>

የኦህዴድ/ኦነግ ከህወሃት ጋር መጣመር: የአማራ ተቆርቋሪዎች አፈናና የእባጭ አማራ አክቲቪስቶች ሚና...!!! (ጌታነህ ካሣሁን)

የኦህዴድ/ኦነግ ከህወሃት ጋር መጣመር: የአማራ ተቆርቋሪዎች አፈናና የእባጭ አማራ አክቲቪስቶች ሚና…!!!

ጌታነህ ካሣሁን

 

• ኦህዴድ/ኦፌኮ/ኦነግ እና ህወሃት በስትራቴጅግ ደረጃ ስለ አማራ ህዝብ ጠላት መሆንና የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት ፈርሶ እነሱን መስሎ መሰራት ወይም መበታተን እንዳለበት ልዩነት ኖሯቸው አያውቁም:: እነዚህ እራሳቸውን የ”ኮንፌደራል” ኃይል ብለው የሰየሙት ሀገር አጥፊዎች ለጊዜው “ማን አውራ ሆኖ ዝርፊያውን በበላይነት ያሳልጥ” በሚል ቢጣሉም ውለው አድረው በአማራው አንገት ላይ እየተደራደሩና በምእራባውያን የታገዘ የተኩስ አቁም ስምምነትን ጨምረው እየተስማሙና እየተረዳዱ ይገኛል::

 የአብይ አህመድ ክህደት

ኦህዴድ/ኦነግ ለህወሓት እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ እመራዋለሁ በሚለው ህዝብ በአለም ታይቶ የማይታወቅ ክህደት ፈፅሟል:: እግሩ እስኪቀጥን ህወሃትን ለማስደሰት ለፍቷል:: እነ ስብሃት ነጋን: አባዲ ዘሙንና አባይ ወልዱን ከእስር ፈታና እነ ታምራት ነገራንና ታዲዮስ ታንቱንና ሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ማሳደድ ጀመረ:: ወያኔ ጠለምትን: ዋግንና ራያን እንደያዘ እንዲቆይ በማመቻቸትና በቂ ጊዜ አግኝቶ እንዲደራጅ ከማመቻቸትም አልፎ አሁን ለሰራዊቱ በቂ ቀለብና ነዳጅ እያቀረበ ይገኛል:: ይህ የአብይ አህመድ ክህደት በሁሉም የኦነግ ክንፎች የተደገፈ የጋራ የኦሮሙማ አቋም ነው::

 አዲስ አበባ እና ወልቃይት

ያለ ባጀትና ያለመብራት የሚያሰቃያትን ወልቃይትንም ለወያኔ ለመመለስ እንቅፋት የሆነበትን የአፈፃፅም ጉዳይ ነው( አማራና ኤርትራ):: ቀላሉ ሆኖ ያገኘው የአማራ ህዝብን መከፋፈልና ውስጣዊ ቀውስ መፍጠርን ነው:: አብይ ይህን ኦፐሬሽን ለብአዴን የሚሸጥለት “ኦሮሞ ክልል ኦነግ-ሸኔን እያጠፋን ስለሆነ እናንተም ፋኖን አጥፉ” በሚል false equivalence ነው:: ፋኖ የወያኔን ወረራ በደሙ ሲመክት በኦህዴድ የሚታጠቀው ኦነግ ግን የወያኔ ተባባሪና የአማራ ሴትና ህፃን አራጅ ነው:: ኦህዴድ ኦነግ-ሸኔን እንደ ፓራ-ሚሊተርይ የሚጠቀምበት ኦህዴድ/ኦነግ/ኦፌኮ አሁን “አማራ ክልል” የሚባለውን አካባቢ ለመበታተን በህወህት የተጀመረውን ፕሮጀክት እየፈፀሙ ይገኛል:: በወሎና ጎጃም አገውን ለመነጠል በጎንደር የቅማንትን ካርድ በማንሳት (የሀይማኖቱንም ዳይሜንሽን ሳንጨምር):: ኦህዴድ አማራን ሲያሳድድ ከህወሃት በተራዋ ኤርትራ ላይ ጦርነት ብጤ ጀምራለች:: በሰሜንም በአማራም የኮንፌደራል ጦርነት!!!

