኩሰታቸው ፈቃድ ማፈጸሚያ ኮንዶማቸው ነበር። ቅድስት ኢትዮጵያ ላይ ነውር ኃጢያታቸውን የሚያራግፉበት ፈረሳቸው ነበር። የኢትዮጵያን ቅድስና የሚሸረሽርላቸው መሳሪያቸውም ነበር። በኢትዮጵያ በኩል አፍሪካን መጠምዘዣ ሮቦታቸውም ነበር። የኢትዮጵያን ቅድስና የሚያረክስ ሰይጣን የዲያብሎስ ግልገላቸውም ነበር። በመቅደስ ኢትዮጵያ ውስጥ በርኩሰት እንዲመላለሱ የሚያደርግ ሎሌያቸውም ነበር። ገነት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘው ብለው እንዲገቡ የሚያደርግ እባብ ዘንዶአቸውም ነበር። አዎ ይሄ የክፋት የርኩሳቸው ዘንዶ መነቀሉ ነው ነው ያበሳጫቸው። ይሄ የዘንዶ አንገት ራሱም መቀጥቀጡ ነው ኢትዮጵያን እንደ አንደኛዋ ክፍለ ሃገራቸው ቆጥረው ነጠላ ዘቅዝቀው እዬዬ እንዲሉ ያደረጋቸው። በሚያምኑት ዐብይ ሳይቀር መከዳታቸው፣ ተስፋ ጥለውበት ባልገባቸው መንገድ አልታዘዝ ማለቱ ነበር አሁን እንዲህ ያፎገላቸው። የሚገርመው ግን ኢትዮጵያን አይችሏትም። አያሸንፏትምም።
…ኢትዮጵያ ዓሣ ናት፣ ለሰይጣናት ፈቃድ የማትጨበጥ ዓሣ። ኢትዮጵያ ተልባ ናት። ለአፋቃሬ አጋንንቶች ሁሉ የማትጨበጥ ተልባ። ሙልጭልጭ የምትል ተልባ። ኢትዮጵያ የጋለ የብረት የኳስ አሎሎ ናት። ሲያዩዋት የምታምር፣ ሲጨብጧት የምትፋጅ እሳት ናት። ኢትዮጵያን የሚያውቋት የሉሲፈር መንፈስ ርዝራዦች አይደሉም። ኢትዮጵያን የሚያውቋት በስሱም ቢሆን ማንነቷ እንዲገለጥላቸው የተፈቀደላቸው አካላት ብቻ ናቸው። ኢትዮጵያ የሙሴ ጽላት መቀመጫ መንበሩ ናት። ኢትዮጵያ የክርስቶስ ኢየሱስ መስቀሉ ማረፊያ ዙፋኑ ናት። ኢትዮጵያ መካነ ቅዱሳት ናት። ኢትዮጵያ 24/7 ስመ እግዚአብሔር የሚጠራባት የቅዱሳን ምድር ናት። (ይሄ የአውሮጳና የአማሪካ የሃይማኖት ፍልስፍና የወለደውን ዲቃላውን አጭቤ ነጋዴ አይመለከትም) አዎ ኢትዮጵያ በምድር ካሉ ሃገራት ሁሉ የተለየች ናት። በ20 ዓመት የአፍጋኒስታን ቆይታቸው የተባበሩት መንግሥታትን ሁለት ጊዜ ብቻ ለውሳኔ የጠሩት አካላት ለኢትዮጵያ ሲሆን በአንድ ዓመት 12 ጊዜ ስብሰባ ሲቀመጡባት ስታይ የኢትዮጵያ ክብር እና ውድ ዕንቁ የመሆኗ ምስጢር ይገለጥልሃል።
