>

የጎንደር ፋኖ ታሪክ ሰራ... ፋኖ ሸርብ አቸነፍን አስለቅቀዋል...!!! (አማራ ሚዲያ ማዕከል)

ጎንደር ፋኖ ታሪክ ሰራ… ፋኖ ሸርብ አቸነፍን አስለቅቀዋል…!!!

አማራ ሚዲያ ማዕከል


*…. ፋኖ አሸናፊ አለሙ ሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለውይይት ተጠርቶ በሄደበት በመንግስታዊ አፋኝ ቡድን ታፈነ።

የምስራቅ አማራ ፋኖ የትራንስፖርት ስምሪት ኃላፊ እና የወልድያ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ፋኖ አሸናፊ አለሙ ሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ በኮማንድ ፖስት አመራሮች ለውይይት ትፈለጋለህ በሚል ተጠርቶ በሄደበት አፈና ተፈጽሞበታል።

በወልድያ ከተማ በርካታ የምስራቅ አማራ ፋኖ አባላትንና ደጋፊዎችን ግንቦት 12/2014 በቡድን መሳሪያ ጭምር ተኩሶ የገደለው መንግስታዊ አፋኝ ቡድን ምሽት ላይ ለውይይት እንፈልግሃለን በሚል የጠራውን የምስራቅ አማራ ፋኖ የትራንስፖርት ስምሪት ኃላፊ እና የወልድያ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ፋኖ አሸናፊ አለሙን ማሰ

ኮማንደር ተመስገን በአሸናፊ የእጅ ስልክ በመጠቀም ወደ ሌሎች የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮችና አባላት በመደወል “አሸናፊ ለውይይት ፖሊስ መምሪያ ገብቷል፤ እናንተንም ኑ እያላችሁ ነው!” በማለት ለማፈን ያደረጉት ሙከራ  ቀድመው በመንቃታቸው መክሸፉም ተገልጧል።

በተያያዘ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ጫንድባ በተባለ አካባቢ ግንቦት 12/2014 ምሽት መንግስታዊ አፈና የተፈጸመበትን ፋኖ ሸርብ አቸነፍን

የአካባቢው ፋኖ እና ህዝቡ በጋራ ባደረጉት ርብርብ አስለቅቀዋል።

“ህግ መስሎን ነው እንጅ ጨዋታው ከተቀየረ እና የአማራ ጀግኖችን ለማዳከም ያለመ ደመ ነፍሳዊ የአባ ጉልቤን መንገድ መከተሉ ይሻላል ካላችሁማ እኛም እምቢ ማለቱን እናውቅበታለን” በማለት ሾፌርና ፓትሮሎችን በመያዝ በር በሩን ዘግቶ ካደረ በኋላ ስለእሱ ሲታገልለትና ከባድ መስዋዕትነት ሲከፍልለት የቆዬውን ፋኖ ሸርብ አቸነፍን ከአፋኞች መንጋጋ ግንቦት 13/2014 ማስለቀቁ ታውቋል።

ራያ ቆቦ፣ መርሳ፣ወልድያ፣ቦረና መካነ ሰላም፣ ጭልጋ ጫንድባ፣እስቴ መካነ እየሱስ፣ መርጦለማርያም፣ ሞጣ፣መራዊ እና ሌሎችም ከአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ጎን መሆናቸውን አፈናውን በመቃወም በተግባር አሳይተዋል።

አንዳንዶቹ ፋኖን በመግደል፣በማፈን፣በማሰር፣ ትጥቅ በማስፈታት፣ በማሳደድና በመበተን አማራን ለማዳከም ታስቦ የመጣ ነው ያሉትን መንግስታዊ ሽብር (አፈና) በአደባባይ በመቃወም ውድ ህይወታቸውን ጭምር አሳልፈው በመስጠት ፋኖን እየታደጉ ነው።

ክብር በሰሜን ሜጫ መርዓዊ፣ በሞጣ እና በወልድያ ለተሰው ጀግኖቻችን ይሁን!

ፍትህ አፈናን በመቃወማቸው ለተገደሉ ለንጹሃን!

ፍትህ በአማራዊ ማንነታቸው፣ በለውጥ ፈላጊነታቸውና በግፍ ጠልነታቸው ለታፈኑ ለአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ይሁን!

Filed in: Amharic