>

ፖሊስ በጎጃም ቢቡኝ የ13 ዓመትን ልጅ ፋኖ በሚል በጥይት ገደለ!

ፖሊስ በጎጃም ቢቡኝ የ13 ዓመትን ልጅ ፋኖ በሚል በጥይት ገደለ!
በአካባቢው ፋኖ አወቀ መንጌ ተገድሏል!

ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት በምስራቅ ጎጃም ዞን፤ ቢቡኝ ወረዳ፤ የወይን ውሃ ከተማ አቅራቢያ የዘመተው የኦሕዴድ-ብልፅግና ገዳይ የወታደሮች ዕዝ ልንገረው አዲስ የተባለ 13 ዓመት አዳጊ ልጅን ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ገድሏል። የፖሊሶች ቡድን በ3 ጥይት ደጋግሞ ቤት ውስጥ በመደብደብ ነው ‘ፋኖ ነህ’ በሚል ፍረጃ ሕፃኑን የገደለው። ሟቹ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በወቅቱ ከብቶችን እየጠበቀ ነበር።
በተመሳሳይ በዚያው በቢቡኝ ፋኖ አወቀ መንጌ ከሕፃኑ መሰዋት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በፖሊስ ተገድሏል። ይህ ግድያ በሜዳ ላይ ሲፈፀም የተመለከተው ሕፃን ልንገረው ድርጊቱን ለመናገር ሩጦ ወደ ቤት ሄዷል። ሆኖም ታጣቂዎቹ በጥይት ተኩስ እያባረሩ ተከትለውት ከቤት ገቡ። ቤት ውስጥም ደጋግመው በቤተሰብ አባላትና በጎረቤት ፊት በጥይት በመደብደብ ገድለውታል። አስክሬኑን ጎትተው ከቤት አውጥተው በር ላይ በመጣል “ተባራሪ ጥይት ገደለው በሉ” የሚል ማስጠንቀቂያ ተናግረው እንደሄዱ ያነጋገርናቸው የቤተሰቡ አባላት ገልፀዋል።
የፋኖ አወቀ መንጌ እና የሕፃን ልንገረው አዲስ የቀብር ስነ ስርዓት በዚያው በተሰውበት ዕለት፤ በተገደሉበት ስፍራ ማለትም በቢቡኝ ወረዳ፤ በደብረ ሲና አስማረ ቀበሌ፤ በጋፋት ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል። (ጌ.ያ)
Filed in: Amharic