>

"የአጉራ ዘለሎች ስብስብ የሆነው አፋኙ መንግስት መስከረም አበራን ከአዲስ አበባ ኤርፖርት አፍኗታል...!!!" (ጋዜጠኛ መዐዛ መሃመድ) 

“የአጉራ ዘለሎች ስብስብ የሆነው አፋኙ መንግስት መስከረም አበራን ከአዲስ አበባ ኤርፖርት አፍኗታል…!!!”
ጋዜጠኛ መዐዛ መሃመድ 


*…. መንግስት ሆይ በሀሳብ የሚሞግትህን ሁሉ እያሰርክ ስንት ዘመን ልትገዛ ይሆን…???
የመንግስት ቁመና የሌለው ፤ በፍርሃት ቆፈን የተተበተበ ፤ የአጉራ ዘለሎች ስብስብ የሆነው አፋኙ መንግስት መስከረም አበራን ከአዲስ አበባ ኤርፖርት አፍኗታል።  ከባህርዳር አዲስ አበባ ስትደረስ ወደ ቢሮ ሲወስዷት ያየ ግለሰብ ነግሮኛል። ከዛ በኋላም ባለቤቷም ስልኳ እንደማታነሳ አረጋግጦልኛል።
ሀሳብን አሰሩት ፈርተውት መሞገት
አጎንብሶ ‘ሚሄድ ቢፈልጉ አንገት ።
Filed in: Amharic