>

አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለዉን የጅምላ እስር ተቃወመች...!!! (DW)

አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለዉን የጅምላ እስር ተቃወመች…!!!

DW


የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን በጋዜጠኞችና ማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ የሚያካሄደው ጅምላ እስር አሜሪካን እንዳሳሰባት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ በማኅበራዊ ገጹ አስታወቀ። የኢትዮጵያ የፌደራል እና የክልል መንግሥታት በሚወስዷቸው ርምጃዎች ሕጋዊ አሠራሩን እና የሕግ የበላይትን እንዲከተሉ አሜሪካ አሳስባለች። አዲስ አበባ የሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ ባደረገዉ የጽሑፍ መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለዉ የሰብአዊ መብቶች መርሆዎችን ያልተከተለና የተስፋፋ እስር ተገቢ አይደለም ሲል ያወጣውን መግለጫ አሜሪካ እንደምትጋራ ገልፆአል። የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረዉ የጅምላ እስር ተገቢ ነዉ ይላሉ? መንግሥት ምን መፍትሄን መዉሰድ ይገባዋል? አስተያየቶን ይፃፉልን!

Filed in: Amharic