>

በብአዴን አስፈጻሚነት በአማራ ላይ እየተተገበረ የሚገኘው  አፓርታይዳዊ የትምህርት  ፖሊሲ  (አቻምየለህ ታምሩ)

በብአዴን አስፈጻሚነት በአማራ ላይ እየተተገበረ የሚገኘው  አፓርታይዳዊ የትምህርት  ፖሊሲ 
አቻምየለህ ታምሩ

*.... ባጭሩ አማራ ብአዴን እንዳይወጣ እየጠበቀው ከሚገኝበት የቁም መቃብሩ  መግነዙን ቀዳዶና በጣጥሶ፤ የተጫነበትን ብአዴን የሚባል የመቃብር ድንጋይና አፈር ፈነቃቅሎ እስካልወጣ ድረጅ ከዩኒቨርሲቲ ደጃፍ ብቻ ሳይሆን ከምድረ ገጽም የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ አይደለም… !!!
 
ኦሕዴድ ኦሮሙማን በአዲስ አበባ ውስጥ ለመትከልና ኦሮምያ ከሚሉት የተስፋ ምድራቸው ኦሮሞ ያልሆነውን ለማጽዳት ቄሮ የሚባለውን መንጋ ሜንጫና ሚስማር የተጠቀጠቀበት አጣና  አስይዞ ሰልፍ እንዲወጣና ሰላማዊ ዜጎችን እንዲያሸብር ሲያደርግ፤ የአማራው ርግማን ብአዴን ግን የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ውጤታቸውን አበላሽቶ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዳይገቡ ያደረጋቸው የአማራ ገበሬ ልጆች መንግሥት ያለ መስሏቸው በጥረታቸው ያስመዘገቡት ውጤት ይስተካከል ዘንድ በአደባባይ ለመጠየቅ የጠሩትን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ ከልክሏል።
ብአዴን የሚባለው ዘግናኝ ፍጥረት የአማራ ተማሪዎች አሁን እየጠየቁት ያለውን ፍትሐዊ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን አማራ በታሪኩ ሲያደርገው የኖረውን የኅልውና ተጋድሎ ሁሉ እየተከታተለ ሲያከሽፍ የኖረ የአማራ ግንባር ቀደም ባለደም ነው።
የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ የአማራ ተማሪዎችን ውጤት አበላሽቶ የኦሮሞ ተማሪዎችን ብቻ እየመረጠ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ያደረገው የአማራ ተማሪዎች ውጤት እንዲበላሽ ቢደረግ ውጤታቸውን ለማስተካከል የሚያደርጉትን ትግል ብአዴን እንደሚያስቆመው ስለሚያውቅና ኦሮሙማ በአማራ ልጆች ላይ እያራመደ ያለው የትምህርት አፓርታይዳዊ ፖሊሲ በብአዴን ጉዳይ አስፈጻሚነት ተግባራዊ እንደሚሆን ስለሚተማመን ነው።
በኦሮሙማ ውሳኔ ውጤታቸው እንዲበላሽ የተደረገባቸው የአማራ ልጆች በብአዴን ጉዳይ ፈጻሚነት  እየተፈጸመባቸው ያለው የትምህርት አፓርታይዳዊ ፖሊሲ እንዲሻርና በአጠቃላይ ብአዴን የሚባል ቀንበር የቀደቀበት የአማራ ሕዝብ ከተጋረጠበት የኅልውና አደጋ ሊወጣ የሚችለው በዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ ውጤታቸው እንዲበላሽ የተደረጉ የአማራ ተማሪዎች ውጤታቸው ይስተካከል ዘንድ እንዳይጠይቁ የሚያግደውና የኦሮሙማ  የትምህርት አፓርታይዳዊ ፖሊሲ ጉዳይ አስፈጻሚው ነውረኛ ብአዴን ሲወገድ፤ አማራም የቁም መቃብሩን ፈንቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆኑ የተፈጠሩ ሆዳም አማሮች ነውረኛ ድርጅት ከሆነው ከብአዴን መግነዝ ሲፈታ ነው።
ባጭሩ አማራ ብአዴን እንዳይወጣ እየጠበቀው ከሚገኝበት የቁም መቃብሩ  መግነዙን ቀዳዶና በጣጥሶ፤ የተጫነበትን ብአዴን የሚባል የመቃብር ድንጋይና አፈር ፈነቃቅሎ እስካልወጣ ድረጅ ከዩኒቨርሲቲ ደጃፍ ብቻ ሳይሆን ከምድረ ገጽም የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ አይደለም!
Filed in: Amharic