>
5:13 pm - Sunday April 18, 4630

የእስክንድርን ምግባር ማድነቅን ከአብይ አምልኮ ጋር ለምታመሳስሉ ውታፍ ነቃዮች ...!!! (ድንበሩ ደግነቱ)

የእስክንድርን ምግባር ማድነቅን ከአብይ አምልኮ ጋር ለምታመሳስሉ ውታፍ ነቃዮች …!!!

ድንበሩ ደግነቱ

ስለ እስክንድር አብዝቼ ስወተውት እናንተ ዓቢይን እንደምታመልኩት ተራ የግለሰብ አምላኪ አድርጋችሁ የምትቆጥሩኝ ካላችሁ ተሳስታችሁዋል። እንዳስረዳ ፍቀዱልኝ። ፀጋዬ ገ/መድሕን ቀዌሳ እንደማንም አንድ ተራ ነፍስ ከአምቦ ዝቅ ብሎ የበቀለ ዜጋ፣ በምግባሩ ገዝፎ ገዝፎ በኢትዮጵያ አድጎ ውቃቢን አክሎ ያለፈ አንድ ነፍስ ነው። በአፉ እንደተናገረው: አንድ ቀን አንድ ጀብራሬ (ሰካራም) አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ አንተ ድንጋይ ጉዋደኞችህ የትና የት ደርሰዋል አንተ እንቢ ብለህ ድንጋይ ሆነህ ቀረህ። እና እሸናብሀለሁ እያለ ሽንቱን ሲያፈስ ፀጋዬ ይሰማል ያያል። ይህን መታገስ ያቃተው ፀጋዬ ከዛ ጀብራራ ጋር አንገት ለአንገት ይተናነቅና በሰዎች ይገለገላል።
ፀጋዬ አቡነ ጴጥሮስ ለቅድስት ኢትዮጵያ የከፈሉትን የሰማዕትነት ዋጋ እንደአንድ ኢትዮጵያዊ ለውለታ ክብር መስጠቱ እንጅ አቡነ ጴጥሮስን ማምለኩ አልነበረም። አሁንም እንደዛ ጀብራሬ እስክንድርን ጉዋደኞችህ የትና የት ሹመት አግኝተዋል፣ አንተ ዝም ብለህ ፌስታል ይዘህ በቺስትነት ትንከራተታለህ እያሉ እንደጀብራሬው የሚሳለቁበት የዓቢይ ካድሬዎች በዝተዋል። እነዚህ ባለጌዎች እንደጀብራራው የሰማዕታት ውለታ ላይ እንደሸኑ እቆጥረዋለሁ። እንደ እስክንድር ለኢትዮጵያ ታላቅነት ክብርና ለዜጎችዋ ልዕልና መስዋዕትነት መክፈል ባልበቃ እንኩዋን እንዚህን ባለጌዎች በፌቡ መፋጠጥ ግን አያቅተኝም። የእስክንድርን ምግባር ሳዳንቅ ግለሰብን እያመለኩ ሳይሆን እንደ ፀጋዬ ለቅድስት ኢትዮጵያ የተከፈለን መስዋዕትነት እያከበርኩ መሆኔ ይታወቅልኝ።
Filed in: Amharic