>
5:13 pm - Monday April 18, 5492

"በኦሮሚያ ክልል በጎሀ ፅዮን ከተማ  30 የሚሆኑ ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን የሸዋ ኦሮሞዎች በግፍ ታረዱ....!!!" (ዘመድኩን በቀለ)

በኦሮሚያ ክልል በጎሀ ፅዮን ከተማ  30 የሚሆኑ ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን የሸዋ ኦሮሞዎች በግፍ ታረዱ….!!!”
ዘመድኩን በቀለ

*….. ትናንት ምሽት ግን የታጠቁ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ቀደም ሲል መንግሥት የተለየ ቀለም በቀባባቸው ዐማሮች ቤት በመዞር ሁሉንም ዐማሮች እና የኦሮሞ ኦርቶዶክሶች ለቅመው ይዘው በመውሰድ ዛሬ ሁሉንም እንዳረዷቸው ነው መረጃው የሚያመለክተው። 
 
“…በኦሮሚያ ክልል በጎሀ ፅዮን ከተማ የሚኖሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን የሰላሌ ሸዋ ኦሮሞዎች በዐቢይ አሕመድና በሽመልስ አብዲሳ ፕላንB የዐማራና የኦርቶዶክስ ማጽጃና ማረጃ ደርጅታቸው በሆነው ኦነግ ሸኔ አማካኝነት መታረዳቸው ተነግሯል።
“…ዐማሮቹ በኦነግ ከመታረዳቸው በፊት መንግሥት የግል መሣሪያ ያላቸውን በሙሉ ነጠቀ። ቀጠለና በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት ሰሞኑን በየታራጆቹ ቤት በራፍ ላይ የቀለም ምልክት አስቀባ። ከዚያም ትናንት ምሽት ግን የታጠቁ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ቀደም ሲል መንግሥት የተለየ ቀለም በቀባባቸው ዐማሮች ቤት በመዞር ሁሉንም ዐማሮች እና የኦሮሞ ኦርቶዶክሶች ለቅመው ይዘው በመውሰድ ዛሬ ሁሉንም እንዳረዷቸው ነው መረጃው የሚያመለክተው።
“…ኦነግሸኔ ተብዬው ቀን ቀን ፖሊስጣቢያ ቁጭ ብሎ የሚውለው ቡድን አሁን በምሽት መጥቶ ንፁሐንን ከማረዱ በፊት በቅድሚያ የኦሮሚያ ፖሊስ ከከተማዋ እንዲወጣ፣ የአስተዳደር ሓላፊዎቹ እንዲወጡ፣ የፀጥታ ክፍሉ ቦታውን እንዲለቅ ከፌደራል መልእክት እንደደረሳቸውና የኦሮሚያ ፀጥታ ሓይሎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ እንደተነገረም ተነግሯል። ብዙዎች በሁኔታው ተደናግጠው የነበረ ቢሆንም የዚህን ያህል የዘር ማጥፋት በመንግሥት ፈቃድ ይፈጸማል ብለው አምነው እንዳልነበረም ነው በስልክ ያነጋገርኳቸው የመረጃ ምንጮቼ የነገሩኝ።
“…አሁን ከጎጃም ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው መንገድ ተዘግቷል። አንድም የፀጥታ ኃይል በአካባቢው የለም። ድፍን የከተማው ህዝብ ወጥቶ እያለቀሰ ነው። ገንዘብ አምጡ ተብለው ወደ ጫካ ለኦነጉ ለመስጠት የሄዱትም ሳይታረዱ እንዳልቀረም እየተነገረ ነው። ምንአልባት የዐማራ መንግሥት ቢደርስልን ንገሩልን የሚሉ ዐማሮችና ኦርቶዶክስ ኦሮሞዎች መንገድ ተዘግቶባቸው የቆሙ ሹፌሮችን ሲማጸኑም ታይተዋል።
“…የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በፀጥታ፣ ያለምንም ተቃውሞና ኮሽታ ዐማራና ኦርቶዶክስን እያጸዳ ነው። ብአዴን ደንተው አይደለም። ህዝቡም መርዶ መስማቱ የተስማማው ይመስላል። የዐማራ አክቲቪስት በጎጥ ተከፋፍሎ ይጠዛጠዛል። ወገኑ ግን በቀን በፀሐይ እያለቀ ነው። ነገ ተረኛው ከተማ ማን ይሆን?
“… ነፍስ ይማር  !!
Filed in: Amharic