>

".... በመጨረሻው ሰአት አብይ አሕመድ እና ቻይና ጨዋታውን ቀየሩት... !!!" (ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ አህመድ አልብሔይሪ.!)

 
“…. በመጨረሻው ሰአት አብይ አሕመድ እና ቻይና ጨዋታውን ቀየሩት… !!!”
ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ አህመድ አልብሔይሪ.!
ሱሌማን አብደላ

« ከገባንብት ጭንቀት ከፈጣሪ በታች ያወጣናል ብለን ተስፋ ያደረግነው በህወሓት ሀይል ነበር.»! ደስታችንን ሳናጣጥም ነገሮች ባልጠበቅነው መንገድ የጠበቅነው ብረሀን ወደጨለማ ተቀይሮ መጣ።
.
እኛ የተከተልነው የአለምን ሚዲያዎች ዘመቻ ብቻ አልነበረም። አሜሪካና አውሮፓውያን የአብይን መንግስት አይፈልጉትም ነበር። ይህንን እኛም ይሁን መንግስታችን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ባደባባይ ይመሰክሩት ነበር።
ኢትዮጵያዊያን ትግላችን ከምዕራባውያን ጋር ነው ሲሉ እኛም በአሜሪካና በአውሮፓዎች ተማምነን አለም ሲከተለውን የነበረውን ሁሉ ተከትለን የህወሓትን ግስጋሴ እየተከተልን መፈንጠዝ ይዘን ነበር። ምን ዋጋ አለው። የተመኘነው ብረሀን ጨለማ ሆኖ ተቀይሮ መጣብን። ከዚህ ድቅድቅ ጨለማ ወጣን ብለን ፈጣሪን ሳናመሰግን፣ በመጨረሻ ሰአት አብይ አሕመድ እና ቻይና ጨዋታውን ቀየሩት። ደስታችንን ጨለማ ውስጥ ከተቱት።
.
አለቀለት የተባለው የአብይ አሕመድ ስረአት
አለምን ባስገረመ ፍጥነት ተመልሶ በማጥቃት ሙሉ በመሉ የትግራይ ክልልን ሊቆጣጠራት ትንሽ ቀናቶች ብቻ ናቸው የሚቀሩት። የህወሓት ሀይል ተንኮታኩቶ ተኗል። ስምና ንፋስ ላይ የቀረ ጉም ሆኗል። በንፋስ የታጠረ ጉም መጨረሻው ትነት እንጅ ዝናብ አይወጣም። ትርፍ ዳመና ብቻ ነው። ከዚህ ቡኋላ ሁሉም ነገር አክትሟል።
የኛ ህልምና” በህወሓት ላይ ያለን ተስፋ አብሮ ጠፍቷል።
.
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ህዝብ በዙሪያው አሰልፎ  በክብር ፣ በፍቅርና በልዩ እንክብካቤ የመሪነት ምሰሶ ችካሉን ማንም እንዳያነቃንቀው አድርጎ ተክሎታል።
የእኛንም ህልምና ምኞት ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎ አብሮ ቀብሮታል ።
በኢትዮጵያ ላይ የጣልነው ተስፋ በዚህ መልኩ ተቋጭቷል። ሲሲ ዛሬ ግብፅን እቀይራለሁ እያለ በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ላይ ሲያለቅስ ነበር። ለምን አያለቅስ .? በደንብ ያልቅስ እንጅ፣ በወሬ ተበልተን መጨረሻችን እንዲህ ከሆነ ለምን አያስለቅስ፣
ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ አህመድ አልብሔይሪ፤ በሸርቅ ቴሌቪዥን ላይ የተናገረው
Filed in: Amharic