>

አንጋፋው ጋዜጠኛና የታሪክ ጸሐፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ታፍነዋል!!

አንጋፋው ጋዜጠኛና የታሪክ ጸሐፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ታፍነዋል!!

ባልደራስ


*….ቤታቸው ተፈተሸ!!

*… ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ ወደ ባሕር ዳር ተወስደዋል!!

አንጋፋው ጋዜጠኛና የታሪክ ጸሐፊ ታዴዎስ ታንቱ ትናንት ረቡዕ፤ ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. እኩለ ቀን 6 ሰዓት ላይ ከቤት እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ጸጋ ሞገስ አረጋግጠዋል።

እስከ ምሽት 1:30 ወደ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልካቸው ሲደወል ሲጠራ የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ተዘግቷል።

ድታዴዎስ የኦሕዴ-ብልፅግናን የኦሮሙማ አገዛዝ በድፍረት በመፅሐፎቻቸውና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የሚተቹ ናቸው።

በዚህም የተነሳ በተደጋጋሚ በአገዛዙ ሲታፈኑ ኖረዋል። ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ጭምር በኦሮሞ ፖሊስ ለወራት ከአዲስ አበባ ውጭ ተወስደው ታፍነው ቆይተዋል።

ተጨማሪ መረጃ:-

አንጋፋው ጋዜጠኛና የታሪክ ጸሐፊ ታዴዎስ ታንቱ ማዕላዊ እንደሚገኙ ተረጋገጠ—-ቤታቸው ተፈተሸ!!

ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ ወደ ባሕር ዳር ተወስደዋል!!

ትናንት ረቡዕ፤ ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በወጡበት በፖሊስ ታፍነው የታሰሩት አንጋፋው ጋዜጠኛና የታሪክ ጸሐፊ ታዴዎስ ታንቱ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ (ማዕላዊ) እንደሚገኙ ለቤተቦቻቸው ተናግረዋል።

ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት ከ5 ፖሊሶች ጋር ወደ ቤታቸው ሄደው በ3 መርማሪ ፖሊሶች ቤታቸው መበርበሩን ባለቤታቸው ወ/ሮ ጸጋ ሞገስ ተናግረዋል። በዚህ ጊዜ ነው ማዕከላዊ እንደሚገኙ የተናገሩት።

በብርበራው ለውንጀላ የሚያበቃ አንዳች ቁስ አልተገኘም። መፅሐፎቻቸውን ብቻ አገላብጠው መልሰው ወደ እስር ቤት እንደወሰዷቸው ባለቤታቸው ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና፣ ከአዲስ አበባ ታፍነው የሰነበቱት ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ወደ ባሕር ዳር መወሰዳቸው ትናንት አመሻሽ ይፋ ሆኗል። በባሕር ዳር ቀበሌ ዘጠኝ የሚገኝ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረዋል።

Filed in: Amharic