>

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ  በአዲስ አበባ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበው ውይይት ማድረጋቸውና ውይይቱ ነገም እንደሚቀጥል ታወቌል፦ *** (ወንድወሰን ተክሉ)

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ  በአዲስ አበባ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበው ውይይት ማድረጋቸውና ውይይቱ ነገም እንደሚቀጥል ታወቌል፦
ወንድወሰን ተክሉ
አዲስ_አበባ_የጠራህ_የሚታመን_ወዳጅ_አይደለም!!
 
* ወዳጄ ሆይ  ባለህበት ጽና!!!!
* አንተ የተፈለግከው በወልቃይት ጉዳይ ብቻ እና ብቻ ነው።  
 
አንተ የተጋደልክለት ወልቃይት ተፈልጔል -ተወስኖበታልም።
 
*   አንተ ወንድሞቼ ያልኴቸው የብአዴን ቱባ ቱባ ባለስልጣናት ተስማምተዋል። ደመቀን አሳምኑ እኛ ችግር የለብንም ብለዋል።
 
* ወልቃይትን ለመውሰድ አንተን አዲስ አበባ ጠርቶ ከሕዝብህ ነጥሎ ከጀግና ጔዶችህ ነጥሎ በፍቅርና በጥይት የማሳመን እቅድን ለመተግበር ጠርተውሃል።
 
 
”   ባለህበት ጽና !!!! 
 
* ትጥቅህን አጥብቅ። ወታደሮችን አጠንክር – ባለህበት ጽና!!!!
ብዙዎች ይህን ቢሉም ኮልኔሉ ወደ መዲናይቱ አቅንቷል!!!

 

በአማራ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ምዕራብ ጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ዞን ም/ል አስተዳዳሪና የሰላምና ደህንነት ጉዳይ ኋላፊ የሆኑት  ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ  የተደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ አድስ አበባ በመጔዝ ማክሰኞ እለት በአገኘሀ ተሻገር በሚመራው  ከፌዴሬሽን ምክር  ቤት ጋር መወያየታቸውን ማወቅ ተችሏል።
የውይይቱ ዋና አጀንዳ በወልቃጽትና ጠገዴ ጉዳይ ላይ ያተኮረ መሆኑን ከማወቅ በስተቀር ለጊዜው በወልቃይት ጠገዴ ላይ ያነጣጠረው ውይይት ይዘትና ዝርዝር ማወቅ ያልተቻለ ሲሆን ውይይቱ በነገው እለትም እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን ለዚህ ውይይት ተጨማሪ ተሳታፊዎች ከወልቃይትና ጠገዴ ተጠርተው አዲስ አበባ መግባት እንደቻሉ ለማወቅ ተችሏል።
ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ከሕዝብ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበው ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ መስጠት ከመቻላቸውም በላይ ምክትል ጠ/ም/ሩን ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፌዴራሉ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደተነጋገሩ መረጃዎች የሚያመላክቱ ሲሆን ከደመቀ መኮንን በኩል መንግስት በደረሰበት ዓለም አቀፍ ጫና ምክንያት የወልቃይት ጠገዴን ግዛት እርቅና ሰላም ለመፍጠር ሲባል ለጊዜው በፌዳራል መንግስት ስር ለማዋል እንደታሰበና ይህንንም ለማድረግ የተፈለገው የትህነግን ወልቃይትና ጠገዴን ግዛቶች ይመለስልኝ ጥያቄን ለማዳፈን ታልሞ ነው የሚል ሀሳብ እንደቀረበና በኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በኩል ብቻውን ውሳኔ ለመስጠት እንደማይችል ጠቅሶ ተጨማሪ አመራሮች ከታች ወልቃይት ጠገዴ እንዲመጡ መጠየቁን ነው ምንጮች የሚገልጹት።
ይህ ሆኖ ሳለ በብአዴን የፕሮፖጋንዳና ቅስቀሳ ዘርፍ በኩል ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ እንደ የወልቃይትና ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴነቱ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ቀርቦ ምላሽ እንዲሰጥ ተደርጔል በማለት ጉዳዩንም ከበጀትና መሰል አስተዳደሮች ጋር የተያያዘ ነው በማለት በመንግስት እንዳልተጠራ አድርገው እያሰራጨ ያለ መረጃ መኖሩንም ማወቅ ተችሏል።
ይህንን የብአዴን የፕሮፖጋንዳ ዘርፍ ያሰራጨውን በማስተጋባት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ወደ አዲስ አበባ የተጔዙት በመንግስት ተጠርተው ሳይሆን እራሳቸው ጠይቀው ነው በማለት እያስተጋቡ መሆናቸውን ማየትና ማወቅ የተቻለ ሲሆን እውነታው ግን ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በመንግስት ፍላጎትና ዓላማ ተጠርተው አዲስ አበባ መጔዝ እንደቻሉ ነው የሚታወቀው።
እንደዚህ ጸሀፊ እምነትና በርካታ የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች ለኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ከመንግስት በኩል የተደረገለትን ጥሪ ተቀብሎ ወደ አዲስ አበባ እንዳይጔዝ የሚያሳስብ መልእክት ያስተጋቡ ቢሆንም ኮ/ሉ ወደ አዲስ አበባ ከመጔዝ ግን ለማስቀረት አልተቻላቸውም።
በአቢይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና መንግስት ከትህነግ ጋር ምስጢራዊ ድርድር እያደረገ ያለ ስለመሆኑ የአደባባይ ምስጢር ሲሆን የሁለቱ ወገኖች የመደራደሪያ ወሳኝ ነጥቦች ውስጥ አንዱና ወሳኙ ክፍል የወልቃይት ጠገዴና የራያ ይገባኛል ጉዳይ የመሆኑ እውነታና ዛሬ ይህው መንግስት የወልቃይትና ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ መሪ የሆኑትን ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን አዲስ አበባ መጥራት አላማው ምስጢራዊውን ድርድር ውጤታማና ስኬታማ አድርጎ ከወያኔ ጋር መሰረታዊ የሆነ ስምምነት ደረጃ ላይ ለመድረስ የወልቃይት ጠገዴና የራያን ጉዳይ ከመላው የአማራ ሕዝብ እምነትና አቌም ባፈነገጠ መልኩ ለመፈጸም ተዘጋጅቷል የሚያስብሉ በርካታ መረጃዎች ከመንግስት በኩል እየሾለከ ወጥቶ እንድናውቀው መቻሉን መጥቀስ ይቻላል።
የሆነው ሆኖ ዛሬ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበው ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። ከደመቀ መኮንን በኩል የቀረበላቸውንም አዲስ ሀሳብ ሰምተው ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ አመራሮችን ከወልቃይትና ጠገዴ አስመጥተው ነገም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበው እንደሚመልሱ ይጠበቃልና በዚህ አጋጣሚ ማስተላለፍ የምንፈልገው መልእክት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱና አጋር ባልደረቦቻቸው አቢይና ደመቀ መኮንን መራሹን የብልጽግናን መንግስት ከማመን እንዲቆጠቡና ብርቱ የሆነ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ ሲሆን መላው አማራ ግን ይህንን ሂደት በቅርበትና በጥልቀት እንዲከታተል አበክረን እናስገነዝባለን።
ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳሽ!
Filed in: Amharic