በዚህ ላይ አማራው ሲወጠር ኦህዴድ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ናት በሚል በሙሉ ብማወጅ ምናልባትም የአማራ ነዋሪዎችን ማፈናቀል ይጀምራል:: ኦነግ/ኦህዴድ አዲስ አበባና ኢትዮጵያ ፈርሳ ቤተክርስቲያኖችና ባህሉ ተቀይሮ አማራ የሌለበት “ኦሮሙማ” በማድረግ እንጅ መንግስት በመሆን አይረካም::

ዛሬ የአማራ የፖለቲካ ማንነት የግድ የሆነበት ምክንያት ለ50 ዓመት ጠላት ስለተደረገና አስከፊ ጭፍጨፋና ግፍ ስለደረሰበት እና የዛሬ የእልቂት አደጋclear and present danger ስላለበት ነው:: የጎጃም ወይም ሸዋ ወይም የሀረር ወዘተ  የአካባቢ የባህል ማንነት እንጅ የፖለቲካ ማንነት ሊኖረው አይችም:: እንደ አማራ እየተግደልህ እንደ ጎንደር ወይም ወሎ ብትደራጅ በጠላትነት ተፈርጀህ እልቂት ይጠብቅሃል እንጅ አትድንም:: ወለጋን “ምእራብ ኦሮሚያ” ብለው ሁሉም የኦነግ ክንፎችና ሚዲያወቻቸው የሚጠሩት አንድ የኦሮሞ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር ነው::

ታዲያ ይህን ማገናዘብ ያቃታቸው ወይም ሆን ብለው እያወቁ “ከኦህዴድ/ኦነግ አጋር ጋር ብንሆን እንጠቀማለን?” በሚል/በሚመስል የእባጭ አስተሳሰብ ሰሞኑን በተለይም በወሎና ጎጃም ላይ በተላላኪው የአማራ ህዝብ ካንሰር በሆነው ብአዴን አማካኝነት የሚደረገውን የአማራ ተቆርቋሪዎችን መንግስታዊ ሽብር: ግድያና አፈና በመደገፍ ያሉ አክቲቪስቶች: የተወሰኑ የአብን አመራሮችና አጋሮቻቸው ኦህዴድን መደገፍ ብቻ ሳይሆን ይህን መንግስታዊ አፈናና ሽብርን የሚቃወሙትን ጭራሽ የወያኔ ደጋፊ ብለው ሊፈርጁ ይሞክራሉ::

በዚህ አጋጣሚ “ከኦህዴድ ጋር ሁነን እነ እገሌን እናስመታለን… እገለ የአማራ ባለሀብትን እናሳስራለን” የሚሉ የጎጥ አክቲቪስትና የፖለቲካ ተዋናኞች ስለሚያደርጉት ነገር ተጨባጭ መረጃ አለን::

ከወያኔ ጋር ተናቦ ሚሰራው የአማራ ጠልነትን መንግታዊ ቅርፅ የሰጡ የህወሃት መስራቾችን በመፍታት ተፈራ ማሞን የሚያፍነው እኮ እናንተው ምትደግፉትና የምትከላከሉለት ኦህዴድ/ኦነግ ነው:: የህወሃት ስትራቴጅግ አጋር የሆነውን ኦህዴድ/ኦነግን እየደገፉ ሌላውን በህወሃት ደጋፊነት መፈረጅ ቅንጨራዊ-ክህደት ነው::  ኦህዴድን መደገፍ ስታራቴጅግ አጋሩን ህወሃትን እንደመደገፍ እንደሆነ ለማየት እንዴት የወንድም ጥላቻ ያውራቸዋል?

ወልቃይት ለወያኔ መመለስም አደጋም ሆነ የአዲስ አበባን በኦሮሙማ ዘንዶ መሰለቀጥንና የኢትዮጵያ ህልውና የማክተም አደጋን እያጋለጡ ያሉ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የሚሰሩ እነዚህ እባጮችና ጨብራራ ተንካሽ ተላላኪዎቻቸው ናቸው::

ኦህዴድ/ኦነግ/ኦፌኮና ህወሓት ስራቸውን እየሰሩ ነው:: እነዚህ  (አንዳንዶች በአካልም በአስተሳስብም የቀነጨሩ: አንዳንዶችም የምፅዋቅት ሳጥን ሰባሪዎች) እባጮች የራሳቸውን አስበው ለህዝባቸው መስራት ቢያቅታቸው የአማራን ህዝብ ጥቃት ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ያሉ ወንድሞቻቸውንና ለማሳሰርና ለማስገደል የኦህዴድ/ኦፌኮ/ኦነግ ወያኔ እጀታ መሆናቸውን ፈፅሞ ይቅር ልንለው አይገባም::

Filed in: Amharic