>

" በመንግስት ታጣቂዎች 297 ሰዎች  ተገድለዋል 500 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል!!!".( ኦፌኮ)

” በመንግስት ታጣቂዎች 297 ሰዎች  ተገድለዋል 500 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል!!!”.

ኦፌኮ

 

(   ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፦ )

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ 297 ሰዎች በመንግስት ታጣቂዎች ተገድለዋል አለ። ፓርቲው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ነው ባለው “ደም አፋሳሽ ጦርነት” ምክንያት ከ500 ሺህ ሰዎች በላይ መፈናቀላቸውን አስታውቋል።

ኦፌኮ ይህን ያለው ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 6፤ 2014 ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው። ፓርቲው በመግለጫው ቅድሚያ የሰጠው በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ይስተዋላሉ ላለቸው “የፖለቲካ ውድቀት፣ የእርስ በእርስ ጦርነት እና የኢኮኖሚ ቀውስ” ክስተቶች ነው።

እነዚህ እርስ በእርስ የተሳሰሩ ክስተቶች “ኢትዮጵያን እያናጉ ያሉ አዙሪቶች ናቸው” ያለው ኦፌኮ፤ ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔው በሀገሪቱ ያለውን የእርስ በእርስ “ጦርነት በማስቆም ችግሮችን ወደ ፖለቲካ ድርድር መድረክ ማምጣት ነው” ሲል ከችግሮቹ መውጫ መንገዱን ጠቁሟል። ፓርቲው በኢትዮጵያ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት መቋጫ ካላገኘ፤ “የሀገሪቱ ፖለቲካው እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የበለጠ እየጠነከረና እየተወሳሰበ መሄዱ አይቀርም” ሲልም አስጠንቅቋል።

የኦፌኮ የህዝብ ግንኙነት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ቃሲም በንባብ ያሰሙትን የፓርቲውን ሙሉ መግለጫ ለመመልከት ከታች የተያያዘውን ቪዲዮ ይጫኑ።

https://fb.watch/cYSFjiUHxx/

Filed in: Amharic