>

የሱዳን ጦር እና የአማራ ልዩ ሀይል ... !!! (ሱሌማን አብደላ)

የሱዳን ጦር እና የአማራ ልዩ ሀይል … !!!

ሱሌማን አብደላ

የሱዳን ጦር ተጨማሪ የቀሩ መሬቶችን ተቆጣጥሬያለሁ እያለ ነው። ማንኛውን መሬት እንደተቆጣጠረ ከማንጋር ውጊያ አድርጎ እንዳስለቀቀ አይታወቅም። ጦሩ ሁሌም የሚለው የአማራ ታጣቂዎች ጋር ተዋግቸ ገለውኝ ወታደር አግተውብኝ ወዘተ እያለ መቀባጠር ይወዳል።
በሱዳን ድንበር በላይ ያለው መከላከያ
ሰራዊት ነው። ከድንበሩ የተወሰነ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ያለው ገበሬ ነው። ንፁህ አራሽ የአማራ ገበሬ ነው። መድፍ ድንሽቃ ታንክ የለውም። አርሶ አደር ነው። አርሶ አደርን አፈናቅሎ መሬቴን አስመለስኩ ብሎ መግለጫ ይሰጣል።
ዋናው ነገር ጦሩ ከበፊቱ ይዞታው ወደፊት ገብቶ ተጨማሪ መሬቶችን ከአማራ ክልል ውስጥ ቀምቶ ተቆጣጥሯል ወይ የሚለው ነው። ጦሩ ወደፊት አንዲት እርምጃ አልተላወሰም። አልመጣምም። እንዳይመጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊትና የአማራ ልዩ ሀይል መግቢያ መንገዶቹን ዘግተውበታል።
ልዩ ሀይሉ ከዚህ ቀደም ሦስት ጊዜ ወደፊት እየገባ ደቁሷቸው ተመልሷል። መከላከያ ሳይፈቅድ በቆረጣ ገብቶ ታንክና ወታደራዊ መሳሪያ ሳይቀር ቀምቷቸዋል። የተጠለሉበትን ምሽግ ሁሉ በዲሽቃ ቀጥቅጥ ነበር ያስለቀቃቸው። ይሄንን ዜና ማንኛውም ሚዲያ አልዘገበውም። የነሱ ሚዲያዎችም አፍረው አልዘገቡትም። የተለየ እንቅስቃሴ ሴያደርጉ ልዩ ሀይሉ ነው ሁሌም ቀጥቅጦ የሚያባራቸው። ደምኮ ሽንፈት አይወዱም። ጦራቸውም ባንድ ሰአት ውጊያ 20 ኪሎሜትር ለቆ ወደኋላ የሚሸሽ ነው። ይህንን ታሪክ የአማራ ልዩ ሀይል ቢናገረው ደስ ይል ነበር። እኔ ብዙውን ጊዜ የማልፅፈው ገፄን ብዙ የነሱ ሰዎች ስለሚከተሉት በጎልጉል ተርጉመው ያነቡታል ብየ ነው።
ከአራት ቀን በፊት አንድ የተሰራን ነገር ልንገራችሁ። የሱዳን ጦር ማንም የለብኝም እያለ ምሽግ ቁፋሮ ላይ ነው። ይሄንን ያዩት የአካባቢው ገበሬዎች መተው ለልዩ ሀይሉና ለመከላከያ ስራዊቱ ይነግሩታል። መከላከያ ትዕዛዝ ካልተሰጠው አይዋጋም። ያንኛው ሀይል ለመግባት ሙከራ ካላደረገ ወደፊት ገብቶ ጦርነት አይከፍትም። ከመንግስት ፍቃድ የለውም። ስለሚቆፈረው ምሽግ
ልዩ ሀይሉ እና ፋኖው ቁጭ ብሎ ከመከረ  ለማጥቃት ወሰኑ።
ተጀመረ፦
ያለምንም ማመንታ ጧት ሊነጋ ትንሽ ሲቀረው ማጥቃት ይጀምራሉ ። ልዩ ሀይሉና ፋኖው እማሱት ምሽግ ላይ ጎርፍ እንዳመጣው ዶሮ አጭደዋቸው ይመለሳሉ። ይሄንን ያየው የሱዳን ጦር ወደኋላ አፈግፍጎ በታንክና በመድፍ ሲደበድብ አረፈደ። የሚደበድውኮ የራሱን ምሽግ ነው። ልዩ ሀይሉና ፋኖው ስራቸውን ጨርሰው ዳር ይዘው እየሳቁ ነው። ይቺን ነገር የገዳሪፍ ከፍተኛ የአመራሮች ይሰማሉ።
ባልተለመደ ሁኔታ የቀይ ጨረቃ መኪኖች ( የቀይ መስቀል ) ቁስለኛን ይዘው ወደ መሀል ከተማ ሲወስዱ ይታያሉ። በዚህ የተደናገጠው የአካባቢውን ዕዝ የሚመራው ጀነራል አብደል ባቂ ወታደራችን ተጨማሪ መሬቶችን ከኢትዮጵያ ሀይል አስለቅቆ ሙሉ በመሉ ተቆጣጥሮታል አለ። ምን ይበል ? ያሁሉ ሙትና ቁስለኛ በአንድ ሰአት እንደዛ ሲነፍር ህዝቡን ምን ብሎ ያታለው በውሸት ካልሆነ በስተቀር !
ኢትዮጵያ ይሄንን እውነት ስለምታቅ የሱዳን ጦር ስለሚሰጠው መግለጫ መልስ አልሰጠችም። ምን ሊሰራልን እንኳንም አዲስ መሬት ተቆጣጠራችሁ እያልናቸው ነው። ይሄ መፃፍ የለበትም ነበር። የህወሓትና የግብፅ ሚዲያዎች የሱዳን ጦር ተጨማሪ መሬቶችን ተቆጣጠሩ ብለው ሲያራግቡት ህዝባችን እውነታውን እንዲያውቀው ያህል ነው ነፃኩት !
Filed in: Amharic