ባልደራስ
*…. የባልደራስ የሀገር አቀፍ ፊርማ ንቅናቄ በደቡብ ክልል ተጀምሯል…!!!
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ደቡብ ኢትዮጵያ፤ አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል። አመራሮቹ ወደ ቦታው ያቀኑት ባልደራስ ሀገራዊ ፓርቲ መሆኑን አስመልክቶ በአካባቢው የሚደረገውን የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ንቅናቄ ለማስጀመር ነው።

አቶ እስክንድር እና አቶ ስንታየሁ አርባ ምንጭ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በቅርቡ የተቋቋመው የፓርቲው የአርባ ምንጭ ኮሚቴ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
/