…ይሄን ስንል የሚበሳጩ፣ የሚጎፈሉ፣ የሚናደዱ፣ የሚንበጫበጩ፣ ለሃጫቸው እስኪዝረበረብ ድረስ የሚንተፋተፉ፣ እሷ ኢትዮጵያ ከሶሪያ፣ ከየመን፣ ከኢራቅ ከሊቢያ በምን ትለያለች? የሚሉ የራሳችን ባንዳ የአጋንንት ፈረሶች እንደአሸን ፈልተው እንደሚተራመሱ እናውቃለን። ደግሞም የትየለሌ ናቸው። የእናት ጡት ነካሾች፣ የተረገሙ። አዕምሮአቸው የተደፈነ፣ የጠላት ቅጥረኞች፣ ዘማውያን፣ ነፍሰበላ ሰዶማውያን፣ አረመኔዎቹ ጡት ነካሽ ባንዳዎች ነፍ ናቸው። በኢትዮጵያ ታላቅነት የሚያፍሩ፣ ነጭ ስላልገዛን የሚቆጩ፣ ባርያ የባርያ ልጆች ነፍ ናቸው። “ኢትዮጵያን ሲኦልም ድረስ ገብተን ቢሆን እንበትናታለን” እስከማለት የደረሱ የአጋንንት ፈረሶችን የሚደግፉ የትየለሌ ናቸው። የፈረሱ ጋላቢዎችም፣ ፈረሶቹም ግን ሁላቸውም በአንድነት ይወቃሉ። ይደቅቃሉ። ይደመሰሳሉ።  እግዚአብሔር ታላቅ ነው።
…አሜሪካ የጥንታውያን ሃገራት ቀበኛ ናት። ገና ለጋ ጩጬ ስለሆነች በጥንታውያን ሃገራት ትቀናለች። አይኗ ደም ነው የሚለብሰው። አሜሪካ ጥንታዊቷን ሶሪያን አፍርሳለች። ጥንታዊቷን ኢራቅን አፍርሳለች። ጥንታዊቷን ሊቢያን አውድማለች። ጥንታዊቷን የመንን ፍርስርሷን አውጥታለች። አሁን የቀረቻት ጥንታዊቷ ሃገር ኢትዮጵያ ናት። ሶማሌን ገንጥለው፣ ጁቡቲን፣ ኤርትራን ቆራርጠው ገንጥለው። ያለ ወደብ፣ ያለውኃም አስቀርተዋት አልረኩም። ከባህሩ አርቀውን ሊያጠፉን በብርቱ ደክመዋል። አሁን ደግሞ ትግራይን ገንጥለው፣ ኦሮሚያ የምትባል አዲስ ሃገር ፈጥረው፣ ሶማሌን ለብቻው፣ ጋምቤላን ወደ ደቡብ ሱዳን፣ ቤኒሻንጉልን ለሱዳን ሰጥተው ኢትዮጵያን ብትንትኗን ለማውጣት ነበር ድካማቸው። እሱ ግን አይሳካም።
… ኢትዮጵያን በሃለል መሳፈጥ ከጀመረች ወዲህ እሜቴ አሜሪካ አሁን መዋረድ ትጀምራለች። #Nomore ዓለምአቀፋዊ የአማሪካና የተባባሪዎቿ የመውጊያ ብረት ሆኖ ያገለግላል። ዳግማዊ ዓድዋ ዳግም በዚህ ዘመን ይገለጣል። አሜሪካ እና ሸሪኮቿ ሁሉ ነገራቸው ” ጓ ” ይልባቸዋል። ብኩርናዋም ለሌላ ይሰጣል። መቅኖ ቢስም ትሆናለች። ኢትዮጵያ ዳግም ታሸንፋለች። የኢትዮጵያ ተዋጊዋ እግዚአብሔር ነው። የኢትዮጵያ ተዋጊ ልዑል እግዚአብሔር ነው። እሱ ባይሆንማ ኖሮ እንደ ውስጥ ከሃዲው ብዛት፣ እንደ ውስጥ ሃገር ሻጩ ባንዳ ብዛት ይሄኔ እኮ የለችም ነበር። አንድም ፓስተር አማሪካን ሲቃወም የማታየው ለምን ይመስልሃል? አሜን ነው? አሜን ሃሌሉያ ብቻ ሙያ መስሎሃል። ሂኢ…
… ማርያምን ኢትዮጵያ ግን ትነሣለች  !! 
• ድል ለዐማራ ፋኖ ‼
• ድል ለዐማራ ልዩ ኃይል ‼
• ድል ለዐማራ ሚኒሻ  ‼
• ድል ለዐፋር ልዩ ኃይል ‼
• ድል ለአፋር ሚኒሻ  ‼
• ድል የኦነጋዊያኑን ሴራ ተቋቁመው ሃገሬን ብለው ለሚዋደቁ ለመከላከያ ሠራዊት አባላት በሙሉ ‼
• ድል ለኢትዮጵያ ‼ 
Filed in: Amharic