>

"ወልድያና በዙሪያዋያሉ ከተሞች ነጻ ወጡ...!!!"  (የመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት)

“ወልድያና በዙሪያዋያሉ ከተሞች ነጻ ወጡ…!!!” 
 
የመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ያበሰሩት የድል ዜና ዋና ዋና ነጥቦች… ‼

 

*….. በዚህ የማጥቃት እርምጃም የወገን ጦር  የሳንቃን፣ የሲሪንቃን፣ የሰሜን ወሎ ዋና ከተማ የሆነችውን ወልድያ ከተማን፣ ሐራን፣ ጎብየን፣ ሮቢትን እና ቆቦን፣ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል
በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተመራ የሚገኘው ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ማጥቃት ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ አከርካሪው በመመታቱ የጠላት ፍላጎት፣ የማድረግ ዐቅም እና ሥነ ልቡናው ብትንትኑ ወጥቷል፤
–  ሌሊቱን በሙሉና ዛሬ ረፋዱን ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራና የአፋር የጸጥታ ኃይሎች ከንሥሮቹ የአየር ኃይል ጋር የተቀናጀ የማጥቃት ዘመቻ አካሂደዋል፤
– በዚህ የማጥቃት እርምጃም የወገን ጦር  የሳንቃን፣ የሲሪንቃን፣ የሰሜን ወሎ ዋና ከተማ የሆነችውን ወልድያ ከተማን፣ ሐራን፣ ጎብየን፣ ሮቢትን እና ቆቦን፣ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል፤
–  የወገን ጦር በእነዚህ አካባቢዎች የመጨረሻ ሙከራውን ሲያደርግ የነበረውን የጠላት ጦር ደምስሶታል፤
– ከድምሰሳ ተርፎ ወደ ጨርጨርና አላማጣ እየፈረጠጠ ያለውን ኃይል ደግሞ የወገን ጦር እግር በእግር እየተከታተለ ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ እያደረገው ይገኛል፤
– የአካባቢው ኅብረተሰብ በተለይም ወጣቶች ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት በየጢሻው እየተሹለከለከ ለማምለጥ የሞከረውን የጠላት ጀሌ በመልቀም፣ ምንም ዓይነት ንብረት እና ተተኳሽ ይዞ እንዳይወጣ የላቀ የጀግንነት ጀብድ ሠርተዋል፤
– እነዚህ ከተሞች ረዘም ላለ ጊዜ በጠላት እጅ የቆዩና አያሌ በደሎች ሲፈጸምባቸው የነበሩ በመሆናቸው፣ ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራና የአፋር የጸጥታ ኃይሎች ከንሥሮቹ የአየር ኃይል ጋር በመጣመር በፈጸሙት አስደናቂ የጀግንነት ገድል ነጻ በመውጣታቸው እንኳን ደስ ያላችሁ፤
– ይህ በእንዲህ እንዳለ በላሊበላና በሙጃ መካከል ሾልኮ ገብቶ ጋሸናን ለመቁረጥ ሲሞክር የነበረው የጠላት ኃይል በጀግናው የወገን ጦር ከበባ ውስጥ እንዲገባና እንዲደመሰስ ተደርጓል፤
– በዚህም የኀሙሲት፣ እስታይሽ፣ አሁን ተገኝ፣ ድልብ፣ ኩል መስክ እና አካባቢያቸው ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነጻ ወጥተዋል፤
– በአሁኑ ሰዓት ጀግናው የወገን ጦር የላሊበላ አካባቢን ከጠላት በማጽዳት፣ በሰቆጣ ከተማና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የመሸገውን የጠላት ኃይል እየደመሰሰ ይገኛል፤
– እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ኮረም አቅጣጫ እየፈረጠጠ ያለውን ጠላት፤ የወገን ጦር እግር በእግር እየተከተለ ሙት፣ ቀስለኛና ምርኮኛ በማድረግ ላይ ይገኛል፤
 የሕዝብ አደራ የተሸከሙት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን  ልጆች ሐሩርና ቁር ሳይበግራቸው፣ ቀን ከሌሊት በተራራማ ሰንሰለቶች እና በየሜዳው በመወርወር፣  በየደረሱበት በጠላት ላይ  እሳት የሆነውን ክንዳቸውን በማሳረፍ  የሽብር ቡድኑን እስትፋንስ ቆርጠውታል፤
– በተደረገው አስደናቂ የማጥቃት ዘመቻም በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ ወጥቷል፤
– በሁሉም አካባቢ የሚገኘው ማኅበረሰብ፣ ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት ላደረገው አስተዋጽዖ መንግሥት ምሥጋናውን እያቀረበ፤ የተለመደውን የደጀንነትና የጀግንነት ጀብድ እንዲፈጽም ጥሪ ያቀርባል፤
Filed in: Amharic