>

"የእነ እስክንድር ጥድፊያ እርጋታ ከማጣት የመጣ ሳይሆን የታሰበበትና ፖለቲካዊ ትንታኔን መሰረት ያደረገ ነው...!!! " (ቴዎድሮስ አስፋው)

“የእነ እስክንድር ጥድፊያ እርጋታ ከማጣት የመጣ ሳይሆን የታሰበበትና ፖለቲካዊ ትንታኔን መሰረት ያደረገ ነው…!!! “
ቴዎድሮስ አስፋው

1ኛ፦ ጦርነቱን በሚመለከት የአለም አቀፉን ጫና ለመቀነስ መንግስት እየወሰዳቸውና በቀጣይም በሚወስዳቸው ፖለቲካዊ እርምጃዎች ቅሬታ ውስጥ የሚገባና መደመጥ የሚፈልግ
***
2ኛ፦ በመንግስትና በሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች በተለይም አዲስ አበባን በሚመለከት በሚወሰዱ ፖለቲካዊ እርምጃዎችና አቋሞች ምክንያት ስጋት ውስጥ የሚገባና መሰባሰብና መደራጀትን የሚፈልግ
***
3ኛ፦ ምንም እንኳ በይፋ “ለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን” ብለው ባይሰናበቱንም የአብንና የኢዜማ የዕድገት ደረጃ ማብቃት እርግጥ እየሆነ በመምጣቱ ምክንያት የሚበተንና ሌላ አማራጭ የፖለቲካ ስብስብ የሚፈልግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህብረተሰብ ክፍልና የፖለቲካ ማህበረሰብ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመፈጠር ሂደት ላይ ነው።
***
ይህ በአገራችን መፃኢ እድሎች ላይ ከፍ ያለ አውንታዊና አሉታዊ ሚና ሊኖረው የሚችል የፖለቲካ ኃይል በአገራዊ ፖለቲካ ውስጥ በአግባቡ መወከል ካልቻለ ሊፈጠር የሚችለው ፖለቲካዊ ስብራትና ቀውስ በቀላሉ ሊገመት የሚችል አይደለም። በተለይ በፍጥነት እየተቀያየረ ከመጣውና ለመገመት አስቸጋሪ እየሆነ ካለው አገራዊ የፖለቲካ ሁኔታን ከግምት ውስጥ አስገብተን ካየነው “ግዜ የለንም” በሚል እሳቤ በጥድፊያ ሊሰራ የሚገባው ፖለቲካዊ ስራ ነው።
***
ይህንን የፖለቲካ ኃይል በዙሪያው ለማሰባሰብና በአገራዊ የፖለቲካ መድረክ ለመወከል ከማንም የተሻለ የፖለቲካ ስብዕና ላይ ያለው አቶ እስክንድር ነጋ በአፋርና በአማራ ክልል የጀመረውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፓርቲው በአጭር ግዜ ውስጥ ከክልላዊ ወደ አገራዊ የፓርቲ አደረጃጀት ለመቀየር ካለው ፍላጎት ጋር አያይዘህ ካየኸው ጥድፊያው እንዲሁ እርጋታ ከማጣት የመጣ ሳይሆን የታሰበበትና ፖለቲካዊ ትንታኔን መሰረት ያደረገ ስለመሆኑ ግልጽ ይሆንልሃል። ስለዚህ ምንም እንኳን ዛሬ በአንዳንድ ንግግሮችና ድርጊቶች የሚያጣው ነገር ቢኖርም ነገ የሚያገኘውም የሚያስገኘውም ብዙ ነውና መጣደፉን አትጥላው።
***
መልካም በዐል!!!
Filed in: Amharic