>

አዳነች አበቤ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ገጠማቸው... ህዝቡ ከአዳራሽ ጥሏቸው ወጥቷል...!!! (ባልደራስ)

አዳነች አበቤ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ገጠማቸው
 ህዝቡ ከአዳራሽ ጥሏቸው ወጥቷል…!!!
ባልደራስ

 

 የታፈሱት የአዲስ አበባ ወጣቶች ከእስር እንዲለቀቁ ሕዝቡ ጠይቋል 
/
ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ከጉባኤው በኋላ ከነዋሪዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን እንመልሳለን በሚል የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አዳነች አበቤ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው፡፡ከንቲባዋ በኮልፌ ቀራኒዮ ከሕዝብ ጋር ለመገናኘት ሞክረው፣ ሕዝቡ በተቃውሞ አዳራሹን ለቆ የወጣ ሲሆን፣ ከአዳራሹ ባሉ ፖሊሶች አስገዳጅነት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡
ከንቲባዋ ከተመረጡ ደጋፊዎቻቸው ብቻ የመወያየት እቅድ የነበራቸው ቢሆንም፣ ሾልከው ከገቡና አዳራሽ ጥለው ለመውጣት ከሞከሩት የከተማዋ ነዋሪዎች  ከተነሱት ተቃውሞዎች መካከል፣ በግፍ የታሰሩት የአዲስ አበባ ወጣቶች ከእስር እንዲለቀቁ፣ በከተማዋ አስተዳደር ውስጥ ዘረኝነትና ሙስና እንደሰፈነ፣ የኑሮ ውድነት የከተማውን ሕዝብ እያሰቃየ ነው የሚሉት ይገኙበታል፡፡ በዚህም ሳቢያ፣ “መንግሥትና ሕዝብ ሆድና ጀርባ ሆነዋል”ተብሏል፡፡ 
 
ከተሰነዘሩት የሕዝብ አስተያየቶች መካከል፡-
 
* ባንዲራችሁን በናንተው የመንግስት መስሪያ ቤታችሁ ስቀሉ የእኛን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ አላማችንን ግን ለህዝቡ ተዉለት
 
መበልፀግ ጥሩ ነው። ነገር ግን መጀመሪያ ከዘረኝነት ውጡ! ይህንን ራስ ምታት የሆነ የክልል አወቃቀርም አሻሽሉ! ባንዲራችንንም አክብሩ!” – አርቲስት አበበ ወርቁ
 
1.የታፈሱት የአዲስ አበባ ወጣቶች ከእስር ይለቀቁልን
 
2.በአዲስ አበባ አስተዳደር የባሰ ዘረኝነት ሰፍኗል
 
3.የህግ የበላይነት የለም
 
4. የፖሊስ ምልመላ ለከተማዋ ነዋሪዎች ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባዋል 
 
5. “አገር እያፈረሰ ያለው አውቅልሃለሁ አውቅልሻለሁ ባይነት ስለሆነ፣ ቆም ብላችሁ አስቡ”
 
6. ህዝብን መናቅ፣ ጥቅምን መፈለግ በከተማዋ ባለሥልጣናት ዘንድ የሚስተዋል ችግር ነው
 
7. ሕዝቡ እህል አጥቶ የሚርበውን ያህል፣ ሠላም እርቦታል 
 
8. የቤት ኪራይ ሊያሳብደን ነው፣ ደመወዝ ስለማይጨመርለት የመንግሥት ሰራተኛም ሊያብድ ትንሽ ነው የቀረው
 
9.ባለሀብቶች የዋጋው ንረት ከባሰብን በራችሁን ሰብረን እንመጣለን፣ እኛ እየራበን እናንተ አትበሉም፣
እንደሚታወቀው፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ከአስተሳሰቡና ከፍላጎቱ ውጭ የተጫነበት የከተማዋ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየሄደበት ያለው መንገድ በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል፡፡ በተለይ የገዥው ፓርቲ ከህወሓት ጋር የመታረቅ ተስፋው እየለመለመ በሄደ ቁጥር፣ በከተማዋ ነዋሪ ላይ የሚያደርገው ዘረኛ ተፅዕኖ እየበረታ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም እንደ ዋነኛ መገለጫዎች መካከል፣ በአዲስ አበባ የመንግሥት ት/ቤቶች የኦሮሚያ ክልል ባንዲራን መስቀል፣ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ህገ-ወጥ ነው ብሎ ክልከላ ማድረግ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችን እንደ ጠላት በማየት በአፈሳ ለጅምላ እስር መዳረግ፣ በከተማዋ መስተዳድር ውስጥ ያለው ዘረኝነት መባባስ ይገኙበታል፡፡
Filed in: Amharic