>

ኣሸባሪው ህወሃት ኣሁን ባቀደው ወረራው ኣሜሪካ ና ግብፅ ትልቅ ተስፋ ጥለውበታል!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ኣሸባሪው ህወሃት ኣሁን ባቀደው ወረራው ኣሜሪካ ና ግብፅ ትልቅ ተስፋ ጥለውበታል!!!

ቬሮኒካ መላኩ


*… ህውሃት ከማይጋባ እስከ መደማመር ድረስ ባለው ቦታ ሌሊቱን ጦርነት ከፍቶ አድሯል!!!

 

በቀይባህርና በአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካ ውስጥ ‘አዲስ ኃይል’ በመፍጠር አሜሪካኖቹ የቻይና-ራሻያን ቀጣናዊ ተፅዕኖ የአስመራን እና የኢትዮዽያን መንግስታት በማዳከም እና በማስወገድ እንደሚሳካ አምነዋል። ለዚህ ደግሞ ትልቅ ተስፋ የጣሉበት ኣሽከራቸውን የወያኔን የሽብር ቡድን ነው።

የአሁኑ የወያኔ ዘመቻ ልዩ ትኩረት የሚያደርገው በኣማራ ክልል በቤኒሻንጉል ክልል እና በኤርትራ ላይ ነው።

በኤርትራ

******

የፕሬዝደንት ኢሳያስን መንግስት በማስወገድ በኤርትራ ውስጥ ለአሜሪካን መንግሰት ታዛዥ የሆነ የአሻንጉሊት መንግስት ማስቀመጥ ኣሜሪካ ለህወሃት የሰጠችው ግብ ነው።

ሌላው የወያኔ ፍላጎት “የአሰብን ወደብ መያዝ” ልዩ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፤ በቀጣይ ለታላቋ ትግራይ ግንባታ ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል።

በኣማራ ክልል

*********

ኣንደኛው የሽብር ኃይል፦ ከትግራይ በወልቃይት ጠገዴ ኣቅጣጫ ወደ ሱዳን ኮሪደር ሲሆን፣ በጠለምት ከሽረ ወደ ኣዲ ኣርቃይ- ጃን ኣሞራ- ደባርቅ- ጎንደር ነው።

ሁለተኛው ደግሞ በሱዳን የሚገኘው የሽብር ኃይል ከሱዳን ኣቅጣጫ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ውጊያ በመክፈት የሱዳንን ኮሪደር ኣስከፍቶ ወደ ጎንደር በማቅናት በኣማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ፈጽሞ በማለፍ የህዳሴ ግድብን ለመቆጣጠር ያለመ ነው።

ሦስተኛው የሽብር ኣቅጣጫ ደግሞ በበለሳ- እብናት ኣቅጣጫ ወደ ባህርዳር ጎጃም የሚጓዝ ነው።

ኣራተኛው ደግሞ በራያ ኣቅጣጫ ወደ ወሎ- ሸዋ በመጓዝ በጎጃም ከሚመጣው የሽብር ቡድን ጋር ኣኣን የሚቆጣጠር ነው።

ኣምስተኛው ግን በዋናነት በግብጽና በሱዳን የሚደገፍ ከሱዳን ወደ ቤኒሻንጉል በመሄድ የህዳሴ ግድቡን የሚነጥቅ የሽብር ሃይል ነው። ይህ ኃይል በጎንደር ከሚመጣው ጋር ተናብቦ የሚያሸብር ነው።

የህወሃት የሽብር ቡድን የስልጠና እና የጦር መሳርያ ድጋፍ የሚያገኘው ከኣሜሪካ እና ከግብጽ ሲሆን በተጨማሪም ወታደራዊ የሳተላይት መረጃ ጅቡቲ፣ ግብፅ እና ሱዳን ከሚገኘው የኣሜሪካ የጦር ሰፈር ይታገዛል።

በሌላ በኩል ኣለማቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር የሓሰት ፕሮፓጋንዳ የሚነፉለት CNN, Aljazira, BBC ን ጨምሮ ብዙ ኣለማቀፍ ሚዲያዎች ዝግጅት እያደረጉ ነው።

የኣሁኑ የሽብር እቅድ የኢትዮዽያ እና የኤርትራ የመደብ ጠላት የሆነው የሽብር ቡድን ቀጠናውን የጦር ኣውድማ በማድርግ ታላቂቱን ትግራይ እውን የማድረግ ህልም እንዲሳካካለት የኣሜሪካና የግብፅ ጫማ ጠራጊ ሆኖ ቢከሰትም የጋላቢዎቹ እና የሽብር ቡድኑ ህልም ቅዠት ሆኖ ቀርቶ ቡድኑም እስከወዲያኛው ድረስ የሚቀበርበት ቀን መቃረቡን ኣመላካች ነው።

ህውሃት ከማይጋባ እስከ መደማመር ድረስ ባለው ቦታ ሌሊቱን ጦርነት ከፍቶ አድሯል!!!

እስከ 500 ሺ የሽምቅ ተዋጊዎችን ሲያሰለጥን የቆየው ቡድኑ የቀን ቀጠሮ በሰጠበት ግንቦት 3 ጦርነቱን ጀምሯል።

እንዲሁም በኤርትራ አዋሳኝ ቦታዎችም በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ ትንኮሳ መጀመራቸው ታውቋል።

እንዲሁም በአበርገሌና በራያ አቅጣጫዎች ተዋጊዎቹን እያስጠጋ ነው።

Filed in: Amharic