>

"ከቀይ ኮከብ ዘመቻ ፋይሎች....!!!!" (ጓል ፈዳይን ሻዕቢያ ቫይናክ)

“ከቀይ ኮከብ ዘመቻ ፋይሎች….!!!!”

ጓል ፈዳይን ሻዕቢያ ቫይናክ

የዛሬ 40 አመት በያዝነው ሰሞን የቀይ ኮከብ ሁለገብ አብዮታዊ ዘመቻ በኤርትራ ተጀመረ፤
ጦርነቱ የጀመረው በምዕራባዊው ቆላማ አካባቢ በከርከበት በኩል ነበር፤ ከፍተኛ የሰው ኃይል የተሰጠው ግዙፉ ሰራዊትና ትልቅ መወዕለ-ኢኮኖሚ የፈሰሰበት ጦርነት ተጀመረ፤ ገዳም ግን አልነበረም፤ ጦርነቱን የመሩት ኮለኔል ውብሸት ማሞ ነበሩ፤ የተሰጣቸው መረጃ እና መሬት ላይ የጠበቃቸው ጦርነት የተራራቀ ነበር፤ ውጤቱም ሽንፈት ሆነና ሪፖርታቸውን ለበላይ አለቆቻቸው ላኩ፤
“… አግባብነት የጎደለው የጠላትን የመሬትን ገጽታ ያላገናዘበ፣ እንኳን ከማሰልጠኛ ወደግዳጅ የገባ የ21ኛ ተራራ ክፍለጦር ሠራዊት ይቅርና ለነባር ክፍለጦሮቻችንም የሚከብድ ግዳጅ መስጠቱ ውጤቱን አባብሶታል፤…” ብለው ነበር የጻፉት፤ የኮለኔል ውብሸት ማሞ ሪፖርት አሃዛዊ መግለጫውም 536 መሞታቸውን፣ 748 ከባድና ቀላል ቁስለኞች መሆናቸውን እና 114 ደግሞ የት እንደደረሱ የማይታወቅ መሆኑን ይገልጽ ነበር፤
አለቆቻቸው ሪፖርቱን እና መርዶ ነጋሪነታቸውን አልወደዱትም፤
መጋቢት 19፣ 1974 በብርጋዴር ጀነራል ሙላቱ ነጋሽ የተፈረመ “ጥብቅ ሚስጥር” የሚለው ደብዳቤ የክፍለጦሩ አዛዥ የነበሩት ኮለኔል ውብሸት ማሞ አብዮታዊ እርምጃ (በሰራዊታቸው ፊት በጥይት እንዲረሸኑ) መወሰኑንና ይህም ተፈጻሚ መሆኑን ይገልጻል፤
Filed in: Amharic