>
5:14 pm - Friday April 20, 2885

ከንቲባ አዳነች አበቤ በጎንደር ባህረ ጥምቀት  ላይ ንግግር እንዳታደርግ በወጣቶች ተከለከለች....! (ስለ ኢትዮጵያ)

ከንቲባ አዳነች አበቤ በጎንደር ባህረ ጥምቀት  ላይ ንግግር እንዳታደርግ በወጣቶች ተከለከለች….!
ስለ ኢትዮጵያ

 

*…. የጎንደሬዎቹ መልእክት “እጅሽን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሽ!”. ነው!!!
በአማራ ክልል ገዥዎች(ብአዴን)ግብዣ ትናንት አመሻሹ ላይ ሹልክ ብላ ጎንደር የገባቸው አዳነች አበቤ በዛሬው ዕለት በጎንደር ባህረ ጥምቀት ተገኝታ ንግግር እንድታደርግ ብአዴን ቢጋብዛትም በጎንደር ትንታግ ወጣቶች ክልከላ ሳይሆንላት ቀርቷል።
 ብአዴን ለአዳነች አበቤ ከፍተኛ ጥበቃ በማሰማራት ከለላ ለመስጠት ቢሞክርም ወጣቱ ሳይፈቅድ ቀርቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ “ከንቲባ”ተብላ በኦህዴድ ብልፅግና ሹመት ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ በከተማው የሚገኙ ኗሪዎች በነፃነት ዕምነታቸውን እንዳያመልኩ ጫና ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።
በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይዞታ የሆኑትን ስፍራዎች ያላግባብ ለሌሎች አካላት በመፍቀድ ከተለያዮ የዕምነት ተከታዮች ጋር የሃይማኖት ግጭት በአዲስ አበባ እንዲነሳ ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።
በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ጊዎርጊስ አደባባይ በኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ለጥምቀት ከተራ በዕል እንዲሆን የተሰራውን”ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” የሚል መልዕክት ያዘለውን ስዕል ፖሊስ ልካ ማስነሳቷ ይታወሳል።
ይህን ጉዳይ በአንክሮ ሲከታተልና ሲመዘግብ የቆየው ጎንደሬ:-   
ከታላቁዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር አጓጉል ፍትጊያ ውስጥ የገባችው  ከንቱ ማለቴ ከንቲባይቱን አዳነች አበቤ ጥምቀትን ለማክበር ሳይሆን ፖለቲካዋን ልትሰራ መገኘቷን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ::
ለክብሯ ይመጥናታል ተገቢዋም ነው  ያለውን  ሸጋ  አቀባበል አደረገላት! አብልቶ አጠጥቶ እንግዳ አክባሪነቱን አሳይ ለክፉ ምግባር ደግሞ  ይህን ባነር ሸለማት!
መልእክቱም “እጅሽን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሽ!”. ነው!!!
↵በተያያዘም ;- የቴዎድሮስ አገር እምዬ ጎንደር አክባሪዬ ያለችውን ኦባንግ ሜቶን በአባ ታጠቅ ፈረስ ላይ አስቀምጣ በሰንደቅ አላማ አስውባ ከፍ ከፍ አድርገው ውላለች፡፤ ጥንቱንም ጎንደር   ታውቅበታለች!!!
ጎንደር! ጉንደ አገር! የአገር ግንድ!!!
Filed in: Amharic