>

"የኦሮሞ ህዝብ የሚፈልገው እራሱን በራሱ ማስተዳደር ነው ፤ ቋንቋውን ማዳበር እና ማጎልበት ነው...!!!" ጃዋር መሀመድ

“የኦሮሞ ህዝብ የሚፈልገው እራሱን በራሱ ማስተዳደር ነው ፤ ቋንቋውን ማዳበር እና ማጎልበት ነው…!!!” ጃዋር መሀመድ
ቃሲም አዳም
አያቶላ ሙላ ዑመር ጃዋር አላስቻለውምና አዲስ ቃለ መጠይቅ አድርጓል።
     … የኦሮሞ ህዝብ በውስጡ የእንግሊዝኛ ቋንቋን ቢያዳብርና ቢያጎለብት ….. እራሱን በራሱ ማስተዳደር አይችልም አያቶላ ሩሆላህ ሁመይኒ ጃዋር? ነው ወይስ አንተም ሆንክ አቶ በቀለ ገርባ አቀላጥፋችሁ ለምትናገሩት የአማርኛ ቋንቋ ከንቱ ጥላቻ እንዳላችሁ እየነገራችሁን ነው። ቋንቋ ብለህ ማጎልበት የሚለውን መጠቀምህ በራሱ አጃኢብ ነው። ቋንቋህን ለማጎልበት የጦር ሃይሎችን የመጠቀም ፕላን አለህ ማለት ነው ?
    “እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ግዛት የተመሰረተው በብሄሮች ጭቆና ላይ ነው” አለ ሁመይኒ ቆጣ ብሎ። እውነክን ነው ?? ዋዉ አያቶላ !! የኬንያ መንግስት እና ግዛት ፣ የናይጀሪያ መንግስት እና ግዛት የጀርመን ፣ ፈረንሳይ ፣ የዩናይትድ እስቴትስ መንግስት እና ግዛት እንዴት ነው የተሰራው ? እንዳውም ከነጭራሹ ፣ ከብሄር ብሄረሰቦች ሽኩቻ እና ጦርነት ውጭ የተሰራ አገር ካለ ለምን አትነግረንም ? ለምንድን ነው ይህ የማህበረሰቦች ችግር ፣ ኢትዮጵያ ላይ ብቻ የተከሰተ ደዌ አስመስላችሁ ለማቅረብ የምትሞክሩት ? ደግመህ እና ደጋግመህ አሃዳዊ  ፣ አሃዳዊ ስትል ሰማን ። አሃዳዊ ስትል ግን ምን ለማለት ነው ? UNITARY ለማለት አስባችሁ ይሆናል የሚል እምነት ነው ያለኝ። እንዴት ነው ግን unitary አስተዳደሮች ኢዴሞክራቲክ ናቸው እያላችሁ ነው እንዴ ያላችሁት ? 60% የአለም አገሮች unitary መሆናቸውን እንዴት ትዘነጋላችሁ ? እንደ ፈረንሳይ እና ጀርመን ያሉ አገሮችን ጨምሮ አያቶላ። ለኔ እስከሚገባኝ ድረስ ፣ አሃዳዊ ማለት ህገወጡ የኦሮሞ መንግስት ነው። unit የሚባሉት ፣ በየትኛውም አስተዳደር ፣ ክልሎች እና ክፍለ ሃገሮች ናቸው። ጋሸ አያቶላ !!! አንተን አንተን ቁጭ አድርጌ የማናዝዝህ እኔ ባለመሆኔ በጣም አዝናለሁ። አንተም እድለኛ ነህ።
Filed in: Amharic