>

የሽመልስ አብዲሳ ትርክት የደም ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም...!!!!  ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ ከባላገሩ ቴሌቪዥን

የሽመልስ አብዲሳ ትርክት የደም ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም…!!!! 
ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ ከባላገሩ ቴሌቪዥን በነበረው ቆይታ ከተነሰቱት ነጥቦች በጥቂቱ
ሰለሞን አላምኔ

 

*…. የፋኖ መለያ የአይበገሬነት የአሸናፊነት መንፈስ የአማራው ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያውያን መንፈስ ነው!!!
 
*…. ጦርነቱ ሊያበቃ የሚችለው ህውሃት ትጥቅ ሲፈታ ብቻ ነው…!!!
የኦሮሚያ ክልል ቁርጠኛ ቢሆን ኖሮ ሸኔን ማጥፋት ይቻል ነበር ነገር ግን የክልሉ መንግስት ፈቃደኛ አይደለም! አለ ቢባል እንኳን ውጤት አላመጣም።
ፋኖ በኦሮሚያ ክልል ተደራጅቶ ኦሮሞን ገደለ የሚለው ነገር ፍፁም ውሸት ነው። እንዲህ አይነት ትርክት ለምን ማራገብ እንደተፈለገ እናውቃለን። ነገር ግን አይደለም እንጅ ከተደረገ እነሱንም ቢሆን ከሽኔ እኩል እንከሳቸዋለን። ለይተን አናይም።
አልጠራም። የኦሮሚያ ክልል ራሱን ሊያጠራ አልቻለም። ለዚህ ነው ተጠያቂነትም የክልሉ መንግስት መኖር አለበት የምንለው።
የጀኖሳይድ አደጋ ህሊና ላለው ሰው ፣ ሰው ለሆነ ሰው፣ የጀኖሳይድ አደጋ ያለው አማራው ላይ ነው። የሽመልስ አብዲሳ ትርክት የደም ዋጋ ያስከፍለናል። ማስከፈሉ አይቀርም። ይህችን ነገር ቀለል አድርገን ማየት የለብንም።
ፋኖ እና ባልደራስ የተሳሰርነበት ጉዳይ ሸኔ አማራ ብሎ ጭፍጨፋ እየፈፀመ ነው። በወለጋ በሸዋ እየፈፀመ ነው። አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ለመፈፀም እያሰበ ነው። ፌደራል መንግስቱ እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሸኔ ለማጥፋት ስላልቻለ ነገ ከነገ ወዲያ ሸኔን ለማጥፋት ፋኖ ያስፈልጋል።
 ስለዚህ ፋኖን እና ባልደራስን ያገናኛቸው የጋራ ጠላትነት ነው ከህውሃት ቀጥሎ ሸኔ ላይ ፌደራል መንግስቱ እርምጃ መውሰድ አለበት። ማለቂያው ሸኔ ላይ መሆን አለበት።
ህውሃት ገፍቶ ሲመጣ መከላከያ ረግቶ እንዲዋጋ እና በልበ ሙሉነት እንዲፋለም ጥንካሬ የሆነው በመንፈስም ጭምር የጦርነቱን ውጤት እንዲቀየር ያደረገው በዋናነት ፋኖ ነው።
የፋኖ መለያ የአይበገሬነት የአሸናፊነት መንፈስ የአማራው ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያውያን መንፈስ ነው።
ከአብን ጋራ የሚያጋጭ አላማ የለንም። የሄድነው የፖለቲካ ሀሳብ ይዘን አይደለም። ኢትዮጵያን ይዘን ነው የሄድነው።
ባልደራስ የፖለቲካ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ነው የምንፈታው። ይሄ ሊሰመርበት ይገባል።
በድምጽና በምስል – ሊያዩት ሊያደምጡት የሚገባ
Filed in: Amharic