>

ከአማራ ወጣቶች ማህበር አዲስ አበባ ሸዋ ቅርንጫፍ የተሰጠ የአቋም መግለጫ፦

ከአማራ ወጣቶች ማህበር አዲስ አበባ ሸዋ ቅርንጫፍ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
ከሰሞኑ ፋኖ ላይ እየተደረገ ያለው የጦር ዘመቻ፣ በአማራ ጋዜጠኞች፣ የማሕበረሰብ አንቂዎችና ፖለቲከኞች ላይ እንዲሁም ፖለቲካዊ ንቃታቸው ከፍ ባለ አማሮች ላይ ሁሉ እየተፈፀመ ያለው እስራት፣ አፈ እና ወከባ ኦሮሞ መር የሆነው መንግስት አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የሚያደርገው ወረራ ዋነኛ አካል ሆኖ አግኝተነዋል። ይህ አጥፍቶ የመውረር እንቅስቃሴ ርዕዮተ ዓለማዊ መሰረት ያለው እንደሆነም እናምናለን።
 ከምንግዜውም በበለጠ በኦሆዴድ/ብልፅግና ዘመን አማራ በጅምላ ተገድሎ፤ በጅምላ የሚቀበር ህዝብ ሆኗል::
እኛ የአማራ ወጣቶች እስከአሁን ለአብሮነት ስንል ታግሰናል::ነገር ግን ጨፍጫፊዎች የአውሬነት ባህሪን እየተላበሱ፤ ይበልጥ ከሰባዊነት እየራቁ መጥተዋል:: መንግስት ከግብረ አበሮቹ ጋር በአማራ ላይ የሚያደርሰውን የዘር ፍጅት፣ ወከባ አፈና እና ማሳደድ ብሎም በፋኖ ላይ የአወጀውን ተደብቆ የማጥቃት የክህደት ውጊያ በአስቸኳይ የማያቆም ከሆነ እራሳችንን ከግድያ የመከላከል ተፈጥሯዊ መብታችንን ለመጠቀም የምንገደድ መሆኑን እናሳውቃለን::
በአዲስ አበባ አማራ የሆንን ሁሉ እያሳደዱ ማፈን፣ ማሰርና ማገት በአስቸኳይ የማይቆም ከሆነ እኛ በአፅመ እርስታችን አዲስ አበባ የምንኖር የአማራ ወጣቶች ከዚህ በላይ የማንታገስ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን:: በመሆኑም፦
 ፩. መንግስት ወደ አማራ ህዝባዊ ሆይል (ፋኖ) ሰብሳቢ አርበኛ ዘመነ ካሴ አፈ ሙዝ ማዞሩ እጅግ የከፋ ደም አፋሳሽ ድርጊት መሆኑን አውቆ ከዚህ ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲታቀብ እናሳስባለን::
፪. መንግስት ጀግኖች ፋኖዎች በሌሉበት ቤታችውን እየበረበረ ጭምር ከፋኖ የነጠቃቸውን መሳሪያዎች እንዲመልስ እንጠይቃለን::
፫. በተለያዩ የአማራ ከተሞች በተለይም በሞጣ፣ በወልዲያ እና በመርዓዊ በንፁሀን ህይወት ላይ እና በንብረት ላይ ላደረሰው ጉዳት መንግስት ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን::
፬. በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ እና በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ)  አባላትና አመራሮች ላይ እንዲሁም ብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን እና አንጋፋው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱን ጨምሮ  በአማራዊ አስተሳሰባቸው ምክንያት የታሰሩት ሁሉ በአስቸኳይ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ዶሴው ተቋርጦ  እንዲፈቱ እንጠይቃለን::
አማራነት ወንጀል አይደለም!
 ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም.
የአማራ ወጣቶች ማህበር አዲስ አበባ ሽዋ ቅርንጫፍ
 አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ!
Filed in: Amharic